/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በአሜሪካን ሀገር የሚገኝ “የትግራይ ተወላጆች ማህበር” የተሰኘ አንድ ቡድን በኢሳት ቴሌቪዥን ላይ ተመስርቶ የነበረው የ“ሽብርተኝነት” ክስ መነሳቱ እንዳሳዘነው በመግለጽ ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የአቤቱታ ደብዳቤ ፃፈ።
ማህበሩ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት በፃፈው ደብዳቤ እንደገለጸው፤ በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን(ኢሳት) ላይ መንግስት መስርቶት የነበረውን ክስ ማንሳቱንና ወደ ሀገር ቤት ገብቶ መስራት እንዲችል ጥሪ መቅረቡ አግባብ አይደለም ሲል ገልጿል።
ከሁለት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ተቀስቅሶ በነበረው ህዝባዊ አመፅ ወቅት የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን በ“ትግራይ” ህዝብ ላይ ያነጣጠረ የጥላቻ ዘገባ ማሰራጨቱን በመጥቀስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔያቸውን ዳግም እንዲያጤኑ ሲል ማህበሩ ጠይቋል።
የማህበሩ የአቤቱታ ደብዳቤ ተያይዟል፦