አቶ አባይ ጸሀዬን ጨምሮ አራት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት መባረራቸው ተገለጸ

አቶ አባይ ጸሀዬን ጨምሮ አራት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት መባረራቸው ተገለጸ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አቶ አባይ ጸሀዬን ጨምሮ አራት ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ከሀላፊነት ቦታቸው ማንሳታቸውን የተለያዩ ምንጮች ገለጹ።

በከፍተኛ ወንጀልና ሌብነት ስማቸው በተደጋጋሚ የሚነሳው በሚኒስትር ማዕረግ የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተር በመሆን የጠቅላይ ሚኒስትር አማካሪ የነበሩት አቶ አባይ ፀሐየ ከሀላፊነታቸው ከተነሱት መካከል እንደሚገኙ ለኢሳት የደረሰው የማሰናበቻ ደብዳቤ ይገልፃል።

C6BADE7E-E1B0-4305-A0B9-1419A5993058

በተጨማሪም የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ቴዎድሮስ ሀጎስ፤ ጠቅላይ አቃቢ ህግ የነበሩ አቶ ጌታቸው አምባየና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ወይም ኢንሳ ምክትል ዳይሬክተር የነበሩት ኮሎኔል ታዚር ገብረ እግዚአብሄር ከሚያዚያ 12/2010ዓ.ም ጀምሮ ከሀላፊነታቸው የተነሱ መሆኑን የሚገልፅ ደብዳቤ እንደደረሳቸው ታውቋል።

LEAVE A REPLY