በቂሊንጦ እስር ቤት ቃጠሎ ምክንያት እነ አብስራ ብርሃኑ ህይወታቸው አደጋ ላይ መሆኑን ዛሬ ፍርድ ቤት በቀረቡበት ወቅት ገለጹ
በዛሬው የፍርድ ቤት ውሎን ወጣት ቲዎድሮስ አስፋው የሚከተለውን አቅርቦታል ፡ –
————–
➣ በገዳይ እጅ ላይ ነው ያለነው።
➢ ገዳይ ማ/ቤቱ ነው በማለታችን ችሎት ደፍራችኋል ተብለን አንድ አመት ተፈርዶብናል።
➣ ፍራሽ ላይ አይደለም እየተኛን ያለነው የጓደኞቻችን እሬሳ ላይ ነው።
ነሐሴ 28/2008 ዓ.ም የቂሊንጦ የቀጠሮ ማረፌያ ቤት ላይ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ ላይ ተጠርጥረው የተከሱት እነ የአብስራ ብርሀኑ ዛሬ ልደታ ምድብ 2ኛ ወ/ችሎት የቀረቡ ሲሆን መዝገቡ የተቀጠረው ተከሳሾች በማ/ቤት የደረሰባቸውን የሰብአዊ-መብት ጥሰት ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ያጣራውን ሬፖርት እንዲያቀርብ፣ በተለያየ መዝገብ ተከሰው የሚገኘውን ክሳቸውን ተጣምሮ እንዲታይላቸው እንዲሁም ከሳሽ ዐ/ህግ ክስ እንዲያሻሽል ፍ/ቤቱ ባዘዘው መሰረት ክሱን አሻሽሎ እንዲያቀርብ ሲሆን ከሳሽ ዐ/ህግ ክሱን አሻሽሎ ቢያቀርብም ተከሳሾች ሌሎች ያቀረቡባቸውን አቤቱታዎች ላይ ዳኞች ጉዳዩን እኛ አይተነው ስለማናውቅ ሌላ ቀጠሮ እንሰጣለን ሲሉ 2ኛ ተከሳሽ ቴዎድሮስ ዳንኤል ከመቀመጫው በመነሳት አቤቱታ እንዳለው ገልዖ እረ እበካቹ ተረዱን ባለፋው ገዳይ ማ/ቤቱ ነው ብለን እውነቱን በመናገራችን ችሎት ደፍራችኋል ተብለን አንድ አመት ተፈረደብን አሁን ደግሞ ፍ/ቤቱ አንዴ 10ኛ ወ/ችሎት ሌላ ግዜ ደግሞ 3ኛ ወ/ችሎት ዛሬ ደግሞ እዚህ 2ኛ ወ/ችሎት እያመላለሰን ነው ጉዳያችን በቋሚ ችሎት እየታየ አይደለም ያለንበትን ተረዱ ፍራሽ ላይ አይደለም ተኝተን ያለነው በጥይት ተደብድበው አና ተቃጥለው የሞቱ የጓደኞቻችን አስከሬን መቃብር ላይ ነው ካለ በኋላ ያለንበትን ችግር ልትረዱ ይገባል ብሏል።ሌላኛው 6ኛ ተከሳሽ ዳዊት በላይነህ በበኩሉ በገዳይ እጅ ነው ያለነው ፣የሰው አጥያት ነው ተሽክመን የምንገኘው ገዳይ ወያኔ ነው እነሱ በገደሉት ተሰቅዬ ተገርፌአለሁ ብሎ ልብሱን አውልቆ ለችሎቱ ካሳየ በኋላ እናንተም በቴሌቭዢን ብቻ አይደለም ፍትህ እንሰጣለን ብላችሁ መናገር ያለባችሁ በተግባርም መሆን አለበት ካለ በኋላ በአስቸኳይ ፍትህ እንዲሰጣቸው ጠይቋል።
ፍርድ ቤቱም የተከሳሾቹን አቤቱታ ካዳመጠ በኋላ በቋሚነት ጉዳያችሁ እዚህ ችሎት ይታይ አይታይ በሚለው ላይ መጀመሬያ ብይን መሰጠት ስላለበን ብይን እንስጥበት ብለው ለመጋቢት 26/2010 ዓ.ም ቀጠሮ ከሰጡ በኋላ ሌሎች አቤቱታዎችን በተመለከተ ከብይኑ በኃላ አንደሚመለከቱ ከገለፁ በኋላ የእለቱን ችሎት ዘግተዋል።
ተከሳሾች ዱ.ነ.ግ (ዱርዬ ነፃነት ግንባር) የሚል ቡድን አቋቁማችሁ ከመቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ጋር በመተባበር ማ/ቤት አቃጥላችኋል፣ እስረኛ ልታስመልጡ ነበር ተብለው በሸዋሮቢት ግዜዊ ምርመራ ጣቢያ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እንደተፈፀመባቸው ይታወቃል።