– ሲያትል በኢትዮጵያ ቀን አሸብርቃ ነበር
– ሃመልማል አባተ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ያድርግልኝ አለች
– ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ እና ሻምበል በላይነህ ተጋባዥ ነበሩ
/Ethiopia Nege News/:- በኢትዮጵያዊያን ስፖርትና ባህል ፌስቲቫል ታሪክ ከመክፈቻው ጀምሮ ሙሉ ሳምንት በድምቀት የተከበረበት የመጀመሪያው ነው የተባለለትና በርካታ ኢትዮጵያዊያን የተሰባሰቡበት ክብረ በአል በድምቀት ተጠናቀቀ፡፡
በመክፈቻው የኢትዮጵያ ባንዲራ ወደ ስቴድዮሙ በፓራሹት ሲወርድ ታዳሚውን ያስደመመው የሲያትሉ የስፖርትና ባህል በአል ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን አካቶ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡
በምግብ ሽያጭ፡ የተለያዩ ሃገራዊ እቃወችና ቅርሳቅርሶች በመገበያያ ድንኳኖች ውስጥ ልዩ ልዩ እቃዎች ሲቸበቸቡ ከመሰንበታችውም በላይ የኢትዮጵያ ባንድራ የታተሙባቸው ቲሸርቶች፡ ቦርሳዎች፡ ጃኬቶችና የቁልፍ መያዣዎች የገበያውን አጣበውት ነበር፡፡ በተጨማሪ እየወጣና እየገባ ይርመሰመስ የነበረው ህዝብ ወደ 30 ሺህ ይደርሳል የሚል ግምት የተሰጠው ሲሆን በርካታ ታዳሚዎች የኢትዮጵያ ባንዲራን ለብሰውና በጃቸው ይዘው ተስተውለዋል፡፡
ከተመሰረተ 34ኛ አመቱን ያከበረው ኢ.ኤስ.ኤፍ.ኤን.ኤ በተለያዩ ጊዜያት ራሱን እያሳደገ እንደመጣ የሚታወቅ ሲሆን ላለፉት ጥቂት አመታት በሃብታሙ ሼክ ሙሃመድ አላሙዲንና አብነት ባቋቋሙት ተለጣፊ ድርጅት ውድድር ውስጥ ገብቶ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ኢ.ኤስ.ኤፍ.ኤን.ኤ ላለፉት ጥቂት አመታት ከፍተኛ ህዝባዊ ተቀባይነትን በማግኝቱ ተለጣፊው በእነ አብነት ተቋም በዘንድሮው አመት ምንም አይነት ዝግጅት ሳያደርግ ቀርቷል፡፡
የዘንድሮው በአል ተመልካች እጅግ በርካታ ከመሆኑም ባሻገር በተለያዩ መገናኛ ብዙሃንና ማህበራዊ ድረገጾች በቪድዩ የተመለከቱ ኢትዮጵያዊያን ቁጥርም እጅግ በርካታ እንደነበር ለመረዳት ተችሏል፡፡
አርብ እለት በሚደረገው የኢትዮጵያ ቀን ዝግጅት ተጋባዥ ከነበሩት መካከል ሻምበል /ራስ/ በላይነህንና ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳን ጨምሮ የተለያዩ ድምጻዊያን ዝግጅታቸውን ያቀርውቡ ሲሆን ድምጻዊት ሀመልማል አባተ ከህዝብ ጉያ በመውጣቷ እንደተጸጸተች በመግለጽ የኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታ እንዲያደርግላት ጠይቃለች፡፡
ሀመልማል she is very smart women!!
ሲጀመር ህዝቡ ጥፋተኛ ስለሆነ ይቅርታ ይጠይቀን ነው ያለችው እንጂ እኔ ስላጠፋሁ ይቅርታ ይደረግልኝ አላለችም ።
መልክቱን ደጋግመኽ አድምጠው
ደንቆሮ ሁላ።