የቴዎድሮስ ራዕይ በአውሮፓ ከተሞች ይታያል

የቴዎድሮስ ራዕይ በአውሮፓ ከተሞች ይታያል

በአንጋፋ የጥበብ ሰዎች የሚተወነው፤ በሰሜን አሜሪካ አድናቂነትን ያተረፈው ‹‹የቴዎድሮስ ራዕይ›› የተሰኘው ተውኔት ከመጭው ወር ጀምሮ በአውሮፓ ከተሞች እንደሚዘዋወር አርቲስት አለምጸሃይ ወዳጆ ገልጻለች።

የአጤ ቴዎድሮስን የጀግንነት ታሪክ ላይ በመመርኮዝ የተሰራው ይህ ድንቅ ቲያትር በቴክኒክ ብቃቱ እንከን የለሽ ቲያትር እንደሆነ የጥበብ አፍቃሪዎች መስክረውለታል። ቲያትሩ በይዘቱ ይህንን ትውልድ በኢትዮጵያዊነት ኩራት የሚያጸና፤ የአኩሪ ታሪካችን አሻራ በመሆኑ ሁሉም ሊያዩት ይገባል።

እስካሁን በደረሰን መረጃ መሰረት የቴዎድሮስ “ራዕይ” የሚታይባቸው የአውሮፓ ከተሞች የሚከተሉት ናቸው።

ሴፕቴምበር 15 – በርሊን
ሴፕቴምበር 16 – ፓሪስ(ገና ያልተረጋገጠ)
ሴፕቴምበር 17 – ፍራንክፈርት
ሴፕቴምበር 23 – አመስተርዳም
ሴፕቴምበር 24 – በርገን
ሴፕቴምበር 30 – ኦስሎ
ኦክተበር 1 – ስቶኮልም
ኦክተበር 7 – ዙሪክ
ኦክተበር 8 – ኑረንበርግ

አድራሻ እና የበለጠ መረጃ ለማግኘት የየሃገሩ አዘጋጆችን ማነጋገር ይቻላል- የቴዎድሮስ ራዕይን ድንቅ ተውኔት የማየት ይህ አንድ እድል አያምልጣችሁ!

LEAVE A REPLY