/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፦ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ለ2345 እስረኞችን በምህረት መፍታታቸውን የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ።
በይቅርታ ከተፈቱት መካከልም 1568 እስረኞች ፍርደኛ የነበሩ ሲሆን ቀሪዎቹ 557 ደግሞ ምርመራ እየተደረገባቸው የነበሩ እንዲሁም 250ዎቹ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት በመታየት ላይ የነበሩ እንደሆኑ ቢሮ ጨምሮ አስታውቋል። እስረኞቹም በህዝባዊ ተቃውሞው ወቅት የታሰሩ መሆናቸውን የክልሉ ፍትህ ቢሮ ገልጿል። ይቅርታ የተደረገላቸው እስረኞች የተሃድሶ ስልጠና ከወሰዱ በኋላ እንደሚለቀቁም የፍትህ ቢሮው አስታውቋል።
አቶ ለማ መገርሳ ከዚህ በፊትም የኢትዮጵያን አዲስ ዓመትና የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ እስረኞችን መፍታታቸው የሚታወቅ ነው።