ሰበር ዜና – አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ለመፍታት የምህረት ደብዳቤ ለፕሬዚዳንቱ መላኩ ...

ሰበር ዜና – አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ለመፍታት የምህረት ደብዳቤ ለፕሬዚዳንቱ መላኩ ታወቀ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ለመፍታት የምህረት ደብዳቤ ለፕሬዚዳንቱ ሙላቱ ተሾመ መላኩ  ታወቀ።

ከየመን ታፍነው ባለፍት አራት አመታት በኢትዮጵያ በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ያለፉት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ለምህረት ስማቸው ከተላከላቸው እስረኞች መካከል ስማቸው እንደሚገኝ ማምሻውን ተዘግቧል።

እንደ ሪፖርተር ዘገባ የተላከውን የምህረት ደብዳቤ ፕሬዚዳንቱ ፈርመው ለፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ይልካሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ  ገልጿል። በጉዳዩ ዙሪያም ነገ የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በጉዳዩ ላይ ነገ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣልም ተብሏል።

 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባለፈው ማክሰኞ በታላቁ ቤተመንግስት ለትግራይ ተወላጆች ባደረጉት የእራት ግብዣ ወቅት  አቶ አንዳርጋቸው በመታሰራቸው ጥላቻና ከእንግሊዝ መንግስት 11 ቢሊዮን ዶላር ኢትዮጵያ ማጣቷን እንደገለጹ መዘገቡ ይታወሳል።

 

LEAVE A REPLY