የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በሲጋፖር ተገናኙ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በሲጋፖር ተገናኙ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በሲጋፖር ሴንቶሳ በተባለች ደሴት ተገናኝተው በሰላም ጉዳይ ላይ መወያየታቸው ተገለጸ።

የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በአካል የተገናኙት ከበርካታ የቃላት ጦርነት በሗላ ነው። የአሜሪካና የሰሜን ኮሪያ በስልጣን ላይ ያሉ መሪዎቻቸው ሲገናኙ ይህ የመጀመሪያ እንደሆነም አለም አቀፍ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

ፒዮንግያንግ በኮሪያ ልሳነ ምድር ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ከዋሽንግተን ጋር ለድርድር እቀርባለሁ ባለችው መሰረት ዛሬ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከኪም ጆንግ ኡን ጋር ሲንጋፖር ላይ እጅ ለእጅ ተጨባብጠዋል። የሰ/ኮሪያው መሪ ኪምትራምፕ እንድንገናኝ ምቹ ሁኔታ በመፍጠሩ አመሰግነዋለሁ፣ ያለፈ ታሪክ ወደኋላ ትተን አዲስ ታሪክ እንሰራለንበማለት ገልፀዋል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው እስካሁን ስለየሀገራችን ብዙ ነገሮችን አውቀናል፤ ኪም ጆንግ ኡን ልዩ ተሰጥኦ ያለውና ሀገሩን በጣም የሚወድ ሰው ነው።” ሲሉ ገልጸውታል።  ውይይታችንም ጥሩና ፍሬያማ የሚባል ነው፤ በቀጣይ በሰፊው እንደምንገናኝ አምናለሁ” ብለዋል። ኪም ጆንግ ኡን የቀረበላቸውን ሰነድ ከፈረሙ በሗላ ባደረጉት ንግግር ዓለም ትልቅ ለውጥ ሊያይ ይችላል ብለዋል። ቻይና የሁለቱን መሪዎች ግነኙነት ታሪካዊና የሚደነቅ ነው ብላዋለች።

የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ሁለቱ መሪዎች ተገናኝተው ፍሬያማ ውይይት እንደሚያደርጉና አዲስ ታሪክ እንደ ሚፅፉ ተናግረዋል። ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር መርሃ ግብሯን ሙሉ በሙሉ እንድታቆም አሜሪካ ፍላጎት ሲሆን የሰሜን ኮሪያው መሪ ሀገራቸውን ከኒውክሌር ሙሉ በሙሉ ነፃ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በፒዮንግያንግ ላይ የተጣለው ማዕቀብ “ሰሜን ኮሪያ ሙሉ በሙሉ ከኒውክሌር ነፃ መሆኗን እስከምናረጋግጥ ይቀጥላል” ብለዋል። በሲንጋፖር በተካሄደው ውይይት ላይም ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመው ተጠናቋል።

ሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ማብላያ ጣቢያዋን ባለፈው ግንቦት ወር ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች በተሰበሰቡበት ማፍረስ መጀመሯ የሚታወስ ነው።

LEAVE A REPLY