መስከረም 10 2010
በትግራይ ውስጥ ከ1993 ጀምሮ ለ17 አመት ምንም አይነት ግጭት ደርሶ አያውቅም። በተቀረው የኢትዮጵያ ክፍል ግን በወያኔ የተቀነባበረ ግጭት ጦርነትና አለመረጋጋት ሰፍኗል። በአንፃሩ ትግራይ 5 አለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያወች በደርዘን የሚቆጠሩ ከፍተኛ ፋብሪካወችና ከአምስት በላይ ዪኒቨርስቲወች ተገንብተዋል።
ትግራይ የተራቆቱ ምድረበዳ ተራራወቿን ከመንግስት ዳጎስ ያለ ብር በሚፈስላቸው ትግራውያንና አፈር ከደቡቡ ኢትዮጵያ በማጓጓዝ ደን እየለበሰ ያለ ምድር በመባል በአለም አቀፍ ደረጃ ሲሸለሙ እንቁልልጨ ሲሉን ሰንብተዋል። ምድረበዳ ያለውን ህዝባሸውን ግን ከእኛው ባድማ ወልቃይት ላይ ወደ 1 ሚሊዮን ትግሬ አስፍረውበታል። ይህ ዘግናኝ ሃቅ ነው። ትግራይ ውስጥ ልዩ ማንነት የጠየቁ ኢሮብ ኩናማና አፋር ሲገኙ ወልቃይትና ራያ ወደ ታሪካውይ ድንበራችን መልሱን ብለው ነበር። የአንዱም ጥያቄ አልተስተናገደም።
በአንፃሩ አዋሳኝ የሆነው ጎንደር ወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ወደ ትግራይ ተወስደውበታል። ጎንደር ውስጥ ጥንት ከነበረው አዘዞ አውሮፕላን ጣብያ ውጭ ሌላ የለም። ጎንደር ውስጥ ወያኔ ከገባ ጀምሮ 26 አመት ሙሉ አንድም አዲስ የተከፈተ ፋብሪካ የለም። ጎንደር በሰላም እንዳይኖር ቅማንት ተለይተህ ኑር እየተባለ ነው። ይህን እያየን እንዴት መታገስ ይቻላል? ይህን እያየን ስር የሰደደ ዘረኝነት አለ ስንል ማን አሌ ሊለን ይችላል?
የወገናችን የኦሮሞ ህዝብ ደም ደማችን ነው ስንል ስለኢትዮጵያ ስለምናስብ ነው። ከግንባራቸው አርቀው በማያስቡ የመንደር ወጠጤወች ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ሊመራ አይልችም። እነ አንዱአለም አራጌንና ዶር መረራን አሳስረን በባንዳ ልጆች ስንመራ ይከረፋል!
ዝም…አንልም…
የሃሳብ መግልፅ ነፃነቱ ጥሩ ሆኖ ግን ትግራይ ለማልማት አፈር ከደቡብ ማምጣት የሚለው እናም በቢቢሲ… “…በባንዳ ልጆች ስንመራ ይከረፋል!” እየመሩት ያሉ ባንዳ መሆናቸው አለመሆናቸው አከራካሪ ቢሆንም አባቶቻቸው ግን ጀግኖች ነበሩ እና ህዝብ እንደህዝብ ጥፋተኛ ማድረጉ ተገቢነቱ አይታየኝም