ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩና ዳንኤል ሺበሺ የዋስትና መብት

ጋዜጠኛ ኤሊያስ ገብሩና ዳንኤል ሺበሺ የዋስትና መብት

/Ethiopia Nege News/:- በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሰበብ ከ8 ወራት በላይ በእስር የቆዩት ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩና የከድሞው አንድነት ፖርቲ ከፍተኛ አመራር የነበረው አቶ ዳንኤል ሽበሺ በ50 ሽህ ብር ዋስ ወጥተው ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ የቦሌ ክ/ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሰሚት ምድብ ችሎት ብይን ሰጠ።

“ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተለያዩ ደንቦች በመተላለፍ፤ የፀረ-ሽብር ቡድኖችን የሚያበረታታ ምስል በመያዝ” የሚል ክስ የመሰረተባቸው አቃቤ ህግ ችሎቱ በዝግ እንዲታይለት ፍ/ቤቱን ጠይቆ ተቀባይነት በማግኘቱ የፍርድ ሂደቱ በዝግ እየታየ ነው።

ዛሬ የተሰየመው ችሎት ተከሳሾቹ ለእያንዳንዳቸው በ50 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ እንዲሁም የፍርድ ሂደቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከሀገር እንዳይወጡ ማ/ቤቱ የተከሳሾችን የፎቶና ሌሎች መራጃዎችን ለብሔራዊ ደኅንነት እንዲልክ ውሳኔ ሰጥቷል።ችሎቱም በዝግ መታየቱ ይቀጥል ተብሏል።

አቶ ዳንኤል ሽበሺ ቀድሞ ከቀረበበት የሽብር ክስ በነፃ እንዲወጣ ከተበየነለት በኋላ አቃቤ ህግ ይግባኝ ጠይቆ፤ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሽብር ክሱን እንዲከላከል ብይን በሰጠው መሰረት ጉዳዩ በከፍተኛው ፍ/ቤት እየታየ በመሆኑ ዋስትናው ያስፈታው አያስፈታው የታቀቀ ነገር የለም።

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ የእንቁ መጽሔት ዋና አዘጋጅ በነበረበት ጊዜ መጋቢት 2006 ዓ.ም በመጽሔቱ ላይ በታተመ ጹሁፍ ተከሶ ጥፋተኛ በመባሉ በ20 ሽህ ብር ዋስ ተፈቶ ጉዳዩን በውጭ ሆኖ እየተከታተለ እንደደነበረ ይታወቃል።ፍ/ቤቱ የጠየቀው የዋስትና የገንዘብ መጠን የዜጎችን አቅም ያላገናዘበ ነው በማለት አስተያየት በመስጠት ላይ ናቸው።

LEAVE A REPLY