«የትብብር ጥያቄ ለፖለቲካ እስረኞች ቤተሰቦች እና ወዳጆች፣»
/ያልተፈቱትን ስለማስፈታት/
«መንግሥት የፖለቲካ እስረኞችን ለመፍታት ከወሰነ 3 ወራት ገደማ ሆኖታል። ብዙዎች ቢፈቱም አሁንም ብዙዎች በእስር ላይ ይገኛሉ። በመሆኑም፣ በ”ሽብር” ወይም/እና “ሁከት” የተከሰሱ (ጉዳያቸው እየታየ) ወይም የተፈረደባቸውን ግለሰቦች (ጉዳያቸው በፌደራል ደረጃ የሚታዩትን) ጉዳይ ስንከታተል የነበርን ጠበቆች ለሚመለከተው አካል እንዲፈቱ ጥያቄዎችን ዘርዝረን ማቅረብ የጀመርን ቢሆንም፣ በጠበቆች ያልተወከሉ፣ ጉዳያቸውን ተከታታይ የሌላቸው ብዙ እስረኞች መኖራቸውን እናውቃለን።
«ስለሆነም ጉዳዩን መከታተል የጀመርነው ጠበቆች እንድንከታተልላቸው የምትፈልጉ የሚመለከታችሁ ሰዎች ብቻ ክሳቸው በመታየት ያሉት ሰዎችን ሙሉ ሥምና የክስ መዝገብ ቁጥር፣ ፍርደኛ ከሆኑም ሙሉ ሥምን ከመዝገብ ቁጥሩ እና የተፈረደባቸውን ጉዳይ አጭር መግለጫ ካለበት ማረሚያ ቤት ሥም ጋር እስከ ግንቦት 20 ቀን 2010 ድረስ መላክ ይችላል።
«ሥራው ምንም ዓይነት ክፍያ አያስከፍልም።
«አስተባባሪ፣ ጠበቃ ኄኖክ አክሊሉ፣
«የኢሜል አድራሻ: henoklawyer@gmail.com ብለው ቢልኩ ይደርሳል።
«እናመሰግናለን!»