በማዕከላዊ ድብደባ ብልቱ የተኮላሸበት አስቻለው ደሴ አሁንም ስቃይ ላይ ነው

በማዕከላዊ ድብደባ ብልቱ የተኮላሸበት አስቻለው ደሴ አሁንም ስቃይ ላይ ነው

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በመጥፎነቱ የሚታወቀው ማዕከላዊ እስር ቤት ውስጥ በወያኔ ጨካኝ መርማሪዎች ድብደባ ምክንያት ብልቱ የተኮላሸበት ወጣት ህክምና ለማግኘት አለመቻሉና በቀጠሮ ፍርድ ቤት በመመላለስ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ።

ጦማሪት ማህሌት ፋንታሁን የዛሬውን የዳኞች ውሳኔና የፍርድ ቤት ውሎ አስመልክታ እንደጻፈችው ፡ –

አስቻለው ደሴ በሽብር ክስ ቀርቦበት ክሱን ቂሊንጦ ሆኖ እየተከታተለ የሚገኝ ወጣት ነው። ማእከላዊ በምርመራ ወቅት በድብደባ ብልቱ የተኮላሸበት መሆኑን ከዚህ በፊት በፍርድ ቤት ልብሱን አውልቆ አሳይቷል። አስቸኳይ ህክምና እንደሚያስፈልገው እና የዘር ፍሬው ካልወጣ ወደ ካንሰር እንደሚቀየርበት ጳውሎስ ሆስፒታል ባለ ሃኪም ተነግሮት ለየካቲት 27/2010 እንዲቀርብ ቀጠሮ ተሰጥቶት ነበር።

የቂሊንጦ ሃላፊዎች ግን የቀጠሮውን ቀን አሳልፈው የቀጠረው ሃኪም በሌለበት/በማይገኝበት የካቲት 29/2010 ቀን ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል ወስደውት ለግንቦት 17/2010 ተለወጭ ቀጠሮ እንደተሰጠው ነግረውታል።

ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቦ የህመሙ ሁኔታ አስቸኳይ እና ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ የቂሊንጦ ሃላፊዎች ሆስፒታል በአስቸኳይ እንዲወስዱት እንዲፈቀድለት ጥያቄ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም ዳኞቹ ሆስፒታል በሰጠው ቀጠሮ ማዘዝ እንደማይችሉ ነግረውታል። ቂሊንጦም የሚገኘው ጨለማ ቤት እንደሆነ አቤቱታ አቅርቦ ነበር። ጉዳዩን የሚከታተለው 4ኛ ችሎት በአቤቱታው ላይ ትእዛዝ ለመስጠት ለመጪው አርብ የካቲት 7/2010 ቀጠሮ ሰጥቶታል።

LEAVE A REPLY