ከኦሮሚያ ክልል የአማራ ተወላጆች ከቀያቸው እየተፈናቀሉ መሆኑን ገለጹ

ከኦሮሚያ ክልል የአማራ ተወላጆች ከቀያቸው እየተፈናቀሉ መሆኑን ገለጹ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ከኦሮሚያ ክልል የአማራ ተወላጆች ከቀያቸው እየተፈናቀሉ መሆኑን ገለጹ። በምዕራብ ሸዋ ዞን ዳኖ ወረዳ(አምቦ አካባቢ) የአማራ ተወላጆች መሬትን ጨምሮ ሀብት ንብረታቸው እየተዘረፈ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ መደረጋቸውን ተፈናቃዮች አረጋግጠዋል።

 ከግንቦት 1/2010ዓ.ም ጀምሮ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ በወረዳውና ቀበሌው አመራሮች የተገደዱት ተጎጂዎች እንደሚያስረዱት “መሬቱን ለኦሮሞ ወጣቶች ማከፋፈል ስለምንፈልግ ለቃችሁ ወደ ምትሄዱበት ሂዱ”በመባላቸው ከ1200 በላይ ሰዎች አዲስ አበባ መግባታው ታውቋል።

አዲስ አበባ የገቡት ተፈናቃዮች 30 ተወካዮችን በመምረጥ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፣ፋና ራዲዮና በፌዴሬሽን ምክር ቤት የገጠማቸውን ችግር ለማስረዳት ቢሞክሩም እስካሁን ሊሳካላቸው እንዳልቻለ ያነጋገራቸው አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል ገልጾልናል።

  በእድሜ የገፉ አዛውንቶችን ጨምሮ ህፃናት ያለመጠለያ ዝናብና ፀሀይ እየተፈራረቀባቸው በመሆኑ መንግስትና ህብረተሰቡ ያሉበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ተረድቶ በአፋጣኝ እንዲደርስላቸው ጥሪ ማቅረባቸውም ተገልጿል።

የአማራ ተወላጆች ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሻና መተከል ዞን በገፍ በመፈናቀላቸው እንዲሁም የአንዳንዶች ህይወት ስለጠፋ ሰሞኑን መነጋገሪያ ሆኖ መሰንበቱ የሚታወስ ነው።

 

LEAVE A REPLY