ጎንደርን በቅማንት ስም ለመከፋፈል ህወሓት እየሰራ ነው ተባለ

ጎንደርን በቅማንት ስም ለመከፋፈል ህወሓት እየሰራ ነው ተባለ

/ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና/፦ ጎንደርን በቅማንት ስም በመከፋፈል የተጀመረውን የነጻነት ትግል ለማዳከም ህወሓት እያሴረ ነው ተባለ። በአንድ ላይ ለዘመናት የኖረውን ህዝብ አማራና ቅማንት በማለት በመከፋፈል ላይ ነው።75 ያህል ቀበሌዎችን ከዚህ በፊት ለመነሻነት ወደ ቅማንት ብሔረሰብ አስተዳድር ከልሏል።መስከረም 7/2010 ዓ.ም ደግሞ የስርዓቱ አገልጋይ በሆነው “ምርጫ ቦርድ” አማካኝነት በ12 ቀበሌዎች ላይ የይስሙላ ህዝበ ውሳኔ ለማካሄድ እቅድ መያዙ ታውቋል።ምርጫ ቦርድ ህዝበ ውሳኔውን የሚያካሂደው ከፌዴሽን ም/ቤት በተሰጠው ውክልና መሰረት ነውም ተብሏል።

መስከረም 8/2010 ዓ.ም የህዝበ ውሳኔው ውጤት በየምርጫ ጣቢያዎቹ እንደሚለጠፍና የተጠቃለለው የህዝበ ውሳኔ ውጤት መስከረም 15/ 2010 ዓ.ም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት እንደሚልክ ታውቋል።

የአማራ ክልል መንግስት ከዚህ ቀደም “በቅማንት” የቀረበው የልዩ ማንነት ጥያቄ በህገ መንግስቱ የተቀመጡ መስፈርቶችን አያሟላም በማለት ውድቅ ተደርጎ የነበረ ቢሆንም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጣልቃ በመግባት ከሁለት ዓመት በፊት እውቅና መስጠቱ ይታወቃል።

በተመሳሳይ ሁኔታ የወልቃይት ህዝብ ያነሳውን የማንነት ጥያቄ የትግራይ ክልል ምላሽ ሲነፍጋቸው ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት ቢያመሩም ስልጣኑ የትግራይ ክልል ነው ተብለው መመለሳቸው ይታወቃል።

የህወሓት ካድሬዎችና የመንግስት ተለጣፊ የሆነው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አማራንና ቅማንትን ለመከፋፈል ለዓመታት ሲሰሩ ቆይተዋል። የጎንደርና አካባቢው ህዝብም ይህንን የመከፋፈል ሴራ ለማክሸፍ ምን ማድረግ እንዳለበት እየመከረና እቅድ እያወጣ እንደሚገኝ መረዳት ችለናል፡፡

LEAVE A REPLY