የማእከላዊ መርማሪዎች መምህር ስዩም ተሾመን ፍርድ ቤት አላቀረቡትም

የማእከላዊ መርማሪዎች መምህር ስዩም ተሾመን ፍርድ ቤት አላቀረቡትም

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የአምቦ ዩንቨርስቲ መምህርና ጦማሪ ስዩም ተሾመ በአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዛሬ ቀጠሮ የነበረውም ቢሆንም የማዕከላዊ ገራፊዎች እንዳላቀረቡት ታውቋል።

የስዩም ጠበቃ ለፍርድ ቤቱ ባሰሙት አቤቱታ ማዕካላዊ ደበኛቸውን ለምን እንዳልቀረበው ማብራሪያ እንዲሰጥና ፍርድ ቤት እንዲያቀርበው ትዕዛዝ እንዲሰጥለት ጠይቀዋል።

ፍርድ ቤቱም የማዕከላዊ ማሰቃያ ቤት ለመጋቢት 17/2010ዓ.ም እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ማስተላለፉ ተገልጿል።

በሌላ በኩል የስዩም ተሾመ ቤተሰቦች ለአዲስ ስታንዳርድ በሰጡት መረጃ “ስዩም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ (ኮማንድ ፖስት) ስለታሰረ ማዕከላዊ ፍርድ ቤት ማቅረብ እንደማይችል” እንደገለጸላቸው አስረድተዋል። ማዕከላዊ ይህን ይበል እንጂ ስዩም ወሊሶ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በተያዘ በሦስተኛ ቀኑ በአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀርቦ የ14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ እንደተጠየቀበት የሚታወስ ነው።

LEAVE A REPLY