የከተራ በዓል እየተከበረ ነው

የከተራ በዓል እየተከበረ ነው

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ በኢትዮጵያ ከ1500 ዓመታት በላይ እየተከበረ የሚገኘው የጥምቀት በዓል፤በዋዜማው የሚከበረው የከተራ ስነ-ስርዓት በዕምነቱ ተከታዮች ዘንድ በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተከበረ ነው።

0DBB39AE-4E7E-472A-A63E-358BF8424BD2

የትምቀት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ቀኖና መሰረት ከዘጠኙ አብይ በዓላት አንዱ ሲሆን በዓሉ የሚከበረውም ኢየሱስ ክርስቶስ በእርሱ ጥምቀት የሰውን ልጅ ለማዳን በፈለገ ዮርዳኖስ በመጥምቁ ዮሐንስ መጠመቁን ለማስታወስ መሆኑን የሀይማኖት አባቶች ያስተምራሉ። የጥምቀት በዓል በዋዜማው ታቦታቱ ከቤተ- መቅደስ በመውጣት በወንዝ ዳር በድንኳን ወይም ዳስ ውስጥ ያድራሉ።ይህም ዮሐንስ ለማጥመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመሔዱ ምሳሌ ነው።

88B49D22-859D-4C4C-8435-0A39460AA32A

በኢትዮጵያ በመላ ሀገሪቱ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በደመቀ ሁኔታ የሚከበር ሲሆን በጎንደር የሚከበረው ጥምቀት ግን ከሌሎች አካባቢዎች በተለየ የደመቀና የውጭ ሀገራት ዜጎች ጭምር የሚሳተፉበት ነው።ጥምቀትን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት(ዩኔስኮ) ለማስመዝገብ ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታውቋል።

LEAVE A REPLY