ከሞያሌ ከተማ የተፈናቀሉ ዜጎች ከ50 ሺህ መብለጡ ተገለጸ

ከሞያሌ ከተማ የተፈናቀሉ ዜጎች ከ50 ሺህ መብለጡ ተገለጸ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ ባለፈው ቅዳሜ የወያኔ መከላከያ ሰራዊት አባላት የጅምላ ጭፍጨፋ ካካሄዱ ወዲህ የከተማዋ ነዋሪዎች ህይወታቸውን ለማትረፍ ወደ ጎረቤት ኬንያ የሚሰደዱ ዜጎች ቁጥር እየላቀ መምጣቱ ተገለጸ።

ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ ከ50 ሺህ የሚልቁ ዜጎች ወደ ኬንያ መሰደዳቸውን የአካባቢው ምንጮች አስታውቀዋል።

ወደ ኬንያ ከተሻገሩት ስደተኞች መካከልም ሴቶችና ህፃናት እንደሚበዙበት የተገለጸ ሲሆን በአራት ትምህርት ቤቶችና ፖሊስ ጣቢያዎች ተጠልለው እንደሚገኙ ታውቋል።

የኬንያ ቀይ መስቀል ማህበርና ስደተኞቹ የሰፈሩበት የማርሳቤት ግዛት አስተዳድር የተለያዩ የምግብ አቅርቦትና የህክምና አገልግሎት እየሰጧቸው እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።

ገዳዮቹ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ዛሬም በሞያሌ ከተማ ቤት ለቤት እየተዘዋወሩ ሽፍቶች (የኦነግ አባላት) የት እንደሚደበቁ ተናገሩ እያሉ በነዋሪዎች ላይ የማዋከብ ተግባር ላይ ተጠምደው እንደዋሉ ተገልጿል።

የኢትዮጵያን ህዝብ እየጨረሰ ያለው ወታደራዊ አገዛዝ (ኮማንድ ፖስት) ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ በሞያሌ ከተማ ከ13 ሰዎች በላይ የሞቱበትና ከ20 በላይ ሰዎች የቆሰሉበትን የጅምላ ጭፍጨፋ በስህተት የተፈጸመ በመሆኑ “ይቅርታ” እንጠይቃለን ማለቱ ይታወሳል።

LEAVE A REPLY