በእስር ቤት በደል የፈፀሙበት 10 የፖሊስ አባላት በሕግ እንዲጠየቁለት ዮናስ ጋሻው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በፃፈው ደብዳቤ አመልክቷል።
———–
~”ወደ ማዕከላዊ ከገባሁ ጀምሮ በመርማሪዎች ዘግናኝ የሆነ ድብደባና ግርፋቶች፣ ስቅላት እንዲሁም ለመናገርና ለመስማት በሚከብድ ሁኔታ የሰብአዊ መብት ጥሰት ደርሶብኛል። ዛሬ አካሌ ጎድሎ እራሴን ችዬ መንቀሳቀስ የማልችል ሲሆን በዊልቸርና በክራንች ለመንቀሳቀስ ተገድጃለሁ።”
~”በማንነት ላይ መሰረት ያደረገ ስድብና ጥቃት፣ የስነ ልቦና ጫና ሆን ተብሎ አካሌንም እንዲጎድል ተደርጓል።”
ዮናስ ጋሻው
ቀን 12/10/2010 ዓም
ለኢፊዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር
ጉዳዩ:_ በማዕከላዊ የደረሰብኝን ጉዳይ ይመለከታል
እኔ ዮናስ ጋሻው ደመቀ የተባልኩ ግለሰብ በሽብር ወንጀል ተጠርጥሬ በቀን 4/5/2009 ዓም በማላውቃቸው ደሕንነቶች ከታሰርኩ በኋላ ወደ ማዕከላዊ ከገባሁ ጀምሮ በመርማሪዎች ዘግናኝ የሆነ ድብደባና ግርፋቶች፣ ስቅላት እንዲሁም ለመናገርና ለመስማት በሚከብድ ሁኔታ የሰብአዊ መብት ጥሰት ደርሶብኛል። ዛሬ አካሌ ጎድሎ እራሴን ችዬ መንቀሳቀስ የማልችል ሲሆን በዊልቸርና በክራንች ለመንቀሳቀስ ተገድጃለሁ።
በተጨማሪም የስነ ልቦና እና ሌሎች ሕመም ምክንያት የጤናዬ ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ተገቢ ህክምና ካለማግኜቴ በተጨማሪ ህክምናው ከማረሚያ ቤቱ አቅም በላይ ነው በመባሉ በቅዱስ ጳውሎስና ዘውዲቱ፣እንዲሁም ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንዲሁም የዓለም ቀይ መስቀል ክትትል በሚያደርጉበት ወቅት ህመሜ መባባሱ ተገልፆልኛል።
በማንነት ላይ መሰረት ያደረገ ስድብና ጥቃት፣ የስነ ልቦና ጫና ሆን ተብሎ አካሌንም እንዲጎድል ተደርጓል። መርማሪዎች በፈፀሙብኝ ድብደባ ምክንያ መንቀሳቀስ አልችልም። የጤናዬ ሁኔታም አሳሳቢ መሆኑ እገልፃለሁ። ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራና ቂሊንጦ በታሰርኩበት ወቅት በደል የፈፀሙብኝ:_
1) ኮማንደር ተክላይ መብርሃቱ
2) ምክትል ኮማንደር አሰፋ
3) ሱፐር ኢንተንደንት ኪዳነ አሰፋ (የቂሊንጦ ኃላፊ)
4) ረ/ኢ ጥጋቡ ሳሙኤል
5) አለማየሁ ካሳ
6) ጋሻው
7) ፅጌ (እቴነሽ)
8/ ረ/ኢ ቸርነት
9)ረ/ኢ ሰፊው ሕዝብ እንዳላማው
10) ረ/ኢ ወንደርጋቸው አማረ በሕግ እንዲጠየቁልኝ ስል በትህትና አመለክታለሁ
(ከጌታቸው ሽፈራው ገፅ የተገኘ)