/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በደቡብ ክልል የብቃት ማረጋገጫ ከወሰዱ 43 ሺህ መምህራን መካከል 41 ሺህ የሚሆኑት ፈተናውን ማለፍ አለመቻላቸውን ደቡብ ቴሌቪዥን ዘገበ።
በክልሉ በማስተማር ሙያ ከተሰማሩት 160 ሺህ መምህራን መካክል፤ 43 ሺህ መምህራን የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ወስደው 1300 መምህራን ብቻ ማለፋቸው አስደጋጭ ነው ተብሏል። ውጤቱን በማስመለክት አስተያየት የሰጡ መምህራን እንደገለጹት “የአስተማሪዎች ብቃት ማነስ” በሀገሪቱ ላይም ሆነ በተማሪዎች ላይ ከፍተኛ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል ጠቁመዋል።
ለዚህ ደግሞ የመማር ማስተማር ነፃነት (academic freedom) በትምህርት ቤቶች ውስጥ አለመኖር እንዲሁም የትምህርት ተቋሙ በፖለቲካ ሰዎች መመራቱ የከፋ ውጤት ለመመዝገቡ ትልቁን ድርሻ እንደሚይዝ ገልጸዋል።
በደቡብ ክልል ከ160 ሺህ በላይ መምህራን በስራ ላይ ሲሆኑ አብዛኛዎቹ የማስተማር ዘዴ ሳይንስ(pedagogy) ክህሎት ማነስ እንደሚስተዋልባቸው አንድ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ መምህር አስተያየቱን አካፍሎናል።