/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ኦሮምኛ ቋንቋን ለማስተማር ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ፡፡ የዩኒቨርሲቲው የሂዩማንቲ ፋኩልቲ ዲን ዶክተር ዳዊት አሞኘ እንደተናገሩት የግዕዝ ቋንቋን ከጥንታዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ ጋር በማቀናጀት ማስተማር ለመጀመር ምዝገባ ላይ ይገኛል፡፡ ከግዕዝ በተጨማሪ የኦሮምኛ ቋንቋን ለማስተማር የስርዓተ ትምህርት ቀረፃና ሌሎች ጥናቶች እየተሰሩ ነው ብለዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት 16 ምሁራንና የፖለቲካ ሰዎች የተካተቱበት አጭር ጥናትና ደብዳቤ በመፃፉ ኦሮምኛን በአማራው ክልል በግእዝ ፊደል ስለማስተማር የሚጠይቅ፤ ለአማራ ክልል ር/መስተዳድር ገዱ አዳርጋቸው ማቅረባቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
እንደ ምሁራኑ ገለፃ ኦሮምኛ ቋንቋን ከላቲን ፊደል ይልቅ በግእዝ ማስተማሩ የኢኮኖሚ፣ታሪክ፣ሀገራዊ ስነ-ልቦና፣የሳይንስና ሌሎች በርካታ ጥቅሞች እንዳሉት ገልጸዋል።
ኦሮምኛ ቋንቋን በኢትዮጵያው ግእዝ ፊደል በቀላሉ ኮምፒተር ላይም ያለ ምንም ችግር መክተብ እንደሚቻልም አብራርተዋል።ለዚህም ዋናው ነገር ቀና ልቦናና በራስ ፊደል ኩራትና ፍላጎት ማሳየት እንደሆነም በደብዳቤያቸው ላይ ማተታቸው ይታወሳል።