/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በብርጋዴር ጀነራል ከማል ገልቹ የሚመራው የኦሮሚያ አንድነትና ነፃነት ግንባር ወደ ኢትዮጵያ የላከው የልዑካን ቡድን ዛሬ አዲስ አበባ መግባቱ ተገለጸ፡፡
በአቶ ተማም ባቲ የሚመራው ዘጠኝ አባላት ያሉት የልዑካን ቡድን ግንባሩ በሰላማዊ መንገድ ትግል ለማድረግ መወሰኑ ተከትሎ ከመግንስት ባለስልጣናት ጋር ውይይት ለማድረግ እንዳለመም ተገልጿል።
የልዑካን ቡድኑ ቦሌ አየር ማረፊያ ሲደርስም በመንግስት ኮሚዩኔኬሽን ጽ/ቤት አቀባበል እንደተደረገለት ታውቋል።ግንባሩ ከመንግስት ጋር ስምምነት በማድረግ በህጋዊ መንገድ ተመዝግቦ በሀገር ቤት ለመታገል መወሰኑን የልዑካን ቡድኑ መሪ አስታውቀዋል።
ብርጋዴር ከማል ገልጁ የመከላከያ ሰራዊት አዛዥ የነበሩ ሲሆን እ.ኤ.አ ከ2006 ጀምረው በኤርትራ አማጺ ቡድን አቋቁመው ሲመሩ መቆየታቸው ይታወሳል።