አስራት አብርሃም፤ የባድሜው ጠበቃ ባቡር ቆሞ አይጠብቅምና ንቃ! /አቢቹ ነጋ/

አስራት አብርሃም፤ የባድሜው ጠበቃ ባቡር ቆሞ አይጠብቅምና ንቃ! /አቢቹ ነጋ/

አቶ አስራት አብርሃም ከኤርትራ ጋር ያለውን ችግር እንዴት መፍታት ይቻላል በሚል የሚአውቀውን ሃሳብ አጋርቶናል። ሃሳብ ማቅረቡ የሚደገፍ ሲሆን እንደ መፍትሔ ያቀረብው ግን በከሸፈ መንገድ ስህተትን በስህተት ለማረም መሞከሩ ነው። የሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ወጣት የዘመዶቹን የተሳሳተና የከሸፈ መንገደ እንደ መፍትሔ ሲአቀርብ መስማት ተስፋ ቢአስቆርጥም የባድሜ ችግር ሲፈጠር እና ሲጠነሰስ ወጣት የነበረ በመሆኑ ያሰበውን ቢአስብ ብዙ አይፈረድበትም።

የልማትና የህክምና ጠበብት ለችግር መፍትሔ ሲአስቡ በቅድሚያ ምክንያቱና ተጽዕኖውን መተንተን (Causality Analysis) ይወዳሉ። የነገሮች መንስዓኤ እና ምክንያት ከታውቀ ለኋላቀርነትም ይሁን ለበሽታ መፍትሔ መስጠት ይቻላል የሚል አመክንዮ ይሰጣሉ። የባድሜ ችግርና መፍተሄ የሚገኘው በሻቢያና በህውሃት እጅ እንጅ በኢትዮጵያዊያን መቃብር አየደለም። ሁለቱ ነፃ አውጪ ቡድኖች ሲጀመር ኢትዮጵያን የመበታተን አባዜ፤ ሕዝብዋን እርስ በርስ የማጫረስ ዓላማ አንግበው የተንቀሳቀሱ ለመሆኑ ማስረጃው ብእጅህ ስለሚገኝ ትንታኔ አይሻም።

የባድሜ ችግር ኤርትራን ከኢትዮጵያ ከመገንጠል ጋር ተያይዞ የመጣ ነው። በዚህ ፍች ምክንያት የይገባኛል ጥያቄ አብሮ ተከሰቷል። እውነቱ ይነገር ከተባለ በንጉሡ እና በደርግ ዘመነ መንግሥት ጥያቄውም ሆነ ሃሳቡ ተሰምቶ አይታወቅም ነበር። እርግጥ በዚያ ዘመን አልፎ አልፎ የድንበር ገፋሃኝ ውዝግብ በትግራይና በኤርትራ ክፍለ ሃገራት መካክል መኖሩ አይካድም። ከዚህ ባሻገር ለጠብ እና ለጦርነት የሚጋብዝ ጉዳይ ግን ተከስቶም፤ ተመዝግቦም አይታወቅም። ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ቆይታ ቢሆን ኖሮ ይህ የይገባኛል ጥያቄ ባልተነሳ፤ ይህ ሁሉ ደም መፋሰስ ባልተከሰተ ነበር። ባጭሩ በሃገር በታኞች የተከሰ የፖለቲካ ችግር ነው።

በታኞች ደግሞ የፖለቲካ ችግርን የሚፈቱት በሃይል፤ በግድያ፤ በእስር ነው። ይህን መንገድ እንደ መርህ እና አማራጭ አርገው ከመያዛቸው የተንሳ የ1998 ጦርነት ተከሰተ። ኤርትራና ኢትዮጵያ ትልቅ ጦርነት አደረጉ። አላስፈላጊ ደም መፋሰስ ሆነ። የአንድ ሃገር ሕዝቦች የነበሩ ተላለቁ። ወያኔም የራሱን ጎሳ ለመጠበቅ በያዘው ስልት አማራውን፤ ኦረሞውን፤ ደቡቡን ቤንሻንጉሉን፤ ሀረሬውን፤ ሶማሊውን፤ ጉራጌውን ወዘተ ከፊት አሰልፎ አስፈጀ። ለባድሜ ሲባል ከ70,000 ላይ ኢትዮጵያዊያን ሕይወታቸውን አጡ። ከ350,000 በላይ ቤተሰቦች ተበተኑ። ኑሮአቸው እንዳልሆነ ሆኖ ቀረ።

በደርግ ዘመነ መንግሥት የሶማሊን ወራሪ ሃይል ለማሸነፍ በተደረገው ጦርነት ይህን ያህል ሕዝብ ማለቁን አናውቅም። የትግሬው መንግሥት ብዙ ሕዝብ አስፈጅቶ ጦርነቱን በድል አድራጊነት ቢቋጭም የአስራት አለቃ፤ የጥፋት ተምሳሌቱ መለስ ዜናዊ ከተባበሩት መንግስታት ጋር ተደራድሮ ባድሜን ለኤርትራ ሰጠ። አሁን አስራት የመለስ ደቀመዝሙር እንደገና ባድሜን በተመለከተ ሃይል ተጠቅመን እንድናስመልስ ይመክራል። ይህ ብቻ አይደለም ለኢትዮ-ኤርትራ ችግር ዘላቂ መፍትሄ መስጠት ካስፈለገ ቆፍጠን ብሎ በኤርትራ ውስጥ የስርዓት ለውጥ እንዲመጣ መስራት ያስፈልጋል ይላል። ኢትዮጵያ አስመራ ያለውን ሕዝብ ያልመረጠውን የኢሳያስ መንግሥት ቀይሮ ለህውሃት አጋር የሆነ መንግሥት አቋቁሞ መውጣት ያስፈልጋል ይለናል። ለመሆኑ ኢትዮጵያ ያለውን መንግስት ሕዝብ የመረጠው ነው ያለ ማነው። የራሷ አሮባት የሰው ታንቃቃ አይሆንም። የኤርትራን መንግስት የመጣል ወይም የማስወግድ ሥራ የኤርትራዊያን እንጅ የሕወሃት ሊሆን አይችልም።

ለነገሩ አቶ አስራት እንደተቃዋሚ እስር ቤት ገብቶ ነበር አይደል። ምን ስቃይ ደረሰበት፤ ከወርቃማው በመሆኑ ዓማራው፣ ኦሮሞው፤ ደቡቡ፤ አኝዋኩ፤ ወዘተ ብልቱ ላይ ሃይላንድ ተንጠንጥሎብት ሲገረፍ፤ ሲኮላሽ፤ ሲገደል እርሱ ዝምብም አላረፈበት ይባላል። ባድሜን ለማስመለሰ በሃይል ወደ ኤርትራ እንዝመት ብሏል። ዘመቻው ሲታወጅ እርሱ ቤት ቁጭ ብሎ ቪዲዮ ሲጫወት ሌላው እስር ቤት ይሰቃያል፤ ይሞታል፤ ይረሸናል፤ በጦር አውድማ ውስጥ ያልቃል።

አንዴ ስታሞኙን ዝም አልን፤ ሁለተኛ ስታሞኙን ታገስን፤ ሶስተኛ ልታሞኙን ስትሞክሩ ዝም አንልም፤ አንፈቅድላችሁም። በመጀመሪያ ኤርትራን በማስገንጠል አሞኛችሁን፤ ሁለተኛ ባድሜን ለማስመለስ በሚል ታገስን አሁን የኤርትራን መንግስት እንቀይር፤ ባድሜን እናስመልስ ብላችሁ እንድታሞኙን አንፈቅድም። ወርቃማው (እንኳን ካብናሁም ሕዝቢ ወርቂ ተወሊዳን) ይሂድና ባድሜን ያስመልስ፤ ኢሳያስን ገሎ መንግስት ይቀይር። ያኔ ጀግንነት ይዘመር። በንፁሕ ኢትዮጵያዊያን ደም ግን የባድሜ ስርየት አይኖርም።

በተለይ አዲሱ ጠቅላይ ምኒስትር ዶ/ር ዓቢይ ኢትዮጵያን መልሶ አንድ የማድረግ ዘመቻ፤ የፍቅርና የመተሳሰብ ዘምባባ እያውለበለበ፤ የጎበጠውን ለማቃናት፤ የተበደለውን ለመካስ፤ የተፈናቀለውን መልሶ ለማቋቋም፤ የተሰደደውን በይቅር ለእግዚአብሔር ለመመለስ፤ እውነተኛ ዴሞክራሲና ሁሉን አቀፍ ስርዓት ለመመስረት ዘመቻና እንቅስቃሴ በጀመረበት ታሪካዊ ወቀት ላይ ፈጽሞ አይሆንም።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዙ የሚአስመልሰው የቤት ሥራ ከፊቱ ይጠብቀዋል። ይህንም ቀስበቀስ፤ በስርዓት፤ በትዕግስት፤ በዘዴና በጥበብ ይሚአደርገው ይሆናል። በቅድሚያ በወረበሎች የተነጠቀውን ኢትዮጵያዊነት ማስመለስ ነው። የዚህ ሂዴት በዶ/ር ዓቢይ፤ ገዱና ለማ ተጀምሯል። የተነጠቅነውን ህብረ ብሄር ሰራዊት አስመልሰን የኢትዮጵያን የህብረተሰብ ስብጥር የሚአንፀባርቅ ሰራዊት ማቋቋም። ቀጥሎም ሁላችንም የምንመርጠውን ሕዝባዊ መንግሥት መመሥረት። ከዚያም ከኤርትራ ጋር የሰከነ ግንኙነት ፈጥረን ቢቻል በፌደሬሽን ወይም በሌላ ዘዴ ከእናት ሃገሯ ጋር ማዋሃድ፤ ይህ ካልተቻለ በውይይት የባድሜን ጉዳይ በጠረጴዛ ዙሪያ መፍታት ይሆናል።

ቀስ ተብሎም አሰብን በዲፖሎማሲ ማስመለስ፤ ይህ ካልተቻለ ሁለቱን በጋራ ገበያ ማእቀፍ አስገብቶ ሁሉንም ወደቦች እንደልብ መጠቀም፤ የኢኮኖሚ ትስስር በመፍጠር ውህደታችንን ማሳካት ይሆናል። አስታውስ ሆንግኮንግና ማካው ከ99 ዓመት ትዕግስት በኋላ በዲፕሎማሲና በጥበብ እናት ሃገራቸው ቻይናን ተቀላቅለዋል። ኢትዮጵያም 27 ዓመት ያለወደብ ከቆየችው ጊዜ አይበልጥምና በዲፕሎማሲ ጥበብ እንመልሳታለን ቀደምሲል ደግነታችንን እንደ ድንቁርና፤ አብሮነታችንን እንደመርገም፤ ስብእናን በንቀት አይታችሁ 40 ዓመት የተጫወታችሁት ቁማር አብቅቷል።

ብዙ ትምህርት እና ግብረ መልስ (lesson & feedback) ሰጦን አልፏል፤ ማለፍ አይበለውና። የኢትዮጵያን ሕዝብ ንብረትና ሃብት ዘርፋችኋል፤ ሃይማኖት አርክሳችኋል፤ ሕዝባችንን አፈናቅላችኋል፤ ገድላችኋል-በቃችሁ። ከዚህ በኋላ ዳግም አንሞኝማ። አሁን ኢትዮጵያዊነትን እየሰበከ፤ የጎበጠውን ለማቃናት፤ የተበላሸውን ለማደስ፤ ጥላቻን ወደ ፍቅር ለመቀየር የተነሳ ቅን ሰው አግኝተናል። መንገዱን አታበላሹበት። ያንተ ምክር ዶ/ር ዓብይ የጀመረውን መልካምና ቀናህ መንገድ ለማጣመም እና የሱን የስራ ጅምር ለማበላሸት የታሰበ፤ መሪአችንን ከሕዝብ ጋር ለማጣላት የተሸረብ የተንኮል መንገድ ስለሆን አንቀበለውም።

ምንአልባት አቶ አስራት ዓላማ አስመራ ላይ መንግስት በመለወጥ፤ አሰብና እና ባድሜን አስመልሶ ታላቋን ትግራይን መስርቶ ነፃ ለመውጣት የታለመ እንደሆነ ካስተሳሰቡ መረዳት ይቻላል። ሶስት ሚሊዮን ሕዝብ ሆናችሁ 97 ሚሊዮን ሕዝብ ላይ ስትጨፍሩ የነበረበት ዘመን እያከተመ ነው። ይህ ሕዝብ ከተነሳ እንደሱናሚ አጥቦ ከምድረገጽ ሊአጥፋችሁ ይችላልና ትንሽ አደብ ግዙ። አንተን የመሰል ወጣት አስተማሪ፤ እስር ቤት ዱላ ሳይነካህ ግን ወገኖችህ ብዙ ግፍ ሲፈጽሙ ካየ ሰው የተሻለ የመፍትሔ ሃሳብ ይጠበቅ ነበር። ምንያረጋል በዘረኝነት የተበከለ አእምሮ ምንጊዜም ደግ አያስብምና ጥሩ ነገር ያስደነብረዋል፤ ቀናሁ መንገድ ይጣመምበታል፤ ጊዜ ይመሽበታል፤ ኢትዮጵያዊነት እሬት ይሆንበታል። ስለሆነም ወጣቱ የባድሜና የትግራይ ትግርኝት ጠበቃ ካሸለምክበት የዘረኝነት አባዜ ንቃና የዶ/ር ዓቢይን ባቡር ተሳፈር። ባቡር ቆሞ አይጠብቀም እና። ቸር ይግጠመን!

ነን ሶቤ

ጥር 16 ቀን 2018

LEAVE A REPLY