~ዛሬ ግንቦት 2/2010 ዓም ከሁሉም የእስር ቤቱ ማማዎች መሳርያዎች ወደ እስረኛው ተጠምደው እንዳረፈዱ ለማወቅ ተችሏል
~ሚያዝያ 30/2010 ዓም ቀጠሮ የነበራቸው በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ክስ መዝገብ 38ቱ ተከሳሾች ችሎት ከተረበሸ በኋላ ቂሊንጦ ዞን 5 የታሰሩት ተከሳሾች ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል
~ ከ38 ተከሳሾች መካከል 11ተከሳሾች ከፍርድ ቤት እንደተመለሱ ጨለማ ቤት ገብተዋል። ፍፁም ጌታቸውን ጨምሮ ፍርድ ቤት ላይ ጥያቄ ያነሱት ተደብድበዋል። የአጥፉ አበራ እጅ ጉዳት ደርሶበት በፋሻ እንደተጠቀለለ ታውቋል
~የቂሊንጦ እስር ቤት ከ38ቱ ተከሳሾች መካከል ነፃ ከተባሉት 8 እስረኞች ውጭ ሌሎቹን ዛሬ ግንቦት 2/2010 ዓም ወደ ዝዋይ እጭናለሁ በማለቱ የዞን 1 እስረኞች “ወደ ዝዋት አይሄዱም” ብለው በመቃወማቸው ውጥረት ነግሶ እንዳረፈደ ለማወቅ ተችሏል። በዚህም መሰረት ከሁሉም የእስር ቤቱ ማማዎች ወደ እስረኛው መሳርያ ተጠምዶ አርፍዷል። የቤተሰብ ጥየቃም ተከልክሎ የነበር ሲሆን የጀመረው ከጠዋቱ አራት ሰዓት በኋላ ነው።
~የ38ቱ ተከሳሽ እስረኞች ከፍርድ ቤት ከተመለሱ በኋላ የርሃብ አድማ እንዳደረጉ ተገልፆአል። እስካሁንም ምግብ አልበሉም። የቂሊንጦ እስር ቤት ከአሁን ቀደምም 22 ተከሳሾችን ወደ ዝዋይ በመውሰድ ጠዋት ጠዋት ራቁታቸውን አሸዋ ላይ አስተኝቶ፣ ላያቸው ላይ ውሃ በመድፋት የግርፋትና ማሰቃየት ተግባር እንደፈፀመባቸው በችሎት መናገራቸው ይታወሳል። እስር ቤቱ ተከሳሾች ወደ ዝዋይ እጭናለሁ ሲል አለመግባባት የተፈጠረውም ከአሁን ቀደን በእስረኞች ላይ ከተፈፀመው የማሰቃየት ተግባር አንፃር ነው ተብሏል።
~የቂሊንጦ እስር ቤት ባልታወቀ ምክንያት ከተለያዩ የእስር ቤቱ ዞኖች ታስረው የነበሩ የፖለቲካ እስረኞችን ወደ ዞን አንድ እንዳዛወራቸው ታውቋል። በአሁኑ ወቅት ቂሊንጦ ዞን 1 ውስጥ ከ270 እስከ 300 ያህል የፖለቲካ እስረኞች በእስር ላይ ይገኛሉ።