በኢትዮጵያ እንዳይታዩ ታግደው የነበሩ 264 ድህረ-ገፆች መከፈታቸው ተገለጸ

በኢትዮጵያ እንዳይታዩ ታግደው የነበሩ 264 ድህረ-ገፆች መከፈታቸው ተገለጸ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በኢትዮጵያ እንዳይታዩ ታግደው የነበሩ 264 ድህረ-ገፆች መከፈታቸው ተነገረ። የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ  ባለፉት በርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ አንዳይታዩ ወይም አንዳይነበቡ አግዷቸው የነበሩ 264 ድህረ-ገፆች (Websites) እንዲሁም ኢሳትና ኦ ኤም ኤን (OMN) በዶክተር አብይ አስተዳደር መከፈታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል።

አቶ ፍፁም አያይዘውም ዜጎች ሀሳባቸውን በነፃነት መግለፅ መሰረታዊ የሰብዓዊ መብታቸው መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል።

ባለፉት በርካታ ዓመታት ስርዓቱን በመተቸት የሚናገሩና የሚፅፉ የሚዲያ ተቋማትን ለማፈን  ከፍተኛ ገንዘብ ወጭ እንደሚሆንና ጋዜጠኞችና ጦማሪያንም ሀሳባቸውን በመግለፃቸው ብቻ ሲታሰሩ መቆየታቸው ይታወቃል።

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) በአዲስ አበባ ከተማ ቢሮ ለመክፈት ዝግጅት እያደረገ መሆኑንም ምጮች ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY