ኢትዮጵያ 27 የስደተኛ ካምፖችን ለመዝጋት መወሰኗን አስታወቀች

ኢትዮጵያ 27 የስደተኛ ካምፖችን ለመዝጋት መወሰኗን አስታወቀች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና፦ የኢትዮጵያ መንግስት 27 የስደተኛ መጠለያ ካምፖችን በአስር ዓመታት ጊዜ ውስጥ ለመዝጋት ማቀዱንና ስደተኞችንም ከማህበረሰቡ ጋር ተቀላቅለው እንዲኖሩ ለማድረግ እንደሚሰራ አስታወቀ።ከደቡብ ሱዳን፣ኤርትራ፣ሶማሊያና ከየመን የመጡ ከ900 ሺህ በላይ ስደተኛች በኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚኖሩ ተገልጿል።

ካምፑን በመዝጋት ስተደተኞቹን በግብርና፣በንግድና በሌሎች የስራ ዘርፎች ለማሰማራት ማቀዱን የኢትዮጵያ መንግስት ትናንት አስታውቋል።በጠመንጃ ሀይል እድሜውን እያራዘመ ያለው የኢትዮጵያ የአገዛዝ ቡድን በቅርቡ እንኳን ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ከሶማሌ ክልል የተፈናቁ እንዲሁም በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ከስደት የተመለሱ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ባሉበት ሀገር ይህን ማቀዱ ከምዕራባዊያን መንግስታት የፖለቲካ ድጋፍ ለማግኘት የታለመ ነው የሚል ትችትም እየቀረበበት ይገኛል።

ከዚህ በፊትም በስደተኞችና በጸረ-ሽብር ዘመቻ ሰበብ ከምዕራባዊያን መንግስታት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ድጋፍ ሲያገኝ መቆየቱ የሚታወቅ ነው።

LEAVE A REPLY