የታሰሩት ህጋዊ የአማራ ፓርቲ መሥራቾች ምሁራን፣ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች የመብት ጥሰት ቀጥሏል

የታሰሩት ህጋዊ የአማራ ፓርቲ መሥራቾች ምሁራን፣ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች የመብት ጥሰት ቀጥሏል

/የሺሀሳብ አበራ/

ህጋዊ የአማራ ፓርቲ ለመመስረት የዛሬ ሳምንት ባህር ዳር ላይ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ስለታሰሩት ምሁራን፣ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ስለደረሰባቸው የመብት ጥሰትና ስለ ግለ ታሪካቸው ጋዜጠኛ የሺሀሳብ አበራ የሚከተለውን አካፍሎናል።

__________

19ኙ በቅዳሜ!!!

በቅዳሜዋ ጀምበር በቀን 13 ፣ የኛ ሰዎች የጣና ገዳማትን ለመጎብኘት ቀጠሮአቸውን አደረጉ፡፡በቀጠሮአቸው ተገናኝተው ደብረማርያምን

እና ዳጋ እስጢፋኖስ ገዳምን ጎበኙ፡፡ በጉብኝታቸው ስለ አማራነታችን ፣ ስለ ሀገራቸው አወጉ፡፡ አማራው ብሄራዊ ፓርቲ እንደ ሚያስፈልገው ከአንዳንዶች በነገር ነገር ተነሳ፡፡ከምርጫ ቦርድ አማክረንም አስፈቅደንም ለመመስረት ሂደት ላይ ነን …አሉ አንዳንዶቹ፡፡ ብዙዎች የአማራ ብሄራዊ ፓርቲ እንደሚያስፈልገው አመኑ፡፡ ሀሳብ ተለዋወጡ፡፡ ስለ ጣና እንቦጭ አረምም መላ ዘየዱ፡፡

ብዙዎች የጣና እንቦጭ አረም ማስወገድ ንቅናቄ አባላት ናቸውና፡፡ የጀልባ ካፒቴኑን እና ጋዜጠኛ ንጋቱ አስረስን ጨምሮ 19 ብሩሃን በጉዞው ነበሩ፡፡ ጋዜጠኛ ንጋቱ በአጋጣሚ ረዳት ፕሮፊሰር ተመስገን ተሰማ በግል ጉዳይ ለማግኘት ሲሄድ ነበር ከ 18 ሊሂቃን ጋር የተቀላቀለው፡፡ ስለምን እንደሚወራ እንኳን እንደመንገደኛ ደራሽ ነበር፡፡ካፒቴኑም ስራው መቅዘፍ ነው፡፡

በዚህ መሃል ያንም ይህንንም እያወሩ ገዳማትን ሲጎበኙ ጀምበር ተሸነፈች፡፡ ከደብረማርያም ጣይቱ መናፈሻ ሲወርዱ ምሽት 1:30 ሆነ፡፡ ገበታ ላይ ተያዙ፡፡ ወዲያው የተሸፈኑ ሰዎች ደርሰው በየአሉበት እንዲቆሙ ቃታ ሳቡ፡፡ ከገዳም የቆዮ ሰላማውያን ናቸው ና ቆሙ፡፡ ሲቆሙ አይናቸውን አሰሯቸው ና በመኪና ጫኗቸው፡፡ ጭነው አባይ ማዶ ወደ ሚገኝ ቀፋፊ መጋዘን አጉረው አቁመው

አሳደሯቸው፡፡… ከዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ቀጥሎ በአዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ ገናና የፍልስፍና መምህር የሆነው ረዳት ፕሮፊሰር በለጠ ሞላ ጌታሁን “ምን አድርገን ነው?” የሚል ጥያቄ ከታጎሩበት ሆኖ ለአጓሪዎች አነሳ፡፡ እውቀት ያዘለ ጭንቅላቱን በሰደፍ መቱት፡፡

ቅዳሜ ማታ የተመታው እሁድ ስድስት ሰዓት ባህርዳር ዘጠነኛ ፖሊስ ጣቢያ ስሄድ ከጭንቅላቱ መጠነኛ ደም ሲፈሰው በአይኔ በብረቱ ተመልክቻለሁ፡፡ (ሀገራችን የደህና ምሁራን ደም እንጂ እውቀት መሬት እንደማታስነካ ፕሮፊሰር በለጠ አሳምሮ ያውቀዋል፡

በለጠ ከ 6 ወር በኃላ የዶክትሬት ዲግሪውን ይይዛል፡፡ ተወልዶ ያደገው ራያ ነው፡፡) ዶክተር ደሳለኝም መጀመሪያ ድብደባ ደርሶበታል፡፡( ከዚህ ቀደም በነበረው ኮማንድ ፖስት የአማራ ዶክተሮች ማህበር ፕሬዜዳንት ዶክተር ጋሹ ክንዱ ታስሮ ተሰቃይቷል፡፡ ለስደትም ተዳርጓል ፡፡

በዕለተ እሁድ ጓደኛየን ጋዜጠኛ ንጋቱን ፍለጋ ስንከራተት ቀድሜ ወንድሞቸ የታጎሩበትን ያወቅሁ እኔ ነበርኩና እነዚህ ወጣት ብርሃኖች ከገዳም መልስ ተይዘው እንደተሰቃዮ የፊታቸው መጠየም በወቅቱ ይመሰክር ነበር፡፡ ከወደ ኃላግን ፊታቸው እየፈካ መጥቷል፡

ወገን ህመማቸውን ወዲያው ተጋርቷልና፡፡( የጋዜጠኛ ንጋቱ የበኩር ልጅ የምኒሊክ ንጋቱ ሁለተኛ ዓመት ልደት ትነናንት አባቱ በሌለበት ተከብሯል፡፡ በእስር ቤትም አማራ ነን የሚለውን የረዳት ፕሮፊሰር ተመስገንን መዝሙር በማዜም ተከብሯል፡፡ መልካም ልደት!!!)

የወይዘሮ ስህኑ የህግ ስፔሻሊስቱ ዮሱፍ ኢብራሄምንም በዕለተ እሁድ ታስሮ ከቀድሞው ተማሪው ከጠበቃ መልካሙ ተሾመ ጋር

አገኘነው፡፡ ጠበቃ መልካሙ ተሾመ በመምህር ዮሱፍ 40 ደቂቃ መማር 40 መፅሃፍትን ከማንበብ ጋር ይተካከላል ብሎኛል፡፡

ዮሱፍ በህገመንግስታዊ ህግ ማስትሬቱን ሲሰራ ጥናቱ በኢትዮጵያ ፊዴራሊዝም አወቃቀር ላይ ነበር፡፡ ጥናቱ በአማዞን የኢንተርኔት ገበያ ከፍተኛ ገቢ አስገኝ ጥናት ሆኗል፡፡የወሎ ዮኒቨርስቲው የህግ ምሁር የሱፍ አማራው በፊዴራሊዝም ስራዓቱ ተጠቃሚ አለመሆኑ ወላሂን ብሎ እንደሚያብከነክነው ነግሮኛል፡፡ እኔም ያነሳልኝ ጉዳዮች መዝኘ ማርያምን እውነትህን ነው አልኩት፡፡ ለየሱፊ አላህ ለአማራው የሚፈልገውን ነፃነት ይስጥልን ብየ በውስጤ መረቅሁ፡፡ የሱፊን ማሰር እውቀትን ማሰር ነው፡፡የሱፌ ሀይማኖቱን አክባሪ ባለምጡቅ ልዕለ አዕምሮ ያለው ምሁራችን ነው፡፡ ነገም ዛሬም ከነዮሱፌ ጎን ነን፡፡ በነገራችን ላይ እነ የሱፊ እንዲፈቱ መጠየቅ ተፈጥሮአዊ መብት ነው፡፡ ምክንያቱም እነ የሱፊ እኛን ናቸው፡፡የኛን ሀሳብ ተሸካሚዎች ናቸው፡፡ ማወቅን በተግባር ለመግለጥ የሚሯሯጡ

የአማራው ፋኖሶች ናቸው፡፡ ፋኖሶች የጋራ መብራቶች ናቸው፡፡ የጋራ መብራቶችን በጋን ውስጥ አስቀምጦ ለመቅጣት መሞከር የማህበረሰብን ጥቅም መጋፋት ነው፡፡

ማን እንደያዛቸው? ለምን እንደተያዙ እንኳን ሳይታወቅ መምህራን ከትምህርት ቤት፣ ሀኪሞችን ከሆስፒታል ፣ ጋዜጠኞችን

ከዘገባ ማስተጓጎል ለድህነት እና ለኃላ ቀርነት ዘብ እንደመቆም ይታሰባል፡፡

ኮማንድ ፓስትም ሆነ ሌላ ህግ ለሰው ክብር እና ልዕልና ካልቆመ ሰባዊ ህግ አይደለም ማለት ነው፡፡ ደህንነቱ እና ወታደሩ ለሀገሩ እና ለወገኑ እንጂ ለፓርቲ ብቻ ጠባቂ መሆን የለበትም ፡፡ ህዝብ እንጂ ፓርቲ ነገ አይኖርም፡፡ ክብር ለህዝብ!!! የታሰሩት ስብሰባ እንኳን ተሰብስበው አይደለም፡፡ አሲረው አይደለም፡፡ ወደ ገዳም እየሄዱ እንጂ ወደ ጫካ እየሄዱም አልነበረም፡፡ ብዕር እና ሀሳብ እንጂ ነፍጥም አላነገቡም፡፡

የሰላም ተምሳሌቶቻችን ናቸው፡፡

እስከዛሬ ሁኔታው ባለበት ቀጥሏል፡፡አዲስ ነገር የለም፡፡ 19 ኙን እሰረኞች ለመጠየቅ ረጃጅም ሰልፎች ዛሬም ቀጥለዋል፡፡ መጠየቅም ይቻላል፡፡

LEAVE A REPLY