አቶ ጌታቸው አሰፋ ከስልጣን ተነሱ

አቶ ጌታቸው አሰፋ ከስልጣን ተነሱ

አቶ አባ ዲላ ገመዳና አቶ ግርማ ብሩ በጡረታ ተሰናብተዋል

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ጌታቸው አሰፋ ከስልጣን ዛሬ ተነሱ። በምትካቸውም የአየር ሀይል ሀላፊ የነበሩት ጄኔራል አደም መሐመድ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከነገ ግንቦት 30/2010ዓ.ም ጀምሮ ተሹመዋል። አደም መሐመድ የብአዴን ታጋይ ሲሆኑ የሙሉ ጄኔራልነት ማዕረግ የተሰጣቸው ባለፈው ጥር 2010ዓ.ም ነው። ከዚህ በፊትም በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ማዕረግ ተሹመውም ነበር።

አቶ ጌታቸው አሰፋ ላለፉት በርካታ ዓመታት የህወሓት ስራ አስፈፃሚ እንዲሁም የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በመሆን ኢትዮጵያዊያንን ያለከልካይ በገፍ ሲገድል፣ ሲያስርና ሲያሰድድ ኖሯል። በማዕከላዊ፣ ቂሊንጦ፣ ቃሊቲ፣ ዝዋይ፣ ሸዋሮቢትና እጀግ በርካታ በመሆኑ ድብቅ እስር ቤቶች አካላቸው ለጎደለ፣ ህይወታቸው ለጠፋና የሞራል ስብራት ለደረሰባቸው አያሌ ኢትዮጵያዊያን በዋናነት ከሚጠየቁት ነብሰ-በላዎች መካከል አንዱ እርሱ ነው።

በሌላ በኩል በመንግስት የተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ ሁለት የሥራ ኃላፊዎች በጡረታ ተሰናብተዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት እንደገለጸው፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፀጥታ ዘርፍ አማካሪ ሆነው በቅርቡ ተሹመው የነበሩት አቶ አባ ዱላ ገመዳና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት አምባሳደር ግርማ ብሩ ከነገ ግንቦት 30/2010ዓ.ም ጀምሮ በጡረታ መሰናበታቸውን አስታውቋል።

 

LEAVE A REPLY