/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከእስር ቤት ተፈተው ቤተሰቦቻቸውና አድናቂዎቻቸው ጋር ተገናኝተዋል። በቦሌ ክ/ከተማ ኦሎፒያ አካባቢ በሚገኘው በአባታቸው ቤት በርካታ አድናቂዎቻቸው ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
አቶ አንዳርጋቸው በሰጡት አጭር ቃለ-ምልልስ አራት ዓመታት በእስር ቤት ሲያሳልፉ ምንም መረጃ እንዳልነበራቸው ገልፀዋል።
አቶ አንዳርጋቸው አክለውም “በዚህ አራት ዓመታት የተከፈለዉ መስዋትነህ ትንሹ ነው፤እንዲህ አይነት ሀገር ከማይ ሞቴን እመርጣለሁ ብየ ለደህነቱ ነግሬዋለሁ። ከ83-85 አገልግያችሁ ነበር ያንን ውለታ ቆጥራችሁ የሞት ቅጣቱን ተፈጻሚ አደረጉት፤ ሰው እዬሳቀ እንደሚሞት አሳያችኋለሁ። ብያቸው ነበር ያንን ቆራርጠው አቀረቡት። ብለዋል።
አቶ አዳርጋቸው በአባታቸው ቤት ካረፉ በኋላ ቀጣይ እቅዳቸውን እንደሚያሳውቁ የተገለፀ ሲሆን አሁን ባሉበት ሁኔታ ሰውነታቸው ከመከሰቱ በስተቀር ሞራላቸው የተጠበቀና በኩራት የሚናገሩትን በሚገባ መግለፅ የቻሉ መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።