አየር መንገድ /ሚኪ አማራ/

አየር መንገድ /ሚኪ አማራ/

የኔ አቋም የኢትዮጵያ አየር መንገድ መሸጥ ሳይሆን ያለዉን የgovernance, human resource, and management ችግር መፍታት እና ባለበት ማስቀጠል ነዉ፡፡ ስለዚህም አሁን ያለዉን ሙሉ ማኔጅመንት መበተን፤ ቦርዱን እንደገና ማዋቀር እና መስሪያ ቤቱ ለሁሉም ኢትዮጵያዉያን በአቅምና ችሎታ የሚሰሩበት ማድረግ፡፡

 የማኔጅመንት ችግርና የሰራተኛ ፍልሰት

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዉስጥ የማኔጅመንት ችግር እየታመሰ ነዉ፡፡ በዚህም ምክንያት ከመስከረም ወር ጀምሮ 350 የበረራ አስተናጋጆች እና ሌሎች በመቶወች የሚቆጠሩ ሰራተኞች ለቀዋል ከዚህም ዉስጥ ወደ 40 የሚሆኑት አሜሪካ እና ካናዳ የቀሩ ናቸዉ፡፡በዚህም ምክንያት የሰዉ እጥረት አጋጥሞታል፡፡ ክፍተቱን ለመሙላት ቀደም ብለዉ የለቀቁትንና አዲስ አበባ የሚኖሩትን አልፎ አልፎ እየጠሩ በከፍተኛ ክፍያ በትርፍ ሰአታቸዉ እንዲሰሩ እየተደረገ ይገኛል፡፡

የሰንሻይኑ የሳሙኤሏ ቅንጡ ልጅ

የሳሙኤል የሰንሻይን ባለቤት ልጅ ከደቡብ አፍሪካ በኢትዮ አየር ምንገድ ትመጣለች፡፡ አዲስ አበባ እንደወረደች ዉሃ አስተናጋጆችን ጠይቂያቸዉ አልሰጠኝ አሉ ብላ ትከሳለች፡፡ ከዛ ወዲያዉ ሁሉንም በዚህ ፍላይት የነበሩ አስተናጋጆች ይጠሩና በመኪና ይዘዉ ቤቷ ድረስ ወስደዉ ይቅርታ እንዲጠይቁ አደረጉ፡፡ ከዛም አንድ ሰዉ የቅርብ ሱፐርቫይዘሩን እንዲህ ይደረጋል እንዴ በመኪና ስታፍ ጭኖ እሰዉ ቤት ድረስ ተሂዶ ይቅርታ ማለት ለስታፍ ሞራል ጥሩ ነዉ ወይ በደብዳቤ መጠየቅ አይሻልም ነበር ወይ ተብሎ ይጠይቃል፡፡ ሱፐርቫይዘሩም ስቆ የሳሙኤል ልጅ እኮ ናት የሚል መልስ ብቻ ይሰጣል፡፡ ይህ ጉዳይ ቆይቶ በግቢዉ ሰራተኛ ዉስጥ ትለቅ ጭቅጭቅ ይፈጥራል፡፡ ከዛም በአቶ ተወልደ እና በኢን ፍላይት ማናጀር ሃላፊ በነበረዉ በአቶ ይነሱ የሚባል ሰዉ መካከል ከፍተኛ ዉዝግብ ተነስቶ በመጨረሻም የሀገር ዉስጥ በረራ ሃላፊዉ ሊለቅ ችሏል፡፡

ተወልደ ገ/ማሪያም

———-

አቶ ተወልደ አየርመንገዱ በአለም አቀፍ የኦዲቲንግ ድርጅት ኦዲት ከመደረጉ በፊት የመልቀቅ ሃሳብ እንዳለዉ እና መልቀቅ ካለበት ኦዲት ከመደረጉ በፊት እንደሚሆን ገልጸል፡፡ አየር መንገዱ ባለበት ችግር ምክንያት የኦዲት ዉጤቱ ጥሩ ላይሆን ይችላል፡፡ አቶ ተወልደ ትልቅ አየር መንገድ ስላስተዳደሩ ቢለቅ ሌላ የአየር መንገድ ድርጅት ወይም ተመሳሳይ የተሻለ ስራ እንደሚያገኝ ያዉቀዋል፡፡ በመሆኑም ኦዲት መደረጉ ሳይሆን ያሰጋዉ ከኦዲቲንግ በኋላ የራሱ ስም እና ዝና ሊበላሽ ይችላል በሚል ነዉ፡፡ ድርጅቱን ችግር ዉስጥ ተብትቦ የወጣ ማናጀር ማንም ሊቀበለዉ አይችልም፡፡ ከዚህም ዉጭ አቶ ተወልደ የረዥም ጊዜ ህመም እንዳለባቸዉ እና በየጊዜዉ ህክምና እንደሚከታተሉ ይታወቃል፡፡ ይሄም ለመልቀቅ አንዱ ገፊ ምክንያት ነዉ፡፡

በነገራችን ላይ ማንም የህወሃት ባለስልጣናት በዚህ አየር መንገድ ሲሄዱ ዉሃ እንኳን አይቀምሱም፡፡ ለምሳሌ ዶ/ር ቴወድሮስ ለ 13 ሰአት በዚህ አየር መንገድ ሲበር አንዲት ነገር አይነካም፡፡ እንመረዛለን ብለዉ ያስባሉ፡፡

LEAVE A REPLY