/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በፍርደ ገምድልነቱ በሚታወቀው ፍርድ ቤት የተጣለበትን የ 3 ዓመት ከ 6ወር የእስር ውሳኔ ጨርሶ ለመውጣት ሁለት ወራት የቀረው የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዮናታን ተስፋዩ በድንገት ተለቀቀ፡፡
በፌስ ቡክ ገጹ ባወጣው ጽሁፍ ምክንያት የታሰረው ዮናታን በፍርድ ቤት ክርክር ‘ምንም አይነት ጥፋት የለብኝም፤ የጻፍኩትም ያመንኩበትን ነው ከዚህ ብወጣም እደግመዋለሁ፡፡ ህዝብ ዝም ብሎ ማለቅ የለበትም’ በማለት ሲሟገት እንደነበር ይታወቃል፡፡
በይግባኝ ሰሚ ችሎት ከ6 አመት ፍርድ ወደ 3 አመት ክ6 ወር የተሻሻለለት ሲሆን ዛሬ ሲለቅቅ የፍርድ ውሳኔውን ሊጨርስ ከሁሉት ወር በታች ጊዜ ቀርቶት ነበር፡፡
ዛሬ ከዝዋይ እስር ቤት ሲወጣ መንገዶች ተዘጋግተውና ህዝባዊ አመጹ ተፋፍሞ ስለነበር ከቤተሰቡ ጋር ለመገናኘት ተቸግሮ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡
ፈርሞ እንዲወጣ ተጠይቆ ‘ያጠፋሁት ጥፋት ስለሌለ ይቅርታ አልጠይቅም በማለቱ እስካሁን እንደቆየና በመጨረሻም በድንገት ተጠርቶ ከእስር እንዲወጣ መደረጉ ታውቋል፡፡