/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ የሚኒሶታ ቅዱስ ጳውሎስ ቤተ መጻሕፍት የህፃናት መጽሐፍን ወደ ኢትዮጵያ ቋንቋዎች ተረጎመ
በአሜሪካን ሀገር ሚኒሶታ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በርካታ በመሆናቸው የቅዱስ ጳውሎስ ቤተ መጽሐፍት የህፃናት መጽሐፍትን ወደ አማርኛና ኦሮምኛ ቋንቋዎዎች ተርጉሟል።
ሁለቱ ቋንቋዎች በሚኒሶታ በርካታ ተናጋሪ እንዳላቸውም የቤተ መጽሐፉቱ አስተዳድር ገልጿል። በቅዱስ ጳውሎስ ከተማ የሚኖሩ ስደተኛ ኢትዮጵያን እስከ 16000 የሚገመቱ ሲሆን ለልጆቻቸው ሊያነቧቸው የሚችሉ ተጨማሪ መጻሕፍት እንደሚያስፈልጓቸው ገልፀዋል።
መጽሐፍቱ ወደ ኢትዮጵያን ቋንቋዎች መተርጎም ህፃናት የሀገራቸውን ቋንቋ ለመማር በእጅጉ እንደሚረዳቸውም ይታመናል።