የሀዘን የቁጭት የምሬት የፀፀት የምፀት ደብዳቤ /ገጣሚ ማህሙድ እንድሪስ/

የሀዘን የቁጭት የምሬት የፀፀት የምፀት ደብዳቤ /ገጣሚ ማህሙድ እንድሪስ/

በጦርዎ ብርታት
እጅግ ለከበሩት
ያኔ ለሚፈሩት
አሁን ለታሰሩት ይድረስ ለሙጋቤ ፣
በጣም ያሳዝናል
ያጋጠመዎትን አስደንጋጭ ፈተና
የመታሰርዎን ድንገተኛ ዜና
ነግ በኔ ከማይሉ
ወሬ አቀባባዮች አሁን ሰማሁና
ወህኒ መውረድዎን በድሜዎ ፍፃሜ
ለጉድ ሲያናፍሱት
ከሀዘኔ በላይ እጅግ ተገርሜ
ምንምንኳ ባውቅም እንደማይሰርስዎ
የወዳጅበቴን
ትዝብቴን ቁጭቴን
ከኔ እንዳይቀር ብየ ይሄው ጻፍኩልዎ :—

ትዝይልወት ይሆን?
መጀመሪያ …. ያኔ
ለትግል ስንወጣ ባገር ፍቅር ቁጭት ተሞልተን በወኔ
ለእናት ምድራችንን
ለጭቁን ህዝባችን እንሙትለት ብለን
በእልህ በወኔ
መላውን አፍሪካ ነጻ ልናወጣ ታግለንና አታግለን
ለጥቁር ዘር ክብር ቆርጠን ልንሰዋ ምለን ተማምለን
ለማንነታችን
ደምና አጥንታችን እየተገበረ
በሲቃ ድምጻችን የነጻነት መዝሙር እየተዘመረ
የዛኔው ግባችን
ፍትህ እኩልነት እድገት ብልፅግናን ለማስፈን ነበረ ።
ሆኖም ምን ያደርጋል
ሙተን ተሟሙተን ከቅኝ ተገዢነት ነጻ ስንወጣ
የተዋደቅንለት ነጻነት መች መጣ?
ነፃ የወጣው ህዝብ
በነጻነት ማግስት
በነጻውጭወቹ ነጻነቱን አጣ
ለስልጣን ሲራኮት ሁሉም በበኩሉ
እናንተም ያለኛ ሰው የለም ስትሉ
ስትዋሹ ስትዘርፉ ስታስሩ ስትገድሉ
በግፍ አለቀና ዘመናችሁ ሁሉ
ግርማችሁ ተገፎ
ክብራችሁ ተራግፎ
ዛሬ በተራችሁ ታሰራችሁ አሉ? ??

የሆነው ሆኖ ግን
ወደታሰሩበት
ብመጣም ባልመጣም
ስኬት ጥፋትወን
ፅናት ውድቀትወን
አስቤ አብሰልስየ በመታሰርዎ አዝኛለሁ በጣም ።

LEAVE A REPLY