የምዬ ምኒሊክ እትብት የያዘች ሰፍራ አንጎላላ! /ታሪኩ ደሳለኝ/

የምዬ ምኒሊክ እትብት የያዘች ሰፍራ አንጎላላ! /ታሪኩ ደሳለኝ/

ኢትዮጲያ የማን ሆና ነው እኔ መሬት የምወስደው” አፄ ምኒሊክ

እዚህ መንደር ንጉሥ ተወልዶል እዚህ ቦታ የንጉሥ እትብት ተቀብሯል አዚህ ቦታ አኛን ብቻ ሳይሆን መላውን የዓለም ጥቁር ህዝብ ቀና እንዲል መልክት የሆነው ምኒልክ ተወልዶል።

ደብረ ብርሃ ይበልጥ ብርሃን ሆናለች። አንጎላላ ስንደርስ የክረምት ቀትር ነው የማያቃጥል የማይወብቅ ግን ለብ የሚያደርግ በዚህ ላይ የምዬ ምኒሊክ የተወለዱበት ቦታ በአይን ማየት በእጅ መንካት ሲጨመር ብርሃኑ ይበልጥ ይበራል።

ምኒሊክ የተወለዱበት ቦታ አሁን ክሊኒክ ሆኖል ሀውልታቸውም እዛው ይገኛል ከምኒሊክ መታሰቢያ ሀውልት በስተቀኝ በለስላሳ ስራ ግን አረም በወረረው መንገድ 5 ሜትር ሲሄዱ አፄ ምኒሊክ የተወለዱበት ቤትና እትብታቸው የተቀበረበት ሠፈራ በሽቦ ታጥሮ ይገኛል። ይህን ቦታ መመልከት ምን ይህል ልብን በደስታ እንደሚያዘልል ቦታውን የረገጠ ይረዳዋል።

ይህ ጉዞ በጥቂት ሰዎች 2007ዓም ላይ የተደረ ሲሆን 2008ዓም ላይ አልተደረገም ዛሬ አብዛኞዎቻችን የመጀመሪያ ጉዞችንን ማድረጋችን ነው። 28 ሆነን አንጎላላ ስንገባ ቦታው ላይ ይገኘናቸው በክሊኒኩ ውስጥ ህክምና ሊያገኙ የመጡ 2 አርሷደሮችና 1ቄስና ሁለት ሀኬሞች ብቻ ነበሩ።

በዶር ዳኛቸው አሰፋ የመታሰቢይ አበባ ሀውልታቸው ሰር በክበር ከኖረ በኃላ ደራሴ አለማየው ገላጋይ ሰለ አፄ ምኒሊክ አስተዳደርና ሩሩህነት የልባችን እስኪደርስ አወጋን ቀጥሎም በምንተስኖት ማሞ በአፄ ምኒሊክ ግዜ የተገጠሙ ግጥሞችን እያጣፈጠን ነገረን ከዛም በዶር ዳኛቸው አፄ ምኒሊክ በወቅቱ የነበረውን የጣሊያን ወራራን የመከቱበትን መንገድና ድሉ የፈጠረው ነገሮች አብራርተው መገቡን ከዛም ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም ድንቅ ግጥም ምኒሊክን በተመለከተ ለዛ ባለው ሁኔታ ጋበዘን ለጥቆም ገጣሚ ደምሰው መርሻ ከሎሬት ፀጋይ ገብረ መድህን ሚኒሊክ ከተሰኛው ተውነቴት ላይ በሚያሰገመግም ድምፁ ግጥም እየነበብ በመፈስ አዛ ቦታ ላይ ወሰደን እንዲሁም ብርሃኑ አየለ አፄ ምኒሊክ የሰሩት ስራ የመጣውን ለውጥ አብራራለን በዚህ መካከል ግን ድንገት የተቀለቀሉን ሦስት ወጣቶች መናገር እንፈልጋለን አሉ አንደኛው ወደ እምዬ ምኒሊክ ሀውልተ ተጠግቶ ቆመ እኛና ጓደኞቹን እየተመለከተ “የመጣነው ከደብረ ብርሃን ከተማ ነው 2007ዐዓም መምጣታቹህን ጋዜጣ ላይ አይተን 2008 ብንመጣም እናተ አልመጣችሁም ዛሬ ድንገት ከመጣቹ ብለን ነበር የመጣነው ይህው አገኘናችሁ ስለመጣችሁ በደብረ ብርሃን ህዝብ ስም አመሰግናለሁ ይህን የምለው ብግሌ ነው” እኛም ደስ አለን ወጣቱ ቀጠለ “እኔና ጓደኞቼ ሆነን በሚቀጥለው አመት ስትመጡ ዳቦና ጠላ አዘጋጅተን እንጠብቃችኃለን” አለን ተሳቅን። ከሀውልቱ በሾቦ ወደ ታጠረው የምዬ ምኒሊክ የተወለዱበት ቤት ወደነበረው ቦታ አመራን ዙረያውን ከበን ቆምን ምኒሊክን አሰብናቸው።

ከአዲሳባ አብረን የሄድነውም አንጎለሰላ የገኘናቸውም እርስ በእርስ ለመተዋወቅ ተብሎ ወደፊት እየወጣን ስማችንን እየተናገርን ተዋወቅ።

ዛሬ የንጉሳቸው የንጉሳችን ልደት መሆኑን አንጎላላ ወረዳና ደብረ ብርሃን ከተማ አልተረዱት ዳሩስ መንግስት መቼ ተገነዘበውና። የአንጉላላም ሆነ የደብረ ብርሃን አሰተዳደርና የሚመለከታቸው ክፍሎች እንዲሁም ከአንጎላላ 16 ኬሜ እርቀት ላይ የሚገኘው የደብረ ብርሃን ዩንቨርስቲስ ይህን የኛ ብቻ ሳይሆን የመላው ዓለም የጥቁር ህዝቦች ኩራት የሆኑትን የእምዬ ምኒሊክ የትውልድ ሠፍራ ምነው ዘነጋቹሁት? ዝምታችሁ ቢበዛም ግን እኛ ዛሬ የተወለዱበትን ቀን ምክኒያት በማድረግ እቦታው ላይ በደስታ ተገኝተናል።

እምዬ ምኒሊክ ክብርት ንግስት እቴጌ ጣይቱ ብርሃናችሁ እስከ ዓለም ዳርቻ እንዳበራ ዘላለም ይኖራል። እንድንከበር እንደራገቹህን ዘላለም ተከብራችሁ ትኖራላችሁ።

ታሪኩ ደሳለኝ
አንጎላላ
ነሐሴ 12/09ዓ.ም

LEAVE A REPLY