የቀድሞ የህወሓት መስራችና የኢኮኖሚ ፋይናንስ ሃላፊ የነበሩት አቶ ገብረመድህን አርዓያ ስለ ባድመና የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት አጀማመር እንዲሁም ታሪኩን ከመነሻው ጀምሮ ይናገራሉ!
________
ዛሬ በሃገራችን ኢትዮጵያ የህዝብ ትልቁ መነጋገሪያ የሆነው የህ.ወ.ሓ.ት.( ኢህአዴግ )ስርአት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ተሰብስቦ ካሳለፋቸው ወሳኔ አንዱ የኢትዮ፟-ኤርትራ ግንኙነት በተመለከተ ነው ።
የአንዲት ሉአላዊት ሃገር ኢትዩጵያ ልጆች ሁነው ለስንት ሺህ አመታት አብረው የኖሩ አንድ አካል አንድ ህዝብ በመሆን የኖረ ህዝብ፤ በሁለቱ ወንድማሞች ሃገራት ሲባል በጣም ከባድ ነው አሁንም የኤርትራ ህዝብና የእትዮጵያ ህዝብ ፤በባህል፤በቋንቋ ፤በሥጋ ዝምድና ወዘተ የተሳሰሩ ህዝብ ስለሆኑ ተመልሶ መተቃቀፉና ወደ አንድነቱ ተመልሶ መምጣቱ አይቀርም ። ኢትዮጵያ ሃገራችን በአንድነት እንገነባት አለን ።ዛሬ በውጭ ሃገር የሚኖሩ በኤርትራ ህዝብና በኢትዮጵያ ህዝብ የሚታየው መልካም መግባባት ፍቅር የአንድነት ሰላም ፤በደጉም ፤በክፉም መተባበርና መደጋገፍ በግልፅ ይታያል ፤ ለቸሩ አምላክ የሚሳነው የለምና ወደ ቀድሞው አንድነታችን ይምልሰናል ። ይህ ባጭሩ ካልኩ ፤የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ክፉ መዘዝ የመጣ ከየትኛው መዓዝን ተነስቶ ነው ።እውነት ባድመ በኤርትራ ግዛት ውስጥ ነበረች ?ለኢትዮጵያ ሊቃውንት ለታሪክ ተመራማሪዎች ልተወው ።
የንፁሓን ደም የፈሰሰው በምን ምክንያት የተነሳ ነው ።ሁሉም ነገር መነሻ አለው ፤በዚች ዓለም አንዱን ነገር ሊያምር ወይም ሊበላሽ የራሱ የሆነ ምክንያቶች አሉት(cause and effect ) ።አንድ ነገር የመነሻ ምክንያት ከሌለ አንድ ምክንያት አይከሰትም ።
በኢትዮጵያና በኤርትራ በባድሜ የተፈጠረው ክ100ሺህ በላይ የሰው ሂወት የቀጠፈው ፤የሃገር ሃብትና ንብረት ያወደመው ደም አፋሳሽ ግጭት የፈጠረው የራሱ ምክንያት አለው ።ይህ ምክንያትም የዛን ጊዜ ስሙ ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ (ተ.ሓ.ህ.ት)የዛሬው ስሙ ፤ህ.ወ.ሓ.ት.)የፈጠረው ፀረ ህዝብ ፀረ ኢትዮጵያ ሉአላዊነት ደደቢት ይዞት የመጣ ነው ።
አንዳንድ ሊሂቃን እንድሚናገሩት ይህ ጦርነት የተነሳው በኢኮኖሚ ሳቢያ ነው፤ሌላ የተማረ ምሁር ደግሞ ሌላ ይናገራል፤ነገር ግን ይህ አውዳሚ ጦርነት የተነሳው ፤በባድሜና በሌሎች የመሬት ይገባኛ ጥያቄ ነው ፤ ለጦርነቱ መንሰኤ ዋና ምክንያቱ ይህ ነው ;። ይህን በድፍረት የምናገረው የተ.ሓ.ህ.ት.(ህ.ወ.ሓ.ት.)የመጀመሪያው ከምስረታው ትንሽ ወራት ቆይቸ የተቀላቀልክት የበረሃ ወይም ሜዳ ታጋይ የነበርኩ ከ15 ዓመታት በላይ የታገልኩለት ድርጅት የመሪዎቹ ሤራና ተግባር ፀረ ኢትዮጵያ ፀረ ኢትዮጵያ ህዝብ ሆነው ደደቢት የወረዱ መሆናቸው በሚገባ ስለማውቃቸው ነው ። በኋላ አውግዠው የወጣሁ ።
ህ.ወ.ሓ.ት.( ማ.ገ.ብ.ት.)(ተ.ሓ.ህ.ት.)በየካቲት 11 ቀን 1967 ዓ.ም. ትግራይን ከኢትዮጵያ ለመገንጠል ብረት ታጥቆ ደደቢት በረሃ እንደገባ ፤ብዙ ችግር ነበረው ፤ከችግሮቹ ፤በሽታ፤ርሃብ፤ወ.ዘ.ተ.ብረት፤ጥይት፤ስንቅ፤ ሌላም ከባድ እጥረት ነበሩት ፤ በጣም የተጎሳቋለ ድሃ ድርጅትም ነው ።ህ.ወ.ሓ.ት. ወያኔው ለጊዝያዊ ጥቅሙ ሲል የማይቆፍረው ጉድጓድ የለም አሁንም እንደዛው ፤የማይሰራው የማጭበርበር የማይዋሸው ጉድ የለም ይዋሻል፤ አስመስሎ ተናጋሪ፤ ከሃዲ፤ ዘራፊ ፤ሽብርተኛ እባብ ተንኮለኛ በዓለም ተዋዳዳሪ የሌለው ህ.ወ.ሓ.ት. ብቻ ነው ።፤ብረት፤ ጥይት፤የእጅ ቦምብ፤አርፒጂ ወ.ዘ.ተ.ለማግኘት ሲል በተወሰነ እንኳን ከሻእብያ ቢያገኝም በበለጠ የታጠቀ የተደራጀ ጀብሓ (ተጋድሎ ሓርነት ኤርትራ ) ስለነበር ክዚሁ ድርጅትም ቀደም ሲል ትንሽ እርጥባን ቢያገኝም እዚህ ግባ የሚባል አለመሆኑ ፤ የህ.ወ.ሓ.ት.ማፍያ አምራር ዘዴ አገኘ ፤ ጊዜው 1969 ዓ.ም. ።በዚሁ ወቅት የነብሩ አመራር ስማቸውን መግለፅ አስፈላኢ ነው ።
የነበሩ የህ.ወ.ሓ.ት. ከፍተኛ አመራሮች ፤
1ኛ አረጋዊ በርሄ (የደደቢት ስሙ በሪሁ በርሄ) ሃላፊነቱ ፤ የህ.ወ.ሓ.ት ሊቀ መንበርና የሰራዊቱ አዛዥ ፤የበላይ ሃላፊ
2ኛ ፋንታሁ ዘርአፅዮን (የደደቢት ስሙ ግደይ ዘርአፅዮን)ሃላፊነቱ፤ የህ.ወ.ሓ.ት.ም/ሊቀ መንበርና አስተዳደር የሓለዋ ወያኔ ሃላፊ
3ኛ አምባየ መስፍን ( የደደቢት ስሙ ሥዩም መስፍን ) ሃላፊነቱ ፤በአስተዳደርም በወታደራዊም ተባባሪ በኋላ የውጭጉዳይ ሃላፊ
4ኛ አምሃ ፀሃየ (የደደቢት ስሙ አባይ ፀሃየ )ሃላፊነቱ ፤ የፕሮፓጋንዳና ቅስቀሳ የህዝብ ግንኙነት ዋና ሃላፊ)
5ኛ ወልደስላሴ ነጋ ( የደደቢት ስብሓት ነጋ )ሃላፊነቱ ፤ የሓለዋ ወያኔና የግደይ ዘርአፅዮን ተባባሪ )
እነዚህ ክ1—5–ተጠቅሰው ያሉትን ፖሊት ቢሮ ሲሆኑ ድርጅቱን በሙሉ ሃላፊነት የሚመሩ ናቸው ።ፖሊሲ እቅዱች የሚያወጣሉ በተግባር ያስፈፅማሉ ፤ሁሉ ሥልጣን ጠቅልለው የያዙ ስለሆኑ ማንም ነገር በእነዚህ ተእዛዝ ተፈፃሚ ይደረጋል ።
ከላይ በተጠቀሱ ፖሊት ቢሮ በ1968 ዓ.ም.መጨረሻ ተመርጠው የመጡ ተለዋጭ ማእከላይ ኮሚቴ ፤
1ኛ ለገሠ ዜናዊ (የደደቢት ስሙ መለስ ዜናዊ ፟)ሃላፊነቱ ፤ የአባይ ፀሃይ ምክትል የፕሮፓጋንዳና ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ከዚሁ ጊዜ ጀምሮ ከአምስቱ ከፍተኛ አመራሮች በማንኛው ወሳኔ የማይለይ ።
2ኛ ወለስላሴ አብርሃ (የደደቢት ስሙ ስየ አብርሃ ) ሃላፊነቱ ፤የአረጋዊ በርሄ ተባባሪ
3ኛ ትኰእ ወልዱ (የደደቢት ስሙ አውዓሎም ወልዱ)ሃላፊነት ፤ በወቅቱ የህዝብ ግንኙነ ትተባባሪ አስተባባሪ
4ኛ አፅብሃ ዳኘው ( የደደቢት ስሙ ሸዊት ዳኘው )አልቆየም በ3 ወሩ ቆይታ ስብሃትን መለስ ዜናዊ ትእዛዝ በጥይት ተደብድቦ ከተረሸነ በኋላ ፤ ተተኪ ብለው ያመጡት ፤ራሰወርቅ ቀፀላ ( የደደቢት ስሙ አታክልት ቀፀላ )
የማእከላይ ኮሚቴ እንደያዘ ከ6 ወር ቆይታ በሳሞራ የኑስ እጅ ጎንባስ ሞሞና በተባለ ቦታ አስገደሉት ዋና መሪዎች ተባብረው ።
ለጥቅም ሲሉ የተ.ሓ.ህ.ት.(ህ.ወ.ሓ.ት.) መሪዎች በኢትዮጵያ ሉአላዊነት የፈፀሙት ሤራ።
ወያኔ በኢትዮጵያ ሏላዊነት፤ በኢትዮጵያ ህዝብ ያልፈፀመው በደል ያልፈፀመው ግፍ የለም ፤ከደደቢት ይዞት የመጣው ኢትዮጵያን ማውደምና ህዝብዋን መበታተን ወደ እርስ በራስ እልቂትና ደም መፋሰስ አሁንም ቀጥሎበታ ፤ይህች በምኒልክ ትናንትና የተፈጠረችው ኢትዮጵያ ይምትባል የአማራው (ኢትዮጵያ ) ግዛት ለወደፊቱ ሕብረተ ሰብአዋዊ ቅሳነት እንደማይኖራት ነው ይምናደርጋት ብለው ይተነሱ ወንጀለኛ ሽብርተኛ ህ.ወ.ሓ.ቶች ናቸው። የዛሬዋ ኢትዮጵያ እንያት የዛሬው የኢትዮጵያ ህዝብ ሁኔታ ተመልከቱ። ወደ ዋናው ሃሳቤ ላምራ ።
ጀብሃ ቀደም ብሎ የተፈጠረ ነው ፤ሻዕብያም ክጀብሃ በ1961ዓ.ም. እ. ኤ.አ. ተገንጥሎ ለብቻው የተደራጀ ድርጅት ነው።ገና ህ.ወ.ሓ.ት.ሳይደራጅ ደደቢት በረሃ ሳይወጣም፤ የባድሜ አካባቢ የኤርትራ ነው ፤ሳይሉ ባድሜ ረግጠዋት አያውቁም ነበር ።ረግጠዉት አያውቁም ብቻ ሳይሆን የባድሜ ወረዳዎች ሁሉ አያውቁትም ዓዲ ሃገራይ፤ሸላሎ፤ዓዲ ነብሬኢድ፤ዓዲ ፀፀር፤መንጠብጠብ፤እንዳጉሬዛ ፤ሞጉእ ፤ሱር፤ሰመማ፤መሬቶ፤ ወ.ዘ.ተ የጀብሃም ሆነ የሻዕብያ የራሳቸው ትግል ከጀመሩ ቦታው አያውቁቱም ።ባድመ ፤ባዳ፤ኢሮብ፤ዓሊቴና አያውቁትም ፤ዛላምበሳ ሞቅ ያለች ከተማ የዓዲግራት ወረዳ አንዳአንድ ነገር ለመግዛት ያውቋታል፤የትግራይ ኢትዮጵያ መሬት መሆኑም በሚገባ ያውቃሉ ።የኤርትራ መሬት ነው ብለውም በየአካባቢው ከሚኖረው ህዝብ የፈጠሩት ችግር አልታየም ፤አልተሰማም ፤ምክንያቱም የትግራይ ጠ/ግዛት ቦታ መሆኑ በተገቢ ሰለሚያውቁት ነው ። ተ.ሓ.ህ.ት.( የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት)ደደቢት ከገባም በኋላም ከሻዕብያም ሆነ ከጀበሃ የኛ ፤ የኤርትራ መሬት ነው ብለው የጠየቁበት ስንዝር የምታክል መሬት የለችም አልጠየቁም ስለ መሬት ይገባኛል አልተነሳም የሚያነስቡበት ምክንያት የላቸውም ።እስከ 1969ዓ.ም. ማለት ነው ። ወያኔ በዚሁ ጊዜ በብዙ ጠላት የተከበበ ነው ፤ ትጥቁ ትንሽ ኋላ ቀር ነው ፤መውጫ መዳኛ ይፈልጋል ሆነም ቀረም ያለው ግንኙነት ከሻዕብያ ብቻ ነበር ፤ከጀብሃም በመጠኑ ።
በዚሁ ወቅት 1969 ዓ.ም. አጋማሽ ወሩን አላስተውሰውም ። የህ.ወ.ሓ.ት. አመራር በድብቅ ተሰባስበው በትግራይ ህዝብ ከባድ ረቂቅ የክህደት ሤራ ፈፀሙ ፤የፈተሉት ሤራ ለሻዕብያና ጀብሃ በኤርትራ ዳር ደንበር የሚገኙ የትግራይ ጠ/ግዛት ከባድመ ባዳ አፋር የነሱም ስለሆነ ገብተው ህዝባቸው ያስተዳድሩ ብለው ፖሊት ቢሮው ወሰነ አምስቱም ተስማሙ ። በሁለት ተከፋፍለው ያዙት እቅድ ፤አራት የፖሊት ቢሮ አባላት ።ሁለቱ ወደ ሻዕብያ ፤ሁለቱ ወደ ጀብሃ ከፍተኛ አመራሮች ተጓዙ ፤በቆጦረው ቀንም ደረሱ ።የሁለቱም መልእክተኞች ማለት የህ.ወ.ሓ.ት.(በዚያን ጊዜ ስሙ ተ.ሓ.ህ.ት.) (ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ )ይዘዉት የሄዱት መለክት አንድ ነው ።መልእክቱ፤ከባድሜ አንስቶ እስከ ዓዲ ፀፀር ፤እንዳ ጉሬዛ ፤ከዛም ከእገላ እስከ አጋሜ (ዓዲግራት) አውራጃ፤ያሉ ወረዳዎች አብዛኛው ነዋሪው ህዝብ ኢርትራዊ ነው፤ ለምን እዛው ገብታቹህ ህዝባቹ አትመሩትም አታስተዳዱሩትም በተ.ሓ.ህ.ት.በኩል ሙሉ ፍላጎታችን መሆኑ እናረጋግጣለን ። ስለ መሬት ጥያቄ የሚነሳ ካለም በሌላ ጊዜ እንነጋገርበት አለን ። በማለት ቃል ገብተው ተመለሱ ። ጀብሃም ሆነ ሻዕብያ ይህን የደረሳቸው መለክት በይፋ ተናግረዋል ፤የኤርትራ ትግል ከየት ውዴት መለስ ዜናዊ በፃፈው መፀሓፍም ከዚህ አያይዞ በአደናጋሪ መልኩ ያስቀመጠው አለ ።በጀብሃ በኩል ያገኘው ምላሽ ፤ከደስታው ብዛት ፈነጩ (ወያኔ ) ወይን ሰማይ ላይ አወጥዋት ፤የተለያዩ ወታደራዊ ትጥቅ ፤ጥይት፤የእጅ ቦምብ ፤አነስተኛ ወታደራዊ መገናኛ ሬድዮ ፤በመጠኑም የፅሕፈት መሳሪም ወ.ዘ.ተ. ሰጡ ።በሻዕብያ በኩል ምን እንደተደረገ አይታወቅም ፤ምክንያቱም ወያኔ ህ.ወ.ሓ.ት. ከትግሉ መነሻ ጀምሮ እስከ መጨረሻው የሻዕብያ ጥገኛ (parasite) ስለሆነች ይህ ሰጡ ይህ አደረጉ ብለህ አታውቀውም ሁሌም የተለያዩ ንብረት ስለሚሉኩ ።ይህ ውሳኔ ከተደመደመ በኋላ በየቦታው እያናፋ የገባው ጀብሃ ነበር ። በ1969 ዓ. ም. የክረምት መግቢያ ጊዜ ወሩ ሰኔ ይመስለኛል ስለዘነጋሁት ይቅርታ ፤ የህ.ወ.ሓ.ት.ፖሊት ቢሮ አመራር ከላይ ስማቸው የተጠቀሱ አምስቱ 6ተኛው መለስ ዜናዊ<span lang=”AMH