ኢትዮጵያ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በማሰሯ የእንግሊዝ መንግስት 11 ቢሊዮን ዶላር መከልከሉን ጠ/ሚኒስትር...

ኢትዮጵያ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በማሰሯ የእንግሊዝ መንግስት 11 ቢሊዮን ዶላር መከልከሉን ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ ገለጹ

በብሄራዊ ቤተመንግስት ለትግራይ ክልል ተወላጅ አርቲስቶች፣ ባለ ሀብቶች፣ ታዋቂ ሰዎች ፖለቲከኞችና ሌሎች ተጋባዦችን  ትናንት ምሽት ከ12 ሰዓት ጀምሮ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ የእራት  ግብዣና ነጻ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።

በግብዣው ላይ የተገኘው አብርሀም ግዛው ጠ/ሚኒስትሩ ከተናገሩት መካከል የተወሰኑትን በፌስ ቡክ ገጹ የሚከተለውን ለአባቢያን አጋርቷል።

——–

  “ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገራም ንግግሮች ቀጥለዋል! ድግሶች ሰብሰባዎች ንግግሮች በዝቷል የሚሉ አሉ። እኛ አዲሰ ሃሳብ እንዲጀመር የምናዳምጠዉ መልስ የምንሰዉና የምናክመዉ ዜጋ አለን ለዛም ሌላም ኘሮግራሞች አሉን

ዛሬ ምሽት 12:00 ላይ ብሔራዊ ቤተ -መንግስት ጥሪ ለተደረገላቸዉ እንግዶች በተለይ ከወትሮ የግብዥ ዝግጅቶች በርካታ መኪና ማቆሚያ ስክንቸገር ነበር ዛሬም ቪዲዮ ሞባይል ባልተፈቀደበት ምሽት

የዛሬዉ ጥሪ አንዳንድ አርቲስቶች ቢያካትትም የበዛዉ ባለሀብቶች ነበሩ ምንም እንኳን የአርቲስቶቹን ስም እንዳይጠቀስባቸዉ ስለጠየቁን የመጡት ባለሀብቶችና አርቲስቶች ስም ለግዜ እንዝለለዉና ወደ ዋነኛዉ ጉዳያችን ብዙዉ ታዳሚዎቹን ያስገረሙ ንግግሮች ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ዶ/ር አብይ አህመድ ተናገሩ አንድ ስንሆን ያምርብናል ስለብሔር ከምናወራ አንዲት ኢትዮጲያ እናዉራ አንዳንድ ባለስልጣናት ፀሐፊዋ ትግሬ ሱፌሩ ትግሬ ጋርዶቻቸዉ ትግሬ ሰራተኞቹ በዘመድ እነዚህ የትግራይን ክልል ተወላጆችን ሌሎችም ብሔራቸዉን መሰግሰግ የተለመደ ሆኗል። የተለየ ጥቅም እንዳገኙ ህብረተሰብ ዉስጥ የተሳሳተ መረጃ አለ።

ለምሳሌ ሸሬን አዉቃለሁ መቀሌ ብትሄድ የዉሃ ችግር አለ። የተወሰኑ ለሆዳቸዉ ያደሩ ባለሥልጣናት ህዝብን በትግራይ ህዝብ የሚነግድ አሉ ስልጣን ልቀቁ ሲባሉ ሞት የሚመስላቸዉ ሰሞኑ ጡረተ እንዲወጡ ከተደረጉት ባለሥልጣናት ዉስጥ አብዛኛዎቹ አኩርፈዎል አንዳንዶቹ 20ዓመት ሌላዉ 15አመት ለተተኪ ቦታዉ መስጠት አይወድም ስልጣን የያዙም ያማርራሉ ሮሮ ነዉ ይህን በህገ መንግስት ማሻሻል አስተካክላለሁ እኔ ባለሁበት ጊዜ አስተካክዬ ሌላዉ ምሳሌ ወኜ በተርሜ መዉረድን ነዉ። የምፈልገዉ ስልጣ ምንድ ነዉ? ብለዉ ኃይለስላሴ ሲጠይቁ አንድ በእግዚሀብሔር የተሾመ ሌላዉ ህዝብ የሚያሰተዳድር ሲሉ ስልጣን ማለት በህዝብ ትካሻ ላይ መቀመጥ ማለት ነዉ አንድ ህፃን ተሸክማችሁት ትንሺ ስትሄድ ልታወርድ ስትሉ ትንሺ ሂድ ይላቹሏል ወይም ያለቅሳል ይህን ቦታ መልቀቅ አይፈልጉም። በነገራች ላይ ከአቶ ታደሠ ሃይሌ በስተቀር ጡረታ የወጡት ደስተኛ አደሉ ።ሁሉንም የግል ሥራ እንዲያገኙ እያደረግን ነዉ። ስልጣን በቃቹ እኔ እያለሁ አንድ አትጠየቁም አትታሰሩ ብዬ ነግሬቸዋለሁ እሲኪ ገለል በሉ ብያለዉ ኩርፌያ ጥላቻ ይቅር። መንግስት ባለሥልጣናት ሚኒስትሮች ይገመገማሉ።

በተለይ ህብረተሰብ የሚነሱ ጥያቄዎች ካልመለሱ ለምሳሌ ፍትህ 50ጥያቄ ባህልናቱሪዝም 10 ቢሆን የማሳያ ቁጥሩ የበዛበት ችግሮች ያሉበት ሚኒስትር የህብረተሰብ ጥያቄ በተገቢ ያልመለሠ ይነሳል ።ኢሃዲግ ከኢትዮጲያ በታች ነዉ እናንተ አታዉቁም ብዙ ችግሮች በድርጅታች አለ። እሱን ለመቅረፍ እየሰራን ነዉ። የኦሮሞ አባገዳዎች ለዉጥ እያመጡ ነዉ ።አማራ ክልልም እየሰራን ነዉ። ትግራይም ስራ ልትሰሩ ይገባል። ሰሞኑን የኤርትራዉን መሪ ኢሳያስ አፍወርቂን ለማግኘት በሳዉዳረቢያ ሸምጋኝነት የሣዉዲዉ ንጉስ ደዉለዉ ኘሬዛዳንቱ አልመለሱም ጥረታች ይቀጥላል። በሳዉዲ በነበረን ቆይታ የጠየቅናቸዉ 10 ጥያቄዎች ከአንድ በስተቀር ሙሉ በሙሉ ተመለሰዎል ከአንድ ጥያቄ ብቻ በይደር እንደሚፈታ ተናግረዉ።

የኤርትራዉ ኘሬዘዳንት ኢሳያስ አፍወርቅ ኢትዮጲያና ሱዳን መንግስቴን ለመጣል አሲረዋል ብለዋል። እኛ ሰለም ጉዳይ ልማት ላይ ነዉ ከኘሬዘዳንቱ አልበሸር የተወያየነዉ። ስለባለሀብቱ ሲናገሩ እንደሰዉ ያመናል ብለዋል ምሽት በርካታ ጥያቄዎች ተነሰተዉ ምላሽ ተሰቶባቸዎልደ 1ኛ በሚቀጥሉት ሳምንታት የታሰሩት ባለሀብቶችና የፖለቲካ እስረኞች እንደሚፈቱ ተናግረዋል ።ከነዚህም መሀከል አቶአንዳርጋቸዉ ፅጌ መፈታት ላይ ከከፍኛ ባለሥልጣናት ጋር ይፈታ አይፈታ። በሚል ጭቅጭቆች ነበሩ እኔ አልቀበልም ይፈታል እኔ ምለዉ እሱ ኢትዮጲያ ላይ አሲሯል ተብሎ ነዉ አንዳርጋቸዉ ፅጌን በማሰራችን በአራት ዓመት ዉስጥ ኢትዮጲያ 11 ቢሊዮን ዶላር በላይ አታለች ትላቻን አትርፈናል።

ምንድነዉ የሱ መታሰር ጥቅሙ እኔ አልሰማማም አይፈታ የሚሉ ባለሥልጣናት አሉ ሰዉ የገደለ እየተፈታ 10 ሰዉ ገሎ ከረኔል ደመቀ ተፈቷል። ታዲያ አንዳርጋቸዉ ለምን አይፈታም? ሁለት ጀኘሯሎች በመንግስት ግልበጣ ላይ አሲራቹሃል በማለት ፍትህ ሳያገኙ ረጅም ጊዜ ታስረዉ ትዳራቸዉ ፈርሳል። እነሱም ምንም ሳይጠቀሙ ያላግባብ ብዙ የተበደሉና የታሰሩ አሉ። በሂደት እያየን እንሄዳለን የዚች ሀገር የፍትህ ሥር-ዓቱ መስተካከል አለበት። አንድ አስገራሚ ነገር ልንገራቹ አንድ ሰዉ ገልሃል ተብሎ ተፈረደበት ማረሚያ ወረደ ሞቷል የተባለዉ ሰዉ አለዉ በስህት ነዉ ያሰራችሁት ብሎ ሞተ የተባለዉ

ብሎ ቢሟገትም አንዴ ስለተፈረደበት ፍርድን ጨርሶ ይዉጣ ነዉ። የሚባልባት አገር ነዉ ያለ ነዉ። ብለዋል ይሄ አይቀጥልም በሚቀጥለዉ ሳምንት ወደ ግብፅ እሄዳለሁ ለዲኘሎማሲ እንዳይመስላቹ በሊቢያ ሀገር የታረድ ወገኞቻች አስክሬን ለማምጣት ነዉ። ይሄ እብድ ጠቅላይ ሚኒስቴር ይበሉ ቅድሚያ የምሰጠዉ ለዜጎቻችን ክቡር ነዉ። በክቡር በሀገራቸዉ መካነ ቀብራቸዉ እንዲያርፍ እናረጋለን ሰሞኑን በሄድንባቸዉ አገሮች ዜጎቻችን እንዲያከብሩና ዜግቻችን እንዲለቁ ጠይቀናቸዉ ተቀብለዉናል።

ሳዉዲ የአንድ አመት ነዳጅ ፍጆታ እንደሚሰጡና የሄድንባቸዉ ሃገራት 5ቢሊዮን ዶላር እንደሚለግሱን ቃል ገብተዋል ።ይህ ሁሉ የመጣዉ አንድ ሰለሆን ነዉ እኔ በ2 ወር ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ የሰራሁት በ2 ዓመት አልተሰራም ከመመሰጋገን ይልቅ አቃቂር ማዉጣትና መተቻቸት እናበዛለን። ዛሬ እንዲህ በነፃነት እንድናወራ እንድንጫወት ነዉ የምጠይቀዉ ጥያቄዎች መልስ እሰጣለሁ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ግብዥዉ አጠራሩ እንዴት ነዉ እኔ ሰለተጋበዝኩ ደስ ብሎኛል በምን መስፈርት ተጠራን ዮኒቪርስቲ ዉስጥ የብሔር ጎራ መለየት አለ እንዴት ያዮታል? ወ/ሮሰሎሜ ታደሠ አለ ይህን ለማስተካከል እየሰራን ነዉ ።3 የዮኒቪርስት ኘሬዘዳንቶች አንሰተናል ቦርዶች በትነናል ብሔርተኝኘት ስላለ የትምህር ካሬ ኩለሙ እናተካክላለን እየተሰራ ነዉ። አቶ ገብሩ አስራት እና ሌሎች ባለስልጣናት መንግስት አገልግለዉ በክብር ለምን አይሸኑም ልክነዉ እነዚህ 20 ወይም 21ቁጥራቸዉ አይበልጡም ግን እዚህ ብዙ ባለብቶች አላቹ እና ሌሎች ግለሰቦች ለመርዳት 1ሚሊዮን አንድ ሚሊዮን አዋጡ እኔ እገኛለሁ በሲህም ከባለሀብቶች ገንዘብ ሰበሰበ ብለዉ የሚጠይቁኝ ካሉ ልጠየቅ እና በክቡር እንሸኛቸዋለን ብዙዎቻቹ በሚዲያ ሰምታቹሁታል ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን ቢሮ ጠራሁት ሲመጣ ዘግይቶ ነዉ ታክሲ አጥቼ ነዉ አለኝ ጫማዉ ጭቃ በጭቃ እንዴ ዶ/ር መኪና የለህም? እንኳን መኪና ቤቴ ያፈሳል ስለኝ ድርጅቻችን ኦሄዴድን ሰብስቤ እንዴት ለሀግር የሰራን ሰዉ ያለማክበር በአስቸኳይ መኪና ቸገዙቶ ተሰጠዉ። ኢሃዲግ ከአመት በፊት ብልሽት ዉስጥ ወድቆል ይህን ለማስተካከል እየሰራን ነዉ።

መንግስቱ ኃይለማርያ ይቅርታ አድርገን አገር ይግባ ስልል ብዙዎች የተቃወሙት እኛ ይቅርታ ካላሳየን ምን ዋጋ አለዉ ።አንዳንድ ወገኖች እሰር ብሩን የበሉትን አስመልስ አጣራ ይላሉ። ጥሩ ነዉ እነሱ በማሳደድ ጊዜ አላጠፋም ምክንያቱም ከፊቴ ብዙ ስራ አለ ከዚህ በሏላ እንዳበሉ እንዲሁም ዶላር ወደ ሀገር ቤት አንዲገባ በቅርብ ዉጭ ያለዉ ዶላር የባለሥልጣናት እያጣራን ነዉ ።ሚዲያ አሁን በዝቷል ጥሩ ነዉ አንዳንድ ሚዲያዎች ከስነ -ምግባር የላቸዉ የራሳቸዉ ብሎ በተለይ ሚዲያዉ ተገልፃል የሼህ ሁሴን አላሙዲን ዘገባ በተሳሳተ መንገድ መዘገቡ እሳቸዉ ለሀገርና ለወገን የረዱ ሰዉ እኛ ችግር አጋጠማቸዉ ብለን ድርጅት ከመዝጋት ጊዜ ሰጠን አሁን ለጊዜ ይዘጋ ብለን ወሰንን ብዙ ከድርጅቶቻቸዉ ጋር በተገናኘ ችግሮች አሉ ህብረተሰብን መርተዉታል በተለይ በሽተኛ ሚዲያ ያሉ ሲሆን ሚዲያ ነፃ እንዲሆን እንፈልጋለን ሰነ- ምግባር የጎደላቸዉ ቅልብተኛ ሚዲያዎች አሉ እነሱን በህግ የሚጠየቁበት አግባብ እየተበጀ ነዉ። ሁሉም ዜጋ ባይተዋር እንዳይሆን ይቅር እንድንባባል ሁሉም ዜጋ በኩልነት እንዲታይ አብረን እንስራ አግዙን።

መስራት ካለብን መስራት ነዉ። ሰዉ እንጂ ዘር አንይ የትግራይ ተወላጆት ኃላፌነት ቦታ ቀነሰ ሲባሉ የሰጡት መልስ ባለፈዉ ጊዜ አሁን ካለፈዉ 11ሚኒስቴር ዴታዎች 13ደርሰዎል ኦሄዴድም አነሰ ካለ ስራ መስራት አይቻልም ችግሮች አሉ ።ደረጃ በደረጃ እንቀርፉለን በየመሃሉ ፈገግ ያደርጉ ነበር ።ፅንፈኝነት ይቅር ካነሱቸዉ ዋና ዋና<span lang=”AMH” style=”font-family:Nyala”

LEAVE A REPLY