/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በባህር ዳር ከተማ ከአስር ቀናት በላይ ታስረው የነበሩት 19ኙ ሰዎች ተፈቱ። ህጋዊ የአማራ ፓርቲ ለማቋቋም በእንቅስቃሴ ላይ በነበሩበት ወቅት የታሰሩት የዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች ዛሬ ጠዋት መፈታታቸው ታውቋል።
ከተፈቱት ሰዎች መካከልም
1, ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ (የባህር ዳር ዩንቨርሲቲ መምህርና የጣና ደህንነትና የአካባቢ ጥበቃ ማህበር ፕሬዚደንት)
2, አቶ ጋሻው መርሻ (የሰማያዊ ፓርቲ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የነበረና የ“አንፀባራቂው ኮከብ” መፅሃፍ ፀኃፊ)
3, የሱፍ ኢብራሂም (ወሎ ዩኒቨርሲቲ መምህር የነበረና ጠበቃ)
4, ተመስገን ተሰማ (ወሎ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህር)
5, በለጠ ሞላ (አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር)
6, ንጋቱ አስረስ (የአማራ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ)
7, በለጠ ካሳ (የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረ)
8, አቶ ሲሳይ አልታሰብ
9, አቶ ዳንኤል አበባው
10, አቶ መንግስቴ ተገኔ
11, አቶ ቦጋለ አራጌ
12, አቶ ካሱ ኃይሉ (የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ መምህር)
13, አቶ ተሰማ ካሳሁን
14, አቶ ድርሳን ብርሃኔ
15, አቶ በሪሁን አሰፋ
16, አቶ ፍቅሩ ካሳው
17, አዲሱ መለሰ (ደ/ታቦር ዩኒቨርሲቲ መምህር)
18, አቶ ተመስገን ብርሃኑ ሲሆኑ ስሙ ያልተጠቀሰው 19ኛው ሰውም አብሮ መፈታቱ ከታሳሪዎች ቤተሰብ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

























