በወልዲያ እግር ኳስ ቡድን ላይ ከፍተኛ ቅጣት ተጣለበት

በወልዲያ እግር ኳስ ቡድን ላይ ከፍተኛ ቅጣት ተጣለበት

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በወልዲያ እግር ኳስ ቡድን ላይ ከፍተኛ ቅጣት ጣለበት። ፌዴሬሽኑ ሚያዚያ 3/2010ዓ.ም ወልዲያ ከፋሲል ከተማ 19ኛ የሊጉን ጨዋታ በመሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ስታድየም ሲያካሂድ በመጨረሻ ሰዓት ላይ የወልዲያ ደጋፊዎች ወደ ሜዳ በመግባት የዕለቱን ዳኞች በመደብደብ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል በሚል ከባድ ቅጣት ዛሬ አስተላልፏል።

6EB407C4-5E53-41DE-8032-4C6AE9BC4174

ፌዴሬሽኑ በወልዲያ እግር ኳስ ቡድን ላይ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፏል(ለዝርዝሩ መግለጫው ተያይዟል) ።

1. ለፋሲል ከተማ ፎርፌ እንዲሰጥ (3 ነጥብ + 3ጎል)

2. በመሐመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ስታድየም ለአንድ አመት ጨዋታ እንዳይካሄድ

3. ቀሪ የሜዳው ጨዋታዎችን ከወልዲያ በ500 ኪሜ ርቀት እንዲያደርግ

4. 250 ሺህ ብር ቅጣት

5. የዳኞች ህክምና ወጪ እንዲሸፍን

7. አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ (አንድ አመት እገዳ + 10,000 ብር)

8. ብሩክ ቃልቦሬ (አንድ አመት እገዳ + 10,000 ብር)

D01F8CFC-0EB9-4B85-80C8-F804C5BDDE1B

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የወልዲያ እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ጥፋተኛ በማለት የቅጣት ውሳኔ ቢያሳልፍም፣ በወቅቱ የደጋፊዎች ማህበር አባላት ወደ ሜዳ የገቡት ደጋፊዎች በቁጥር አነስተኛና የማያውቋቸው መሆናቸውን በተናጠል መግለፃቸው ይታወሳል።

LEAVE A REPLY