የማለዳ ወግ…ከወልድያ ሐዘን እስከ ባህር ዳር የፍቅር ጉዞ

የማለዳ ወግ…ከወልድያ ሐዘን እስከ ባህር ዳር የፍቅር ጉዞ

* በወልድያ አዝነን፣ በባህርዳር ስጋታችን ተከልቷል !
* “ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር ጉዞ ” በሰላም ተጠናቋል…

በወልድያ የቃና ዘገሊላ ጥምቀት በዓል አከባበር ላይ በወጣቶችና በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች መካከል በተነሳ አንባጓሮ የንጹሃን ዜጎች ነፍስ ተነጥቋል ፣ ሰው ተጎድቷል ፣ ንብረትም ወድሟል: ( የወልድያው አንባጓሮው መነሻ እንደ ተለመደው ለግድያ በሚያበቃ ምክንያት አለመሆኑን ሰምተናል። መረጃውን የሰማነው ከክልሉ ኃላፊዎች ከተሰጡ መግለጫዎች ነው ። በወልድያ የተመለከትነው ግጭት እንደ ከዚህ ቀደም ግጭቶች መሰረታዊ ምክንያቱ የበሳልና አስተዋይ ህዝባዊ አመራር አለመኖር መሆኑን መረዳት ይቻላል ። ይህ መረዳት በራሱ ያሳዝናል 🙁 ከግጭቱ በኋላ ከወልድያ የሚደርሱን መረጃዎች ደስ አይሉም። በወጣቶች ላይ የደረሰው ጉዳት ሰቅጣጭነት ደግሞ ሰላም ይነሳል ፣ ያማል 🙁 ከምንም ጊዜ በላይ ግጭቱ መስመር እንደይስት አሁንም በቦታው የጦር ኃይል ሳይሆን በሳል ከህዝብ ወገናዊነት ያከው አመራር ያስፈልግ ይመስለኛል !

ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን – ቴዲ አፍሮ ልዩነታችን በማጥበብ ስለፍቅርና ስለ ኢትዮጵያዊነት ሊዘምር ደስ ብሎን በተስፋ ስንጠባበቅ የወልድያው ፍጅት ልባችን አደማው … 🙁 … ከዘባተሎው ፖለቲካ ትርፍ ፣ ከጊዜና ከወቅት አልማር ብለን ባጅተናልና መከራው ተከትሎን አብሮን ይጓዛል …ይህም ደስታውን ሳንጠግብ መከራ ተሸካሚ አድርጎናል … ያሳዝናል 🙁

ከመቸው ጊዜ በላይ ወንድም በወንድሙ ላይ ጨክኖ በወልድያ እየሆነ ባለው እያዘንን በባህርዳሩ ሰግተን ውለን አድረን ካመሸን በኋላ ሰናዩን መረጃ ሰምተናል … የድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን “ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር ጉዞ ” ልዩ ሀገራዊ አንድምታ ያለው የሙዚቃ ዝግጅት በሰላም ተጠናቋል ! ተመስገን !

ፈጣሪ ለተጎዱት ምህረት ይላክ ፣ የሞቱትን ነፍስ ይማር 🙁

የተጎጅ ቤተሰቦችን ጽናት ይስጣቸሁ !

ነቢዩ ሲራክ
ጥር 13 ቀን 2010 ዓም

LEAVE A REPLY