ከታሪክ መድረክ – ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ትላንትናና ዛሬ /ፕሮፍ. ኀይሌ ላሬቦ/

ከታሪክ መድረክ – ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ትላንትናና ዛሬ /ፕሮፍ. ኀይሌ ላሬቦ/

ጽሑፌን የኢትዮጵያ ጠቅላይ መሪ የነበሩት አቶ ኀይለማርያም ደሳለኝ ሥልጣናቸውንከመልቀቃቸው በፊት ከተናገሩት ልጀምር።

ይኸ መሥርያ ቤታችን ዐይነተኛ መረጃ አለን ወይ ውሳኔ ልንሰጥ የሚያስችልወቅታዊ የሆነ መረጃ አለን ወይ። እኔ ርግጠኛ ነኝ። አሁን በጠቅላይ ሚኒስቴርመሥርያ ቤት ውስጥ [ውሳኔ ሊያሰጥ የሚያስችል መረጃ] አለን ብዬ ለመናገርየሚያስችል አፍ የለኝም። ሰዎች በተናገሩት ላይ ተመሥርቼ ነው እየወሰንሁትያለሁት እንጂ በጣም ወቅታዊ የሆነ ታች ያለውን መረጃ አግኝቼ በዚያ ላይተመሥርቼ ውሳኔ እየሰጠሁ ነኝ ብዬ ለማለት አልችልም። እያንዳንዳችሁምእንደዚያ እንደሆናችሁ ርግጠኛ ሁኜ ለመናገር እችላለሁ። በመሥርያ ቤቱበምትሠሩት ሥራ በቂ መረጃ ወቅታዊ የሆነ መረጃ እንደዚሁም ደግሞየመረጃ ሥርዐት የተዘረጋበት ሁናቴ የለም።” (ጠቅላይ አስተዳዳሪ ኀይለማርያምደሳለኝ)

ከሺዘጠኝመቶስድሳዎቹ . . ጀምሮ በአገራችን የታየው ሁናቴ ይኸንን የጠቅላይመሪውን ንግግር ያንጸባርቃል ብል የተሳሳትሁ አይመስለኝም። ከዚያ ጊዜ ጀምሮአብዛኞቻችን ምንም ሳንመረምርና ሳንጠይቅ እንደማያከራክር እውነት አድርገንየተቀበልናቸው ብዙ ነገሮች አሉ።

የሺዘጠኝመቶስድሳዎቹ ተማሪዎች ባልተጨበጠናበምርምር ባልተደገፈ፣ ብዙም ስለአገራችን በቂ ዕውቀት በሌላቸው ባንዳንድምዕራባውያን ምሁራን መረጃዎች ጥራዘነጠቅነት የማይሻሉ አወናባጅ ጥናቶችምርምሮች በመመርኰዝ፣ ወይንም ምንም ባልተረዱት በነማርክስና ሌኒን ርእዮተዓለም ብቻ በመመሠረት፣ እጅግ ከሐቅ ወደራቀ ድምዳሜ ደርሰው አገሪቷን እከፍተኛጥፋት ላይ ለመጣል በቅተዋል።፡ በግለሰብ ደረጃ በዚህ መልክ የሚሠራ ሥራ እጅግያስነውራል። በአገር ደረጃ ከሆነ ደግሞ የሚያሳፍር ብቻ ሳይሆን፣ ከፍተኛ ምስቅልቅልናትርምስምስ ይፈጥራል።

የሺዘጠኝመቶስድሳዎቹ ተማሪዎች ወጣት ልጆች እንደመሆናቸው አእምሯቸውብስለትና ሚዛን በተነፈገ ከጫቅላነት ባልተላቀቀ የዕድሜ ጣራ ውስጥ ነበሩ። በጊዜያቸው ከፍተኛ ተሰሚነ ተቀባይነ ያለው በየአቅጣጫው ይነፍስየነበረውግራዘመም ርእዮተ ዓለም ሰለባ መሆናቸው አይገርምም ይሆናል ችግሩበሽምግልና ዘመናቸውም ያንኑ የተዛባና የተጣመመ አስተሳሰባቸው እንደማያከራክርእውነት አድርገው መውሰዳቸውና አለመታረማቸው ነው። አሁንም እንደድሮውየኢትዮጵያ ታሪክ ከመቶ ዓመት በላይ እንዳላለፈ ይተርታሉ፤ አገሪቷ ማኅበራዊአወቃቀር በበዝባዥና በተበዝባዥ በጨቋ በተጨቋኝ መከፋፈላቸውንአልተውም። አገሪቷ ተዳደር የነበረችውና የተመሠረተችውአብዛኞቹን ብሔረሰቦችጨቈኖ ይገዛ በነበረ ባንድ ብሔረሰብ ጉልበት ነው ብለው ማውራቱን እንደቀጠሉነው

ተማሪዎለጭቈናው መፍትሔ ብለው ያቀረቡት፣ ላገሪቷ ባዕድና ፋይዳቢስ የሆነ፣ግራዘመም ርእዮተ ዓለም ግድ በሕዝቡ ላይ እንዲጫን በመስበክ ነበረ። አጋጣሚምሆነና፣ የዘውዱን ሥርዐት ገርስሶ የተተካው ወታደራዊው የደርግ መንግሥት፣ጩኸታቸውን ምቶ ስብከታቸውን በዐዋጅ ኀይል በግብር ላይ ሊያውለው ሞከረ። ግንምንም ሳይሠራለት ቀረ ብቻ ሳይሆን፣ ከልክ በላይ እየተፋጠነ ይሄድ የነበረውን የአገሪቷንዕድገትና ልማት ወደመቶ ዓመት ወደኋላ ለመቀልበስ በቃ ደርግን ደምስሶ የመጣውአሁን በሥልጣን ያለው የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ዴሞክራሳዊ ግንባር [ኢሕአዴግ] በመባል የሚታወቀው በዳግማዊ ወያኔ የሚመራው አገዛዝ የተማሪዎቹን ኮቴና ፈርበመከተል የመጡት የጐሣ ታሪክ አቀንቃኞች ጥርቅም መሆኑ መረሳት የለበትም።ይኸም አገዛ በበኩሉ፣ በተማሪዎቹ እንቅስቃሴ ወቅት ይነዛ የነበረውን የጐሣ ሥርዐትአንግቦ ብቅ ያለው እንደግራዘመሞቹ ተማሪዎች ምንም ዐይነት ጥናትና ምርምርያልተደረገበት ታሪክ ሳይሆን ተረት በጥላቻ ላይ ተገነባየጠላና የቡና ቤት ወሬእንደማስረጃ አቅርቦ በጦር ኀይል በማሳመን ነው። ሱም ርእዮተ ዓለም ልክእንደደርጉ ከኢትዮጵያ ታሪክ የማይጣጣም የፈጠራ ተረት እንደመሆኑ፣ ሥርዐቱበየቦታው እየተመታና ፍርስርሱ እየወጣ እንደሆነአሁን ጊዜ ሁላችንም እያየን ያለነውሐቅ ነው። ርግ የኢትዮጵያን ዕድገት በመቶ ዓመት ወደኋላ ሲቀለብስ ኢሕአዴግደግሞ አንድነቷን በመቦርቦርና በማዳከም ወሰኗንና ልዑላዊነቷን በማስደፈር ታሪኳንበማስነወር ንነቷን በመናድ፣ ከስድስት በላይ ዓመታት በጋብቻና በአምቻበመተሳሰር፣ በባሕልና በቋንቋ በመወራረስ፣ በፍቅርና በመልካም ጉርብትና የኖረውንሕዝብ፣ባሰኘው መልክ በፈጠረው ክልል አደራጅቶ፣ ርስበርስ በማጋጨትና በመከፋፈልበማጣላትና በማጥላላት ከወታደራዊ መንግሥት ከፋ ሁናቴ ቢያንስ በሦስትናበዐራት መቶ ያህል ዓመታት ወደኋላ መልሷ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ ግፍና ወንጀልፈጽሟል ማለት ይቻላል።

የዛሬው ጽሑፌ ዋና ትኩረት ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ምንድር ነው በሚለው ላይነው። አንድ ሕዝብ ማንነቱን ካላወቀ ነፍሱን እንደሳተ ግለሰብ ነው። የሁሉምሣለቂያ፣ መዘባቻ ይሆናል። ከየት እንደመጣ፣ ለምንስ ባለበት እንዳለ ትስእንደሚሄድ ይጠፋበታል። ለኔ ታሪኩን የማያውቅ ሕዝብ የጉዞን መነሻና መድረሻእንደማያውቅ በባሕር ላይ እንደተንሳፈፈ መርከብ ነው። በየጊዜው ሚነሣውማዕበልና ነፋስ እየተመታ የመስ ወይንም የመዘረፍ መጥፋት ዕድሉ ከፍተኛነው። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን እንደአገርና ሕዝብ ማንና ምን እንደነበሩ ማወቅአሁንም ያሉበትን ሁናቴ መገንዘብ ብቻ ሳይሆን የወደፊቱንም አገሪቷንም ሆነየመጪውን ታሪክ ተረካቢ ትውልድ ዕጣና ዕድል በትክክል ለመተለም ይረዳል። ከዚያምአልፎ ያላቸውን ብሔራዊ የተፈጥሮ ሀብትና ቅድመ አያቶች የኪነጥበብ ቅርስ፣በደምብ አድርገው ተረድተው የራሳቸው የታሪክ ድርሻ ምን መሆን እንደሚገባው፣ከሌላውስ ምንና ምንስ ያህል መዋስና አለመዋስ እንዳለባቸው ጥርት አድርገውእንዲያውቁ ያግዛል።

ጽሑፌ አለቅጥ ረጅም ቢሆንም፣ ውድ አንባቢዬ በትዕግሥትና በርጋታእስከመጨረሻው ከማንበብ እንደማቦዝኑ ርግጠኛ ነኝ። ካልሆነም ተስፋ አደርጋለሁ።ንግግሬ፣ጀመርያ ደረጃ የውጭ አገር ጸሓፊዎች ካላቸው ዕይታ በመነሣትእነሱስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ያሉትን፣ አንዲሁም ኢዮጵያም ለውጭ አገሮችያበረከተችውን አስተዋፅዖ ኛል። ቀጥሎም ነዚህን ገለጻና አስተያየት፣በአገር ውስጥከነበሩት ሁናቴዎችና ከተፈጸሙት ድርጊቶች ጋር በማነፃፀር ያገናዝባል። ከዚያም፣እንዴትአሁን ወዳለንበት ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውነትን ወደመሸራረፍና ወደመሰርሰር ሁናቴእንደመጣን በአጭሩ ተመልክቶ ይደመድማል።

እስከቅርብ ጊዜ ድረስ የኢትዮጵያን ታሪክ ማኳሰስ፣ መሬቷን ማንቋሸሽ፣ ምንነቷን መካድእንደሙያቸው አድርገው በየቦታው የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችና ድርጅቶች እየተራቡናእየበረከቱ ነበሩ ሊባል ይቻላል። እነሱ የሚነጋገሩባት ኢትዮጵያን የሚደግፉ መዛግብግን የትም በኩል፣ በምንም መልክና ደረጃ እስካሁን ድረስ ብቅ አላሉም። ወደፊትምይገኛሉ ብዬ ከቶውኑ አላምንም። በውጭ አገር ጸሓፊዎች ስለኢትዮጵያ ብዙ ተብሏል።ግን ከጥንት ጀምሮ ተደጋግሞ የሚነሣ ነገር ቢኖር አገሪቷ እጅግ በጣም ጥንታዊት፣ነፃነቷንና ልዑልናዊነቷን ጠብቃ የኖረች ረጅምና አስደናቂ ታሪክ ያላት፣ በመሬቷአቀማመጥና ሀብት አስቀኚ መሆኗ ነው። ስለሕዝቧ ደግነትና ልበሰፊነት፣ ሕግአክባሪነትና ጀብዱነትመንፈሳዊነትና ታታነት፣ ስለገዢዎቿ ፍትሕና ርትዕ ወዳድነትእንዲሁም ነገሥታቱ ቅንነታቸው የሚደነቁ፣ ስለአገራቸው ጥበቃ ለሕዝባቸውደኅንንት ከማንም ጋር ማይደራደሩ ስለመሆናቸው በሰፊው ይነገራል።

ከጥንት ጀምሮ ከሚነገሩት ዋኖቹ ነገሮች መካከ ዋናው የኢትዮጵያውያን ታላቁክብራቸውና ኩራታቸው በባዕድ ቀንበር አለመውደቃቸው ነው። ግን ይኸ ብቻአይደለም። ራሳቸውን የሥልጣኔ ሁሉ ምንጭ አድርገው የሚያስቡ መሆናቸውንምይጨምራል ሌላው ቀርቶ ዓለም እየተደነበት ያለው የግብጾች ሥልጣኔ ባለቤቶች፣የኢትዮጵያውያን ዝርያ መሆኑን አይደብቁም። በአንደኛ ዘመነ ዓለም የነበረ ዲዮዶሩስሲኩሉስ የተባለ የጽርዕ ታሪክ ጸሓፊ ይኸንን የኢትዮጵያውያንን ጥልቅ የጋራ ስሜትእንዲህ ሲል ይገልጣል።

የታሪክ ሰዎች እንደሚነግሩን ከሆነ፣ ኢትዮጵያውያን ከሰው ሁሉ የመጀመርያዎቹናቸው። ስለዚህ ያለው ማስረጃ ግልጥ ነው ይላሉ። አሁን ወደሚኖሩበት ምድርየመጡት፣ እንደሌላው መጤ ሁሉ ከውጭ አይደለም፤ ታዲያ በመሠረቱ የአገሩተወላጆች ናቸው። ሰው ሁሉ እንደሚስ  ባላገሮች በሚል ትክክል በሆነመጠርያ የሚጠሩት ከዚህ የተነሣ ነው። ሌላው ደግሞ ግብጾችበኢትዮጵያውያን የተላኩ ሰፋሪዎች ናቸው፤ አብዛኛው የግብፅ ባህል የኢትዮጵያእንደሆነና፣ ሰፋሪዎቹ አሁንም ቢሆን የጥንት ልማዳቸውን እንዳልተው ነው ይላሉ።ከዚህ በተጨማሪ [ኢትዮጵያውያን] ስለራሳቸው ጥንታዊነትም ሆነ ስለላኳቸውስለሰፋሪዎቹ ግብጾች የሚናገሩት እጅግ ብዙ ነገር አለ።

ሁላችንም እንደምናውቀው የማንኛውም ሥልጣኔ መሠረቱ ሃይማኖት ነው።አማልክቶቹን ለማስደሰት ሲልየሰው ልጅ ለሰማው የሚያስገርም ላየው የሚያስደምምወደሰማይ የመጠቁ፣ ወደምድር የጠለቁ ሥራዎች ሠርቷል። የግብጾቹ ፕራሚዶች፣የክርስቲያኖቹ ካቴድራሎች፣ የእስላሞቹ ደማም መስጊዶች፣ የአይሁዶቹ አስቅኚምኩራቦች፣ ንዶቹ አስደናቂ ቤተመቅደሶች፣ የላሊበላ ካንድ ለት የተፈለፈሉ ግሩምድንቅ የሆኑ ቤተክርስቲያኖች የሃይማኖት ፍሬ መሆናቸው አይካድም። ሃይማኖትንመጀመርያ የጠነሰሰው ሰውም ይሁን ሕዝብ የሥልጣኔ ሁሉ ምንጭና መሠረት ነውቢባል የሚያከራክር አይመስለኝም። ታዲያ እንዲህ የመሰለ በአሳብ የተራቀቀበአእምሮው የመጠቀ ሕዝብ የትኛው ነበር ብንልዲዮዶሩስ መልሱን በጊዜውካገኛቸው የኢትዮጵያውያን አፍ ነጠቅ አድርጎእንዲህ ሲል ያሰማናል።

ኢትዮጵያውያን የሰው ልጅ አማልክትን እንዴት መወደስበመሥዋዕትዑደትናበዓላት እንደዚሁም ሌላውም ሥነሥርዐት እንዴት ማመስገን እንደሚገባውበመማር መጀመርያዎቹ እነሱ እንደነበሩ ይናገራሉ። ከዚህም የተነሣመንሳፈዊነታቸው በሁሉም የውጭ አገር ሰው ዘንድ ይታወቃል፤ሰማይን እጅግበጣም አድር የሚያስደስተው ኢትዮጵያዉኖች የሚያቀርቡት መሥዋዕ ብቻእንደሆ በሁሉም ዘንድ ይታመናል ለዚህም በምስክርነት የሚጠሩት በግሪኮችዘንድ ምናልባት እጅግ ጥንታዊ የሆነው በርግጥ ከፍተኛ አክብሮት ያተረፈውንባለቅኔውን [ሆሜርን]ነው ምክንያቱም እሱ በኢሊያድ [መጽሐፉ] ውስጥ፣ዜውስና አብረዉት የነበሩት አማልክት ለምን ሊገኙ እንዳልቻሉ ሲገልጥ፣ኢትዮጵያውያን በየዓመቱ ለአማልክ ሁሉ ባንድጋ ሚያቀርቡት መሥዋዕትናድግስ ሊሳተፉ ብለው ደኢትዮጵያ በመሄዳቸው ነው ይላል [ስለነፃነታቸውምሲያብራሩ] ለአማልክት ካላቸው መንፈሳዊነት የተነሣ ፊታቸው ሞገስ ስላገኙከውጭ መጣ ወራሪ ተገዝተ እንደማያውቁ ይናገራሉ

በዲዮዶሩስ አባባል ኢትዮጵያ የሁሉም ሥልጣኔ ምንጭ ናት። ኢትዮጵያውያን ደግሞእንደቀረው የሌላው ዓለም ነዋሪ ሕዝብ ውጭ ፈልሰው ያልመጡ፣ ታዲያ ያገራቸውየመጀመርያዎቹ ሰፋሪዎችና ባላባቶች በባዕድ ተገዝተው የማያውቁ ነፃና ኩሩሕዝብ ናቸው።

ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ የሚነሣው ጥያቄ እንደዲዮዶሩስ የመሳሰሉት ይልቁንም የጥንትጸሓፊዎች ኢትዮጵያ የሚሉት አገር ከአሁኗ ኢትዮጵያ ጋር ምንም ዐይነት ግንኙነትየለውም፤ በፍጹም ልዩ አገር ነው የሚል ነው። ዲዮዶሩስም ሆነ ከእሱ በፊትና በስተኋላስለአካባቢው ጻፉት ውጭ አገር ደራስያን ገለ መሠረት፣ ከጊዜ ወደጊዜ ቈዳዋ ይሰፋወይንም ይጠ ይሆናል እንጂ፣ አገሪቷ ግን ከሞላ ጐደል ዛሬም ያንኑ ስም ይዛየምትገኘው ኢትዮጵያ መሆኗን ነው የሚያረጋግጡት። ዲዮዶሩስ ራሱ ስለ ኢትዮጵያመልክአ ምድር ሲናገር፣ የዐባይ ወንዝ የሚመነጭበት፣ አስደናቂ ሐይቅ የሚገኝበት፣በጣም ተራራማና ለየት ያለ የዝናም ወራ ለበት ምድር ነው ይላል። ጥቂት ቈይተንወደዐራተኛ ዘመነምሕረት መኻል ስንመጣ ደግሞ፣ ከሮማው ቄሳር ወደአክሱምየተላኩት አቡነ ቴዎፍሎስዮስ እንዱስዩስ የተባሉ ጳጳስከዐረብ አገር ቀጥለው እንደሄዱ ቦታውን ሲገልጡ ራሳቸውን ኢትዮጵያውያን ብለው ወደሚጠሩትወደአክሱሞች[3] ዘንድ እንደሆነ ያብራራሉ። እንግዴህ አክሱሞች ራሳቸውንየሚጠሩት ኢትዮጵያውን ነን በማለት ከሆነ፣ ጥንት ኢትዮጵያ ተብሎ የሚጠራ አገርከአሁኑ የተለየ ነበር የሚለው አስተያየት ውሃ አይቋጥርም። በሦስተኛ ዘመነምሕረት ላይየኖረው ዕው የፋርስ ተወላጅ ማኒ (216-276)በዓለም ከታወቁት አራቱ ታላላቅመንግሥታት ናቸው በማለት ከሚዘረዝራቸው ከፋርሶች ሮማውያን ቀጥሎሦስተኛውን ቦታ የያዘው፣ ነዚህ ራሳቸውን ኢትዮጵያውያን ብለው የሚጠሩትየአክሱማውያን መንግሥት ነው ይላል እንዲሁም ከዘውድ ቅርፅነቱ የተነሣ የአዱሊስዙፋን በመባል ሚታወቀው ሦስተኛ ዘመነምሕረት ላይ ባንድ ስሙ ባልታወቀ ንጉሥእንደተሠራ ሚገመተው መታሰቢያ ሐውልት፣አክሱም በጊዜዋ መናገሻ ከተማነትአልፋ፣ አብዛኞቹን ዛሬዎቹን የኢትዮጵያ ግዛቶች በምሥራቅ እስከኬንያጠረፍ፣ከዚያም ቀይ ባሕር አልፋ የመንንና ደቡብ ዐረብን በሰሜን ደግሞ እስከግብጽወሰን ድረስ ትቈጣጠር እንደነበረች ይነግረናል

ዲዮዶሩስ ስለኢትዮጵያ የሚናገረው በዘመኑ የነበረውን ሐቅ እንጂ ፈጥሮ አይደለም።ከሱ በፊት ወደሦስት መቶ ዘመን አስቀድሞ ግብጽን አገር ዙሮ ያየውና፣ምዕራባውያን ዘንድ የመጀመርያው የታሪክ ጸሓፊ ወይንምየታሪክ አባትበመባልየሚታወቀው፣ ጽርኣዊው ሄሮዶቱስየዲዮዶሩስን ምስክርነት ያጸናል። ለምሳሌያህልሄሮዶቱስ ከግዝረት ጋር አያይዞ ስለግብጾችና ስለኢትዮጵያውያን ሲናገር፣ግብጾችየግዝረትን ልማድ የወረሱትቅድመ አያቶቻችን ናቸውከሚሏቸው ከኢትዮጵያውያንሲሆን፣ ሌላው ዓለም ግን ነሱ ኮርጆ ነውሲል ይገልጻል። በዚህም የኢትዮጵያንጥንታዊነትን ብቻ ሳይሆን ባህላቸው እንዴት ወደቀሪው ዓለም እንደተዛመተ፣ በዓለምወደር የሌለውን ሥልጣኔ ፈጠሩ የሚባሉት ግብጾች ራሳቸው የኢትዮጵውያን የልጅልጆቻቸው መሆናቸውን ያመለታል።

በውጭ አገር ኢትዮጵያ የሚትታየው የዓለምን ሥልጣኔ ቀያሽ በመሆኗ በማንምየውጭ ኀይል ባለመገዛቷ ብቻ አይደለም በዘመኑ ከነበሩት አገሮች ተግባርና ከሰዎችእምነት አንጻር ስንመለከት፣ ካገሩ ለተሰደደው መሸሻውና መጠጊያው፣ በጭቈና ቀንበርሥር እየማቀቁ ላሉት አማራጭ ኀይል፣ የነፃነታቸው ተስፋ፣ የችግራቸው ማስረሻምማስታገሻ ሁና ትታያለች። ከአገራቸው የተሰደዱትን ተቀብላ በክብር በማስተናገድ፣ከባህሏ ጋር አዋሕዳቸው ለከፍተኛ ማዕርግና ክብር የበቁት እጅግ ብዙ ናቸው። ይኸምሁናቴ ከጥንት ተስዐቱ ቅዱሳን ከተባሉት የክርስትና ሃይማኖት አባቶች ጀምሮእስከቅርብ ጊዜ ድረስ በዘመናችን ሲፈጸም የታየ የማይካድ ሐቀኛ ታሪክ ነው።በስደተኝነት የመጣው ሰው፣ ባህሉንና እምነቱን እንዲቀይር አልተገደደም። ይልቅስባለው ሙያና ዕውቀት አገሪቷን እንዲያገለግል መድረኩ ስለተመቻቸ፣ በኢትዮጵያግንባታና ነፃነት አሻራውን ያልተወ የውጭ አገር ሰፋሪ የለም ማለት ይቻላል። ዘጠኙቅዱሳን ከሮማውያን ግዛት ሸሽተው መጥተው ሪቷን ክርስትናን እምነትከማጠንከር አልፈው፣ አሁን ናደንቃቸውን ታሪካዊ ቅርሶች ሠርተው ትተደዋ በወቅቱ ብሔራዊ ቋንቋ የነበረውን ግእዝ ለሥነ ጽሑፍነት አብቅተውትአዳብረውታል። የክርስትና እምነት ደምድሪቷ ያስገቡት አቡነ ሰላማ ከሣቴብርሃንበመባል የሚታወቁት ወጣቱ ፍሬምናጦስ ራሳቸው የትውልድ አገራቸው ተብሎከሚገመተው ከሶርያ ወደህንድ ሲጓዙ፣ መርከባቸው ባቸው መጠለያ ሰጥበእንክብካቤ አሳድ ታላ ክብርና ርግ ያበቃቸው ኢትዮጵያ ናት። እንዲሁምበግራኝ ወረራ ወቅትብዙ መጻሕፍት ወደግእዝ በመተርጐምም ሆነ የክርስትናንእምነት በማጠናከር ከፍተኛ ሚና የተጫወቱት፣ የመናዊው እስላም ነጋዴ የበስተኋላውየደብረሊባኖስ ዕጨጌ አባ ዕንባቆም ሌላ ጥሩ ምሳሌ ናቸው። ኢትዮጵያ በዘመናችንምቢሆን ከፍተኛ ሰብኣዊነት የመላበትንና፣ ሳያቋርጥ በታሪክ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውንለጋሥነቷን እንደተጐናፀፈች ናት። ባገራቸው ክፉ ግድያና ጭፍጨፋ ርሶባቸውበስደት ወደአገራችን የመጡት አርመኖች በተለያየ የልማት ዘርፍ በመሰማራትለኢትዮጵያ የዘመናዊነት ግንባታ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንዳበረከቱ፣ ሁላችንም እናውቀዋለን ብዬ ስለምገምት ልገፋበት አልፈልግም። በገዛ ራሳቸው ምርጫኢትዮጵያን እንደእናት አገራቸው ተቀብለውዋት ለኖሩትም መልካም መስተንግዶአልተነፈገም። እነሱም ምንም ዐይነት አድልዎ ሳይደረግባቸው ለከፍተኛ ሹመትናማዕርግ በቅተ በተለያየ ዘርፍ ተሰማርተው በሥነጽሑፍና በሌላም የእምነት ሆነየፖሊትካ መስክ ከፍተኛ ሚና እንደተጫወቱ ከላይ የተጠቀሱት ምሳሌዎች ማስረጃናቸው።

ከላይ እንዳልሁት፣ በዚህ ረጅም ስደተኞች ማስተናገድና ጥገኝነት በመስጠት ታሪክ፣ወደኢትዮጵያ ሲደርስ፣ ማንም በእምነቱና በትውልዱ ምክንያት አድልዎ የተደረገበትጊዜና ሁናቴ ያለ አይመስለኝም። ነቢዩ ሙሐመድ ያገራቸው ባለሥልጣናትና ሕዝብበአዲሱ ሃይማኖታቸው ምክንያት ያሠቃዩአቸውና ዕረፍት ቢነሧቸው፣ባልንጀሮቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ያሸሹት ወደኢትዮጵያ እንጂ ወደሌላ አገርአልነበረም። በላኳቸውም ጊዜ ስለኢትዮጵያና ሕዝቧ እንዲሁም ስለገዢዋ የተናገሩት፣ከሳቸው በፊትም ሆነ በኋላ የመጡት በተከታታይ አለማቋረጥ ያስተጋቡትን ድምፅ ነው።ነቢዩ እግዜር ለችግራቸው እልባት እስከሚሰጥ ድረስ ተከታዮቻቸውን ወደኢትዮጵያእንዲሄዱ ሲመክሯቸው፣ የሰጡት ምክንያ አገሩ ሰው ወዳድ ነው፤ ንጉሡም ምንምዐይነት ግፍ የማይታገሥ ሕዝቡን ለማንም ሳያዳላ ሰላምና ፍትሕ የሚገዛ ስለሆነወደኢትዮጵያ ብትሄዱ እዚህ ከሚደርሳባችሁ ችግር ታመልጣላችሁ የሚል ነበርባልንጀሮቻቸው ደግሞ በአካባቢው ካሉት ኀያላን ከተባሉት እንደሮማዊው (ጽርኡ)ፋርሱ ከመሳስሉት መንግሥታት መካከል ሁሉ ኢትዮጵያን ነጥለው የመረጡበትናደስብሏቸው ወደዚያ የሄዱት፣ሐራጥቃነትን ፈርተው ወደእግዚአብሔር ሊሸሹሲሉ ነበር ይላል። እንግዴህሐራጥቃነትን ፈርተውየሚለው ቃል ሊሰመርበት ይገባልበነቢዩ ባልንጀሮች ቤተሰቦች አስተያየት፣ እምነታቸውን ለመካድ ሳይገደዱ፣ ወይንምበመናፍቅነት ሳይከሰሱቀረው ኅብረተሰብ ሳይገለሉ፣ ፈጣሪያቸውን ሊያመልኩየሚችሉበት አገርኢትዮጵያብቻ እንደሆነች ነው የምንረዳው። እነሱም እንደዚህዐይነት ንግግር እያሰሙ ያሉት፣ የኢትዮጵያ ነገሥታ ክርስትና እምነት የአገሪቱመንግሥት ዋና ሃይማኖት መሆኑን ለዓለም በይፋ ካስታወቁ ወደሦስት መቶ ዓመአስቈጥሮ ቈየበት ወቅት ነው። ነቢዩ መሐመድና ደቀመዛሙርቶቻቸውምስክርነትከጥንት ጀምሮ ስለኢትዮጵያና ስለኢትዮጵያውያን ይነገር የነበረውን ጥልቅእምነት ደግመው ከማስተጋባት አልፈው፣ በማያወላውል መንገድ ያጠናክሩታል።

አስተያየታቸው ስምንት መቶ ዘመነዓለም ጀምሮ በታወቁ ጥንት የቀለም ሰዎችይነገር ነበረበምንም መልኩ የተለየ አልነበረም እንግዴህ፣ ስመጥ የጽርዕ ባለቅኔሆመር ሆነ፣የታሪክ አባትሄሮዶቱስ የተውልን ማስረጃዎች ከዚህ በላይእንዳየናቸ የኢትዮጵያን ታላቅነት ብቻ ሳይሆን ልክ ነቢዩ መሐመድ አንዳሉትሕዝቧ ደግ ተወዳጅ፣ ኑሮው ባህሉና ሥርዐቱ በፍትሕ ላይ የተመሠረመሆናቸውን አጥብቀው ነው የሚመሰክሩት

ኢትዮጵያ እንደአብዛኞቹ አገሮች በታሪኳ ባላቋረጠ ጦርነት ተዘፍቃ የኖረች አገርሲትሆን፣ በአውሮጳና በሌሎች አገሮች እንደታየ ሁሉ በሃይማኖት ላይ ብቻ የተመሠረተጦርነት ግን አልተካሄደም ማለት ይቻላል። በኢትዮጵያ ታሪክሃይማኖት የግልአገርየወልየሚለው አባባል ዛሬ የተጠነሰሰ ሳይሆን ዘመናት ያስቈጠረ ነው ቢባል ስሕተትአይመስለኝም። ብዙውን ጊዜ እንደሃይማኖት ጦርነት ሁኖ የሚጠቀሰው [ንጉሥ] ግራኝበመባል በሚታወቁት፣ በእስላሙ ኢማም አሕመድ ቤንኢብራሂም አልጋዚናበክርስቲያኑ አፄ ልብነድንግል ከዚያም ቀጥሎም በልጃቸው በአፄ ገላውዴዎስ መካከልየተካሄዱት ውጊያዎች ናቸው እነዚህ ግጭቶች ግን በመሠረቱ የሃይማኖት እንዳልሆየሚያመለክ ብዙ ማስረጃዎች አሉ።

በመጀመርያ ደረጃ፣ ንጉሥ ግራኝ ወደጦርነት ሊያመሩ የበቁት አባቴ ሞተብለው አፄልብነድንግልን ቢያረዷቸው ሹመትህን አጽድቄልሃለሁ ግብሬን ገብየሚለውየንጉሠ ነገሥቱ ትእዛዝ ቢደርስባቸው የለም አልገብርም ብለው በጉልበታቸውተማምነው በር ዕድሉም ቀንቶላቸው ለድል በቁ ይሁንና በእስልምና እምነታቸውቀስቅሰው ስላም ስለሆንሁ ለክርስቲያን ንጉሥ ግብር አልገብርም ብለውእንዳልሆነ ግልጥ ነው። ለጦርነቶቹ ሃይማኖት ተገን እንጂ መነሻውና መሠረቱ መላውንኢትዮጵያን እኔ ብቻዬን እገዛለሁየሚለው ኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የተለመደውሥር የሰደደው የሥልጣን ሽኩቻ ነው።

በሁለተኛ ደረጃ፣ ግራኝን የተዋጉት ዘልማድ የክርስቲያን ግዛቶች ነበሩ የተባሉት ብቻልነበሩም። የእስልምና እምነት የሰፈነባቸው እንደሐረር፣ ባሌና አሩሲ፣ እንዲሁምሐድያና ጉራጌ የመሳሰሉ ግዛቶችም ጭምር በጀግንነት ተዋግተዋቸዋል። ግራኝራሳቸው የንጉሥነትን ሥልጣን የጨበጡት እስላሞች የነበሩ ዐምስቱ የአዳልነገዶች ኀይላቸውን ስላልቻሉትና በጦር ሜዳ ድል ተመቱ በኋላ ነው። ይኸምመነሻቸው ለሥልጣን እንጂ በሃይማኖት ቅናት እንዳልሆነ ይበልጥ ያስረዳናል።

በሦስተኛ ደረጃ፣ ከግራኝ በፊት ወደሁለት መቶ ዓመት አስቀድመው የነገሡትናበተደጋጋሚ ከእስላም ንጉሥ ጋር የተዋጉት ታላቁ ዐምጽዮን [1314-1334]በኢትዮጵያውስጥ የሚኖረው የመላው እስላም ንጉሥ እኔ እያለሁ ራሱን የእስላም ንጉሥ ነኝብሎ ሾመ ብለው ይከሱታል ወቅቱ ታሪክ ሓፊ ንግግር መሠረት የእስላሞቹምንጉሥ ምኞት የክርስቲያኑን ንጉሥ መንግሥ ወርሼ አገሬ ገውና ጫትእተክልበታለሁ የከብቱንም ጠባቂዎች ግመ ኞች እለውጣቸዋለሁየሚል ነበር ስለዚህ ክርስቲያኑ ንጉሠነሥት ሆነ እስላሙ አገር ንጉሥ ጠባቸውየመላዋኢትዮጵያ ንጉሥ ለመሆንሥልጣን እንጂ ሃይማኖትን ያማከለ ትግልእንዳልነበር ያመለክታል። እንግዴህ በየጊዜው በክርስቲያኑና በእስላሙ፣ እንዲሁም በኋላበተመሳሳይ ደረጃ መልክ ክርስቲያኑና ፈላሻው መካከል ይካሄዱ የነበሩት ውጊያዎችጠባይ፣ ከመላ ጐደል ሃይማኖት በማስታከክና በማሳበብ ይካሄ የነበ የሥልጣንጦርነቶች እንጂ በእምነት ላይ የተሠረ ግጭ እንልነበሩ ይመሰክራል። ሁኖምከነዚህ ጦርነቶች መታወቅ የሚገባ አንድ በጣም ጠቃሚ ፍሬ ነገር አለ። ተፈላሚዎቹበሃይማኖት በማሳበብ መላዋን ኢትዮጵያን ለመግዛትና ለመቈጣጠር ሲጥሩልባቸውን ሲዳዳው አንዴም እንኳ የዳሩ አገር ከመኻሉ ለመገንጠል ሲል ጦርነትያካሄደበት ጊዜ ሁናቴ እስከቅርብ ወቅት በታሪክ አልታየም

ብዙዎች፣ አንዳንድ ታሪክ ጸሓፊዎችንም ጭምር፣ኢትዮጵያን ከክርስቲያን እምነት ጋርአጣምረው የሚያዩ አሉ። እኔም ራሴ ገና በታሪክ ምርምር ዓለም ዳዴ እያልሁበነበርሁበት ወቅት፣ ባንዳንድ ምዕራባውያን ጽሑፎች ላይ በመመርኰዝ፣ ይኸንኑ አሳብተጋርቼ በተደጋጋሚ ያስተጋባሁበት ወቅት ነበር። ዛሬ ግንከፍተኛ ስሕተት መሆኑንመረዳት ብቻ ሳይሆን፣ታሪካችን የተጻፈበትን ቋንቋ መናገር ይቅርና፣ማንበብ እንኳየማይችሉ፣ ምርምራቸውን ብዙውን ጊዜ በአስተርጓሚ ያካሄዱት፣ የውጭ አገርበተለይም ምዕራባውያን ጸሓፊዎች አሳባችንን ገና በጫቅላነታችን ሳለንእንደሚመርዙ ለመገንዘብ ችዬአለሁ። ኢትዮጵያ የክርስቲያኑ ክፍል የበላይነትይዝም ነዋሪዎቿ ግን የተለያየ እምነትና ባህል ቸው።ለቲካውም ሆነ ሃይማኖቱሕዝቧን ርስበርስ ከመጋባት አላቆቸውም። የዚህ ጥሩ ምሳሌ፣የእስልምና እምነትተከታዮች የሆኑት የአዳሎቹና የሐድያዎቹ ባላባቶች ክርስቲያኖቹን ሴቶች አሰልመውሲያገቡ፣ የክርቲያኖቹ መሪዎች ሚስቶቻቸው በበኩላቸው እስላሞቹ ባላባቶችሴቶች ልጆች እንደነበሩ ማየቱ ይበቃል። ከዚያም ባሻገር በዘመነመሳፍንትየክርስቲያኑን መንግሥት በእንደራሴነት ይገዙ የነበሩት የየጁ ወረሼኮች እስላሞቹንሴቶች እያከረስተኑ ሲያገቡ የአብዛኞቹ ጐረቤቶቻቸው የወሎዎቹሐመዶችሚስቶቻቸው የሰለሙ ክርስቲያኖች ነበሩ ማለት ይቻላል። ሁናቴውየሚያሳየን በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደጊዜ ሃይማኖት ሽፋን የተካሄደ ግጭት ነበረ ቢባልምእንኳን፣ ያንዳንዱ ሃይማኖት ባህል በሌላው መወሳሰቡንና መሰበጣጠሩን ነው

መጪውን አለአድልዎ አስተናግዶ ወግና ለማዕርግ ከማብቃት ባላነሰ መልክ ደግሞኢትዮጵያ እንደረቂቅ መንፈስና አሳብ ሁና ያገለገለችበትም ሁናቴና ወቅት አለ።ባጭሩ ሁለት ምሳሌዎችን ልጠቅስና ላብራራ እፈልጋለሁ።

አንደኛ የነቢዩ መሐመድ ተከታዮች ጉልበት አግኝተው፣ ዓለምን በጦር ኀይላቸውባንቀጠቀጡበት ወቅትበክርትስና እምነታቸው የሞራልና የሥልጣን አምባገነንነትይሰማቸው የነበሩትን አውሮጳውያንን ይመለከታል። ጥምቀተ ክርስትና ምርጥየእግዚአብሔር ልጆች በመደረጋችን፣ የመንግሥተሰማያት ወራሾች እኛ ብቻ ነን እያሉይደነፉ የነበሩት አውሮጳውያን፣ በኢየሩሳሌም ቅዱሳት መካናትን የነጠቀባቸውን፣የሜዲቴራኒያንም ባሕር በመቈጣጠር እንቅስቃሴቸያውን የገታውን፣ የእስላሞችንኀይል በምንም መልክ ማንበርከክ ሲያቅታቸው፣ አዳኛችን ብለው የጠነሰሱት ፕርስቴርጆን የሚሉት በቋንቋችን ሲተረጐምካህኑ ዮሐንስየተባለውን ነበር። በእምነታቸውመሠረት፣ ካህኑ ዮሐንስ እንደቅዱስ መጽሐፉ መልከጼዴቅ የክህነትንና የንጉሥነትንማዕርግ የተቀባ በፍትሕና በርትዕ የሚገዛ፣ ባንድ ስሙ በማይታወቅ በሩቅ ምሥራቅአገር የሚኖርክርስቲያንንጉሥነው። እንደ . . በ፲፫፻፻፳፱ .. ላይ አንድ የካቶሊክቄስ ህንድ አገር ሁኖእጅግ አስቀኚ ነገሮችበሚል መጽሐፉ የካህኑ ዮሐንስ አገርኢትዮጵያ ናት ብሎ ከመሰከረበት ጊዜ ጀምሮ፣ ቈይተው በ፲፮፻፸ዎቹ ላይሌሎችኢትዮጵያን በኙ የካቶሊክ ካህናት ደግሞ ካህኑን ከኢትዮጵያ ጋር የሚያያይዘውምንም ነገር የለም ብለው እስካስተባበሉበት ጊዜ ድረስ፣ የካህኑን ዮሐንስ አገርለመድረስ፣ ከዚያም የጦር ቃል ኪዳን ጓደኛ ለማድረግ በሚል አሳብ በመነሸጥ፣በአውሮጳውያን እጅግ ብዙ አስደናቂ ነገሮች ፈጽመዋል። ካህኑ ዮሐንስ አገር ፍለጋዘመቻ ተከታታዩን አውሮጳውያን ትውልድ መንፈስ አነቃቅቷል። አገሩን ማግኘትምኞት እንደሸረሪት ድር በልባቸው ውስጥ በማድራት፣ ዐይነኅሊናቸውንበየአቅጣጫው በማወናጨፍ፣ ለሕይወታቸው ሳይሰጉ በዚህም በዚያም በድፍረትሲያወራጫቸው ቈይቶ እንደአሜሪቃ የመሳሰሉትን አዳዲስ አህጉሮችን እንዲያገኙናከሌላውም ዓለም ጋር እንዲተዋወቁ ረድቷቸዋል።

ሁለተኛው ምሳሌመላውን ጥቊር ሕዝብ ይመለከታል። በካህኑ ዮሐንስ አገር አሰሳስሜት ቀስቅሰው አዲሱን የአሜሪቃን አህጉር ያገኙትና እዚያ የሰፈሩትአውሮጳውያን፣ አህጉሮቹን ለማልማት ነፃ የሰው ጉልበት ፈልገው ሊያገኙት የቻሉትአፍሪቃውያንን በባርነት ፈንግለው በማስመጣትና ኢሰብኣዊ በሆነ ሁናቴ በግድበማሠራት ነበር። የባርያ ንግድና የባርነት ኑሮ ሲያከትም ደግሞ፣ ዐይናቸውን ወደአፍሪቃአዙረው፣ አህጉሩን በሙሉ በቅኝ ግዛትነት ሲይዙት፣ ከዚህ የግፍ ቀንበር ያመለጠችውኢትዮጵያ ብቻ ነበረች ማለት ይቻላል። በአሜሪቃም ሆነ በአፍሪቃ አህጉራት የነበረውጥቊር ሕዝብ ከነጭ የጭቈና ግዛትና ሥርዐት ቀንበር ሊላቀቅ ዐቅም ቢያንሰው፣ዐይኑን የጣለው በኢትዮጵያ ላይ ነበር። ካህኑ ዮሐንስ የአውሮጳውያንን የአሰሳ ወኔእንደነሸጠ ሁሉ፣ የኢትዮጵያም መንፈስና ረቂቅ አሳብ የጥቊሩን ሕዝብ ነፃነትናእኩልነት የመጐናፀፍ ተስፋ አነሣሣ። ከአድዋ ድል በኋላ ደግሞኢትዮጵያከአሳብደረጃኢትዮጵያዊነትወደሚለው የፖለቲካና የሃይማኖት እንቅስቃሴ ወደመለወጥደረሰ። ከአሜሪቃ እስከደቡብ አፍሪቃ፣ ከናይጀርያ እስከኬንያ በኢትያጵያዊነት መፈክርዙርያ ተሰልፎ የተነሣው ሕዝብ የነፃነትና የእኩልነት ትግሉን ድምፅ በያለበትሲያክላላው፣ ሲያስተጋባው፣ ሲያከለውና ሲያንረው ቈይቶ በመጨረሻም ዓላማውንለመምታት በቅቷል።

እንግዴህ ኢትዮጵያ በውጭ አገር ዕይታ የተለያየ አስተያየት ቢሰጣትም፣ ባጠቃላይየተጫወተችው የሙጥኝ፣ የአማራጭ ኀይል፣ የነፃነትና የእኩልነት ፋና በመሆን ነው።ክርስቲያኖቹ አውሮጳውያን የእስላሙ ኀይል ጡንቻ አይሎ ቢታይባቸው፣ከኢትዮጵያዊው ካህኑ ዮሐንስ ጋር መተባበር በሚለው አሳብ ዙርያ እንቅልፍ አጥተውአለዕረፍት፣ የተለያዩ ከፍተኛ ጀብዱነት ያሳዩበትን አሰሳዎችንና እርምጃዎችንእንዲወስዱ ድርጓቸዋል። የእስምና እምነት መሥራቾች በበኩላቸው በጠላቶቻቸውእጅ ተጨፍልቀው ከመጥፋት የዳኑት፣ ኢትዮጵያን መጠለያቸው በማድረግ ነው ማለትይቻላል። የመላው ዓለሙ ጥቍር ሕዝብ ተራው በነጮች የበላይነት ጭቈና ታፍኖማንነቱና ታሪኩ በመደፍጠጥ ላይ በነበረበት ወቅት ርጋታውንና መጽናኛውንያገለነጻነቱና ለእኩልነቱ ተግቶ እንዲዋጋ ያሰባሰበውና በአንድነት ጐራ ያሰለፈውኀይል የኢትዮጵያነት መንፈስ ነበር። እንግዴህ ኢትዮጵያዊነት ዘርና ቀለም፣ መደብናእምነት፣ ጾታና ዕድሜ ሳይለይ፣ በአገርና በድንበር ሳይታገድ፣ በችግር ላይ ላለ ሁሉ ፈጥኖደራሽ መንፈስና ረቂቅ አሳብ ብቻ አልነበረም። በረጅም የታሪክ ዘመኑ ፍትሕ ለተነፈጉ፣ሰላም ለተነሡ፣ መጠጊያ ላጡ ከለላቸው ሁኖ የኖረ፣ ሁሉንም በክብር ተቀብሎ ዐቃፊምአስተናጋጅም በበጎ እንጂ በሌላ ተግባር ማይታወቅ ኢትዮጵያ የተባለ ያንድ ግዙፍ አገርመለዮውና መግለጫው ነው

ታሪክ ያነበበ ሰው የካህኑ ዮሐንስም ሆነ ጥቊሩን ሕዝብ ባንድጋ አሰባስበው ለነፃነትትግል ያሰለፉዋቸው ኀይሎች ትረካዎች ምን ያህል እውነተኝነት አላቸው ብሎ መጠየቁአይቀርም። ጥያቄዎቹ አገባብ ያላቸው ናቸው። ከርቀትና የጊዜውን ችግር ለመወጣትሲባል ያልሆነ ገጸባሕርይ ተሰጥቷቸው በበርካታ የፈጠራ ልብስ ስለተሽሞነሞኑእውነቱን መለየት ቀላል ባይሆንም፣ ታሪኮቹ ከምናብነት አያልፉም ማለት ግንአይቻልም።ካህኑን ዮሐንስን በተመለከተ፣በ፲፪ኛ ዘመነምሕረት መኻል አካባቢየነገሡትየዛጐው አፄ ይምርሐነክርስቶስ በሥርዐቱ ደንብ የክህነት ማዕርግ የተቀቡ ቄስስለነበሩ፣ እንደቅዱስ መጽሐፉ መልከጼዴቅ፣ ካህንም ንጉሥም ነበሩ ማለት ይቻላል።በ፲፫ኛ ዘመነምሕረት ላይ

የኖረው አቡጻሊሕ የተባለ የዐረብ ክርስቲያን ጸሓፊ እንደሚነግረን ከሆነ፣ የኢትዮጵያነገሥታት በሙሉ እቤተመቅደስ ውስጥ ገብተው ይቀድሳሉ ይላል። ይሁንና ከነዚህመካከልማንም አውሮጳውያን በሰጡት ዮሐንስ በሚል ስም የሚጠራ ካህን ንጉሥእስካሁን በኢትዮጵያ ምድር አልተገኘም። ግን ርቀትና ጭንቀት ስለተጨማመሩበትአውሮጳውያን ስሙን አዛብተውት ይሆናል። ማንነቱንም በማጋነን ገጸባሕርዩንአኳኲለውት ታላቅነቱን ለማጉላት እንደሞከሩ አይጠረጠርም። አለበለዚያ ለየት ያለጠባይ የሌለው መደበኛ ንጉሥ ከሆነማ፣ የእስላሞችን ኀይል ለመጋፈጥ ትብብሩንናጓደኝነቱን ማግኘቱ ምን ፋይዳ ይኖረዋል። ስለዚህ የካህኑ ዮሐንስ ታሪክም በፍጹምመሠረተቢስ የሆነ ፈጠራ ነው ሊባል አይችልም።

ጥቁሩን ሕዝብ ለትግል ባንድጋ አሰላፊ የሆነችውኢትዮጵያ ሆነች በአገሪቷየመነጨው፣ ጥንታዊውየክርስቲያንሃይማኖትና የዚህም እምነት ጠባቂ አራማጅተቋም ማለትም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ታሪክነታቸው እጥያቄውስጥ የሚገባ አይደለም። ልክ አውሮጳውያን ለካህኑ ዮሐንስ እንዳደረጉት፣ ጥቍርሕዝብ አንዳንድ አጠያያቂ ገጸባሕርያትን ስላለባበሰ፣ እውነተኛ ምንነታቸው ጥቂትቢዛነፍም፣ የታሪኩ ባለቤቶች በርግጥ ሕያውና ግዙፍ ማንነት ያላቸው ናቸው።ርቀትናጭንቀት መደበኛውን ሰማያዊ ገጸባሕርይ ቀባብተው የተለየ ፍጡር ብቻ ሳይሆንፈጣሪም እስከማስመሰል እንደሚደርሱ በጊዜያችን ታሪክ የተገነዘብነው ነው። የነጮቹየቅኝ አገዛዝና የባርነት ቀንበር ያንገፈገፋቸው የጃማይካ ጥቍሮች፣ ለብታቸውእምነታቸውንና ተስፋቸውን የጣሉት የሃይማኖታቸውና የማንነታቸው መታወቂያምሰሶ ሁኖ በቀረው በራስ ተፈሪ ነው። ቈይተውም ከታሪክ ጋር ሲተዋወቁና፣ ግንኙነቱእየተጠናከረ ሲሄድ፣ ራስ ተፈሪ አፄ ኀይለሥላሴ መሆናቸውን ተገነዘቡ። ከዚያም ራስተፈሪ የእንቅስቃሴአቸው ስም ሁኖ ሲቀር፣ኀይለሥላሴን መለኮታዊነትን በማልበስአምላካቸው እስከማድረግ በቅተዋል። ታዲያ ጃማይካውያን መለኮታዊ ገጸባሕርይቢያለባብሷቸውም፣ ራስተፈሪ የበስተኋላው አፄ ኀይለሥላሴ የተባሉ ንጉ ነገሥትበኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ኑረው አያውቁም ተብሎ አይካድም። በዚያው ልክ ደግሞአውሮጳውያን ስሙን በማዛባት ዮሐንስ ቢለው ቢጠሩትም፣ በኢትዮጵያ ምድር ላይየክህነትንና የንጉሥነትን ማዕርግ አጣምሮ የለበሰ ገዢ አልነበረም ማለት አይቻልም።ሁለቱም ኑረዋል።የአፍሪቃ አባትበመባል የሚታወቁትን አፄ ኀይለሥላሴንብዙዎቻችን በዓይናችን አይተናቸዋል። ካህኑ ዮሐንስ ስማቸው ቢዛባም፣ታሪካቸውበአውሮጳ በሚናፈስበት ወቅት አካባቢ በሥነሥርዐቱ ተቀብተውእንደቅዱስ መጽሐፉመልከጼዴቅ ካህንና ንጉሥ የሆኑ ገዢ መኖራቸው ሐሰት አይደለም። በሌላው ደግሞየኢትዮጵያ ነገሥታት አብዛኞቹ የዲቁና ማዕርግ የለበሱ እንደመሆናቸውየቤተክህነትአካል መሆናቸው የሚጠረጠር አይመስለኝም።

በምዕራባውያን ጭቈና ይማቅቅ የነበረው ጥቍር ሕዝብ ፈታኝና እልህ አስጨራሽትግሉ ወቅት በኢትዮጵያዊነት ዙርያ በመሰለፍ ብቻ አልነበረም የታገለው በሰንደቅዓላማዋም ነው። ስለሰንደቅ ዓላማ ብዙ የሚባል ነገር አለ። ግን ጨርቅም ቀለምም፣እንጨትም እንዳይደለ ርግጥ ነው ባጭሩ ያንድ ሕዝብ የመሬቱ ባለቤትነት፣ የነፃነቱርግጠኝነት፣ (የጥሩም ሆነ የመጥፎ) ታሪኩ ርእዮተ ዓለሙ መግለጫ ነው ብሎማጠቃለሉ ይበቃል። ኢትዮጵያ ከዐምስት ዓመት ትግል በኋላፋሽስቶች አገራችንንጥለው እንደወጡ መላው ዓለም ያስታወቀችው፣ ለሕዝቧም ያበሠረችውበመጀመርያ ሰንደቅ ዓላማዋን በመሬቷ ላይ በመትከል ነው። በቀስተደመና ምስልየተሣለው የኢትዮጵያ ባለሦስት ቀለም ሰንደቅዓላማ በጥንታዊነቱም ሆነ ባዘለውምሥጢር የሚያስደምም ነው ማለት ይቻላል አረንጓዴ፣ ብጫ፣ ቀይ ቀለማትትርጒማቸው የአገሪቷንምድር፣መንግሥትና ሕዝብሲያመለክት ባሕርያቸው አንድምሦስትም መሆኑን ያሳያል። ሦስት ፍጽምናን ሲያንፀባርቅ፣ አንድ ደግሞ የሦስቱንምአካላት በዓላማ፣ በአቋምና በግብር ያላቸውን ውሕደትና እኩልነት ያረጋግጣል።በአረንጓዴ የተመሰለችው ምድር የሁሉም ፍሬ ሕይወት ሲትሆን፣ ሕዝብ ደግሞየምድሪቷ ነዋሪዎች ላገርና ለወገን ፍቅር ካስፈለገ ሕይወታቸው በጀግንነትሊሠ ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋግጣል። ብጫው መንግሥት የምድርና የሕዝብጠባቂ፣ የሁለቱም አንድነት ማተብና ሐረግ ሲሆን ሕዝቡን አገር ለመከላከልም ሆነለልማት በኅብረት ማሰለፍ ግዴታውና አላፊነቱ እንደሆነ ይነግረናል።

ከአስድናቂው የአድዋ ድል በኋላ ጥቊር ሕዝብ የኢትዮጵያዊነት መግለጫና የማንነቷመለዮ ሁኖ ለዓለም የተበሠረውን የኢትዮጵያን ሰንደቅ ማንም ነፃነትና እኩልነትትግሉ ወቅት እንደትእምርተ ኀይልና እንደትእምርተ መዊዕ ውለብለብ ነበር። የአሳቡጠንሳሽ የመላውን ዓለም ጥቊር ሕዝብ ለዚህ ዓላማ ባንድጋ ያሰባሰበው ስመጥሩውየጃማይካው ተወላጅ ማርኩስ ጋርቬይ ነው። አቶ ጋርቬይ፣ በአ. . በ፲፱፻፳ .. ተመልከት ዓላማህን፣ ተከተል አለቃህንሲል ጥቊር ሕዝብ ማንነ ግለጫ፣የትግ ተስፋ እንዲሆንለት ሰጠው የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማን ቀለማት ነውወደሠላሳ ዓመታት ቈይተው፣ ነፃነታቸውን የተጐናፀፉት አብዛኞቹ የአፍሪቃመንግሥታትም የአገራቸው ክቡርና አኩሪ ታሪክ የነፃነታቸው ማረጋገጫ፣ መሬታቸውባለቤትነት ማስመሰከርያ እንዲሆን የመረጡት እነኚሁኑን ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማሦስቱን ቀለማት በመዋስና መሠረት በማድረግ ስለነበር፣ ዛሬየመላዋ አፍሪቃቀለማትበመባል ይታወቃሉ።

የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ከፍተኛ አድናቆት በዚህ ብቻ አላበቃም። የአድዋ ድል ጥቁሕዝብ ተጋድሎ ደጋፊ የነበረውንና በዘመናዊ ፈጠራው የታወቀውን ጋሬት አውጉስቱስሞርጋን ከኢትዮጵያ ጋር ሊያተሳስር በቅቷል። መኪናና የተለያየ ተሽከርካሪ በዓለም ላይብቅ ማለት መጓጓዣ መንገዶቹን እጅግ በጣም አጨናንቆ ብዙ ሕዝብ ለአደጋሲያጋርጥ ለሞት ሲዳርግ፣ ብዙ ቢሞከርም ፍቱን መፍትሔ ሊገኝ አልተቻለም።የተቻለው፣ በአ. . ፲፱፻፳፪ ዓ. ም. ላይ አቶ ሞርጋን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለሞችትራፊክ መብራት አገልግሎት በማዋሉ ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስሦስቱ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለማት ዘመናዊ ተሽከርካሪ በሚጓዝበት መንገዶችበመላው ዓለም ከዳር እስከ ዳር የሰው ልጅ መመለሻ ጠባይ ተቈጣጣሪ ነዋል።ሦስትዬው ቀለማት የትራፊክ መብራት በያለበት የሕግ አስጠባቂና አስከባሪ ኀይል ብቻሳይሆን፣ አገልግሎቱን ከጀመረበት ወቅት ጀምሮ የብዙውን ሰው ሕይወት ከሞትአድነዋል፤ ትርምስምስና ጭንንቅ ከየመገናኛ መንገዱ አስወግደው ዘርና አካባቢ፣ቋንቋ ባህል፣ እምነትና የትምህርት ደረጃ መደብና ማዕርግ ዳራና ፆታ ሳይለሁሉንም በእኩልነትና በትክክል ሥነሥርዐትና መከባበር እያስተናገ ይገኛ

ኢትዮጵያ ዓለምዐቀ ጥቊር ሕዝብ የነፃነት አድማሱን የምታንቀሳቅስ ረቂቅመንፈስ የመጨረሻ ድሉ ተስፋና አርአያ ብቻ ሁና አልቀረችም። የትግሉን ሕልምእውን ለማድረግ ለአብዛኛው ጥቊር ሕዝብ በተለይም ለአፍሪቃ ወሳኝ አስተዋፅዖበተግባር አበርክታለች። ከዚህም የተነሣ የአፍሪቃን የነፃነት ትግል በጊዜው በዋናነትየመሩት አፄ ኀይለሥላሴየአፍሪቃ አባትየተባለ ስያሜ ሲሰጣቸው፣ ኢትዮጵያ ደግሞየአፍሪቃ እናትበመባል ትታወቃለች። መናገሻ ከተማዋም የመላዋ አፍሪቃ ድርጅትመቀመጫ ሁና ተመርጣለች።  

ኢትዮጵያ ሁሉንም በክብር ተቀብላ በእኩልነት በነፃነት የማስተናገድና የማዋሃድ፣የማቻቻልና አብሮ የማ ታሪክ ያላት አገር መሆኗን አይተናል። እነዚህ እሴቶች ከውጭለሚመጣ ብቻ የሚለገሡ ወይንም ይስሙላ የተደረጉ አይደሉም። ጩራቸውንወደውጭ አገር ለማፈናጠር በቁትበአገር ውስጥም የኢትዮጵያዊነት ምንነት ራሱመግለጫውና መለዮው በመሆናቸው ናቸው ኢትዮጵዊነት ሁሉንም ዐቃፊናአስተናጋጅ፣ አግባብቶና አቻችሎ አንዲት አገ ጥላ ሥር በአንድነት በነፃነትበእኩልነት የሚያኖር ባለረጅም ታሪክ ሁለገብና ውስብስብ ማራኪ ባሕርይ ያለው ረቂቅኀይል ነው። ዛሬ የዘውግና የግራዘመም ርእዮተ ዓለም አቀንቃኞች እንደሚሉን፣ኢትዮጵያ ባንድ ዘውግ ወይንም አንድ ቋንቋና ባህል ባለው ብሔረሰብ የተፈጠረች አገርአይደለችም፤ ሁናም አታውቅም። በተለያየ ጊዜና ምክንያት ሰበብ ወቅት፣ ልዩ ልዩአካባቢ በመሳብ የተዋሐዱ የብሔረሰቦች ጒንጒን ናት

በኢትዮጵያ ሕዝብ መካከል ያለው ልዩነት የቋንቋና የእምነት እንጂ የዘር ወይንምየቀለም አይደለም። ከስድስት በላይ ዓመታት ጀምሮ ሕዝቡ በወረራና በፍልሰትሲንሰራራና ሲስፋፋ ሲደበላለቅና ሲዋሐድ ኑሯል። አገሪቷም በየጊዜው የውድቀትናየትንሣኤ፣ የመጥበብና የመስፋት ተመክሮ አጋጥሟታል። እነዚህ ሁናቴዎች በተከታታይበተፈራረቁባት የረጅም ታሪክ ጉዞ ባላት አገር ውስጥ፣ ለሥልጣን፣ ወይንም ለሀብት፣አለበለዚያም ከብት ግጦሽ ወይንም ለፍትሕ ፍለጋ ሲል የሰሜኑ ማኅበረሰብወደደቡብ፣ የደቡቡ ወደሰሜን፣ የምሥራቁ ወደምዕራብ የአዜቡ ወደሊባ፣ የመስዑወደባሕር፣ መሃሉ አገር አቋርጦ በማለፍ ፈልሶ በየአቅጣጫውና በየዳር ድንበሩሲሰፍር ቈይቷል። በየጊዜው አገሪቷን ያናጧት የነበሩት የርስ በርስ ጦርነቶችናግጭቶች ባንድ በኩል አካባቢውን ጐድተዋል ቢባልም በሌላው በኩል ደግሞአብዛኛውን የኢትዮጵያን ሕዝብ በዚያው ልክ ከማቀራረብ አልፈው አዋህደዉታል።በተለያየ መንና ምክንያት በየወቅቱ የተካሄደው የሕዝብ ፍልሰ በተራለሃይማኖቶች መስፋፋት ረድቷል ለንግድና ለንግደት ከሚደረጉት እንቅስቃሴዎችጋር ሁኖ እሱም ልክ እንደጦርነቶቹ፣ በመጨረሻ ላይ ሕዝቡን ወደየርስ በርስ ጋብቻወደባህልና ቋንቋ ውርርስ መርል። በጠቅላላ፣ እነዚህ ገጠመኞችና ሁኔታዎችበርካታውን የኢትዮጵያን ሕዝብ በታሪክ፣ በደም፣ በቋንቋ፣ በባህል ከማስተሳሰርአልፈው እንደሰርገኛ ጤፍ ደበላልቀውታል ለማለት ያስደፍራል ከዚህም የተነሣ፣በዘሩ ጭንጩ የሆነ ዘውግ በርግጥ በኢትዮጵያ ውስጥ አለ ማለት አስቸጋሪ ነውእውነት ነው እያንዳንዱ ዘውግ ራሱን የሚገልጥበት የተለየ ራሱ ነው መባል የሚአካባቢ ቋንቋ አለው። ይኸ ማለት ግን ሁሉም ቋንቋውን ተናጋሪው ሕዝብ ሆነግለሰብ ካንድ እንጅላት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ነው ማለት አይቻልም። አብዛኛውለሚኖርበት መጤ፣ አለበለዚያም ከሌላ አገር ከፈለሰ መጤ ጋር የተቀላቀለና የተዋሐደነው። ስለዚህም በርካታው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣አንዱ የሌላው የሥጋው ቊራጭ፣የደሙ ፈሳሽ ነው ቢባል መቼም ከእውነት የራቀ አባባል አይደለም። ድርና ማጉ አንድነገድ ወይንም አንድ ጐሣ የሆነ በኢትዮጵያ ምድር አካቶ የለም ማለት በርግጥባይቻልም የብሔርነት ስያሜ የሚገባው ሕዝብ አለ ማለ ግን እጅግ ያጠራጥራል።

ለኢትዮጵያዊነት ስብጥርነት ዋነኞቹ ምክንያቶች የማእከላዊው መንግሥትየመንሰራ ግዛቶቹን ለማስፋፋት ሲል ኩታገጠም አገሮችን የማዋሀድ ጥረትያስከተቸው ጦርነቶች ሆኑየሕዝብ ፍልሰቶች ናቸው ብለናል እስኪ አጠር ባለ መልኩጥቂቶቹን እንቃኝ።

ከክርስቶስ ልደት በፊት የጀመረው የአክሱሞች መንሰራ ከዛሬዋ ኢትዮጵያበርዝመትም በስፋትም እጅግ የሚበልጡ አገሮችን በውስጣቸውም የሚኖረውሕዝብ በኢትዮጵያዊነት ሥር ካጠቃለለ በኋላ፣ ዘጠነኛው ዘመነምሕረት አካባቢሲያበቃ፣ እስከ፲፫ኛው ዘመነምሕረት ድረስ ባለው ጊዜ አገዎች ተተኩ

                                                    ካርታ ፩።

ሁለቱ ሥርወ መንግሥታት ሽግግ መካከል በነበረው የጨለማና የድብልቅልቅ ዘመንበመባል በሚታወቀው ወቅት የአካባቢው ከፍተኛ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዝውውርናፍልሰት ተፈጽሟል ማለት ይቻላል። የአገዎቹ በትረመንግሥት ሲያከትም፣ ሥልጣኑንየወረሱት ሰለሞናውያን እስከ፲፮ኛ ዘመነምሕረት ቈዩ በግዛታቸው ዘመን፣ እነሱያልደረሱበት የኢትዮጵያ ምድር፣ ያልተዋጉበት ማእዘን አልነበረም ማለት ይቻላል። ከነሱቀጥሎ፣ ተራው የሱማሌዎችና የአዳሎች ሆነ እነሱም ለተሻለ ኑሮ ሲሉ ከአደን ሰላጤተነሥተው ወደሐረር ርሰው በተለያየ የሥራ ዘርፍ ተሰማርተው ሲኖሩ፣የእስልምናእምነት አራማጆችና ሰባኪዎች ሁነው ግራኝን በመከተል ከምሥራቅ ወደምዕራብዘመቱ እዚህ ላይ መሰመር ያለበት ዛሬ ሱማሌና ጂቡቲ በመባል የሚታወቁት ሁለቱልዑላን መንግሥታት ከአክሱማውያን ዘመን ጀምሮ የኢትዮጵያ ግዛት እንደነበሩ ነው።ስለዚህ ግራኝም ሆነ ጦር ሠራዊቱ ኢትዮጵያውያን ነበሩ።

                             ካርታ

ግራኝ ለዐሥራዐምስት ዓመት ያህል ባካሄደው ጦርነት ኢትዮጵያን የመግዛት አሳቡቢከሽፍበትም፣ ወረራው ያስከተለው ለውጥ ሥረነቀል ብቻ ሳይሆንጥልቀትና ዘላቂነትያለው ነበር። በወረራው ምክንያት የአክሱማውያን ውድቀት ካስከተለው ይበልጣልማለት የሚቻል፣ከፍተኛ የሕዝብ ፍልሰትና ዝውውር ተፈጽሟል በኢትዮጵያ ላይለበላይነት ይታገሉ የነበሩት ሁለቱ የክርስቲያኑና የእስላሙ ኀይ ከልክ በላይ ሲዳከም፣ተጠቃሚ የሆነው ዘላኑ የኦሮሞ ሕዝብ ነው። በአፈታሪክና በሱም ተደግፈው በየጊዜውበተጻፉት ጽሑፎች መሠረት፣ ኦሮሞ ሕዝብ መነሻው ከደቡብ ከባሌ እንደሆነይነገራል ከዚያ እሱም ተራውን ከብቱን ይዞ ግራውንና ቀኙን እየወረረ እየተጓዘበ፲፯ኛና በ፲፰ኛ ዘመነምሕረት አራቱ የአገሪቷ እዘኖች መንዘራፈጥ በቃ  

                                            ካርታ

በኢትዮጵያ ታሪክ የአባ ባሕርይን ጽሑፍ በስሕተት በመተርጐም ኦሮሞችን በተመለክተሁለት ዐበይት ስሕተቶች ሲደጋገሙ ይታያ አንደኛው፣ ኦሮሞችን እንደመጤዎችየማየት ዝንባሌ ነው ሐቁ ግን ከዚያ እጅግ በጣም የራቀ ነው። አባ ባሕርይ ጻፉትስለኦሮሞ ሕዝብ በኢትዮጵያ ታሪክ መድረክ ብቅ ማለቱ፣ ስለኅብረተሰቡ አወቃቀርናከሱም ጋር በማያያዝ ፍልሰታⶨው ስላስከተላቸው ብሔራዊ ጠንቆች ውዝግቦችእንጂ ስለኢትዮጵያዊነት ማንነ ይደለም ኦሮሞች ኢትዮጵያውያን የአገሪቷምሕዝብ አካል ስለመሆናቸውበፍጹም የሚያጠያይቅ ሁናቴም ጊዜ ለም። በኢትዮጵያውስጥ ይኖ ነበረው ሕዝብ አንዱ መሆናቸውን በ፲፬ኛ ዘመነምሕረት ላይ የተጻፈታሪከ ነገሥት በግልጥ ይመክራል። ከ፲፫፻፯ እስከ፲፫፻፴፮ .. የነገሡት ስመጥሩናገናናው ለሞናዊው ንጉሥ ዐምደጽዮን በደዋሮ አድርገው ሽፍታውን የአዳልንጉሥ ሊወጉ ሲሄዱ በ፳፰ ሚያዝያ ላይ በዓለትንሣኤበደስታና በሰላምያከበሩትናየሚወዷቸውንና እጅግ የምትደነቀውንባለቤታቸውን ንግሥት መንገሣመጀመርያ ትተውአቸው የሄዱት ኋላም በሠኔ ሰባት ላይ ተመልሰው መጥተውየወሰዷቸውበጋላከጋላአገር ነበር ይኸ በንጉሠነገሥቱ የተፈጸመው ሥራበማያከራከር ግዛታቸው

                                    ካርታ

ውስጥ መሆኑ ጠያይቅም። ድርጊቱም ሆነውጋላየተባለ ሕዝብ ኢትዮጵያንመውረር ጀመረ ከተባለበት ጊዜ ሆነ አባ ባሕርይ መጽሐፋቸውን ከመጻፋቸውወደሁለት መቶ ዘመን አስቀድሞ ነው።

ሁለተኛው ስሕተት፣ ካንዳንድ ባህላቸው መመሳሰል የተነሣ ኦሮሞችን እንዳንድ ሕዝብየማየት ወረራቸውንም አንድ ሁነው እንደፈጸሙ አድርጎ ማሰብ ሁናቴ አለ። እውነቱግን ከባህል ከቋንቋ ተመሳሳይነት በዘለለ፣ የተረጋገጠ ምንም ዐይነት ታሪካዊ አንድነትላቸውም። በታሪክም የሚታወቁት ቱለማ፣ ጃዊ፣ ሊበን ለበቻ በመሳሰሉት እጅግ በጣምበተለያዩ የጐሣ መጠርያቸው እንጂ ኦሮሞ ወይንምጋላተብለው አይደለም። የኦሮሞዘር አባቶች እንደሆኑ የሚነገሩት በረይቱማና ቦረንም ጥንት አንድ አካባቢ ሲኖሩ አንድሕዝብ ሊሆኑ ይችላሉ። ልክ እንደዛሬዎቹ አይሁዶችና ዐረቦች፣ ወይንም ከዚያ ወረድ ሲልየጀርመን ዘር ምንጭ ናቸው እንደሚባሉት እንደኦስትሮጎቶችና ቪሲጎቶች ማለት ነውየቋንቋቸውና የባህላቸው ተመሳሳይነት ዚያ ጋር የተያያዘ ሊሆን ቢችልም፣ የተረጋገጠነገር ግን በፍጹም የለም። ይሁንና፣ አዝማናት የቈጠረ፣ የጥንት ታሪክ ነው። የአዳምምሆኑ፣ ከዚያ ወረድ ስንል የይስሐቅ ልጆች፣ ማለትም የዛሬዎቹ አይሁዶችና ዐረቦች፣እንዲሁም የእንግሊዞችና የሰሜን ኢጣሊያን ሎምባርዶች ቅድመአያቶች አንድ ቋንቋይናገሩ ነበር እንደማለት ነው። ዛሬ ግን ሁሉም እንደየአሰፋፈራቸውና እንደየነገዳቸውበተለያዩ ስሞች ይጠራሉ፤ የሚናገሩትም የየአገራቸውን ቋንቋ ማለትም እንግሊዝኛ፣እስጳንኛ፣ ኢጣሊያንኛ ወዘተ. ነው።

ወረራቸውን በተመለከተ፣ ባህላቸው ቢመሳሰልም፣ ተለያዩ ኦሮሞ ጐሣዎች ከጥንትመኖርያቸው ከደቡብ ኢትዮጵያ ተነሥተው መኻል አገሩን የወረሩት እንደአንድ ሕዝብሳይሆንርስበርሳቸው በከብታቸው ግጦሽ እየተፋጁ ነበር። ላንድ ዓላማ፣ ወይንም የጋራችግር ወይንም ጠላት ሊጋፈጡ ሲሉ አብረው የመከቱበት የዘመቱበት ጊዜ በታሪክውስጥ ከቶውኑ የለም። ጐሣዎቹ በታሪክ የሚታወቁት በትብብር ሳይሆን በርስበርስለከብታቸው ግጦሽ መጣላትና በመጨፋጨፍ ነው። የማንነታቸውና የአንድነታቸውመግለጫ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ነው። ሁለቱንም ገሃ ያስመሰከሩትበኢትዮጵያና በኢትዮጵዊነት ጥላ ሥር ከሌላው ሕዝብ ጋር አብረው በመኖር ከሱም ጋርጠላትን በአንድነት በመመከት አገሪቷን ጀብዱነት በመከላከል ነው ከዚህ የተለየታሪክ ግን የዛሬው የጐሣ አቀንቃኞችና የግራዘመም ርእዮተ ዓለምአራማጆችእንዲሁም ብሔረሰባችን ወኪል እኛ ብቻ ነንብለው ራሳቸውንበራሳቸው የሾሙት የጠባብ ብሔርተኞች ስብስብ የፈጠሩት ልበወለድ እንጂ ምንምዐይነት እውነተኝነት የላቸውም ቀጥለን ሚናየው ታሪክ ይኸንን እውነት በማያወላሁናቴ ያረጋግጥልናል።

ኦሮሞች ተራቸው ሁኖ ፍልሰታቸውን የጀመሩት ከላይ እንዳልሁት በ፲፮ኛዘመነምሕረት መኻል አካባቢ ነው ተብሎ ቢገመትም፣ ግማሽ ዘመን ባልሞላ ጊዜውስጥ ግን ውጭ አገር ከመጣ ማለትም ከባዕድ የኢትዮጵያ ወራሪ ጠላት ጋርሲፋለሙ ኢትዮጵያን ዳርና ድንበር ሲጠብቁና ሲያስከብሩ ይታያሉ።አብዛኞቻችንይልቁንም ኢትዮጵያ የመቶ ዓመት ታሪክ አገር ናት እያሉ ሚያንቋሽ ዘጠኝ መቶ ዐምሳዎቹ ስድሳዎ ትውልድ ኢትዮጵያውያን በውጭ አገር ጠላትላይ የተቀዳጁት ድል ሲነሣ እንደወሳኝና ታሪካዊ አድርገው የሚያዩት በኢጣልያን ላይየተፈጸመው የቅርብ ጊዜው የአድዋ ድል መሆኑ አይካድም ዚያ ግፋ ሌላለትዝታ በቃ ቢኖር፣ ራስ አሉላ በዚሁ በኢጣሊያ ጠላት ላይ አስቀድመው በዶጋሌአለበለዚያም አፄ ዮሐንስ በግብጽ ላይ ጉራዕና ጉንዴት የተጐናጸፏቸው ድሎችናቸው። እውነቱ ግን ኢትዮጵያ ዳር ድንበሯን በመድፈርቅኝ ግዛቱ ለማድረግየሞከረው ኀይለኛ ባዕድ ወራሪ ልጆ ትብብር ጡንቻውን ሰብራ ነፃነቷንናልዕልናዋን ያስከበረችው ቅርቡ ዘመናችን የመጣውን ጠላት በጀግንነት መመከትብቻ አልነበረም። በ፲፭፻፸፩ና በ፲፭፻፹፫ .. ላይ ከኦቶማን ቱርኮች ጋር ሁለት የሞትየሽረት ትግል ተፋልማ የኢትዮጵያ ሠራዊት ከፍተኛ ድል ለመቀዳጀት በቅቷል። ድሉከያገሩ ተወጣጣው ወታደር ኀይል ውጤት ቢሆንም፣ ለመጀመርያ ጊዜ የኦሮሞፈረሰኛ ልክ በጊዜአችን በአድዋ እንዳደረገው በዚህም ጦርነት ወሳኝ ሚናየተጫወተበት ጊዜ ነበር ተብሏል። ጦርነቱ ልክ እንደአድዋው ለኢትዮጵያ ህልውናእጅግ በጣም ወሳኝ ነበር። ያኔ አብዛኛውን ዓለም ይገዛ በነበረው በኦቶማን ቱርክ የጦርኀይል ኢትዮጵያ ብትሸነፍና ሰለባው ሁና ብትቀር ኑሮ፣ ታሪኳና ቅርጿ፣ የሕዝቧምሥነልቦና፣ እንዲሁም የአገሪቷ ባህልም ሆነ እምነት ዛሬ ከምናየው እጅግ በጣም የተለየሁኖ እንደሚቀር አያጠራጥርም። ሌላው ቢቀር፣ በማንም ባልተደፈረ ሕዝቧ ነፃነትናየድል ታሪክ የማይሻር መጥፎ የሥነልቦ ጠባሳ ተወ ነበር እንግዴህ ኦሮሞኛተናጋሪው ኅብረተሰብ ታሪክ ከመዘገባቸው ከነዚህ ሁለቱ ጦርነቶች ጊዜ ጀምሮ አሁንእስካለንበት ወቅት ድረስ እንደሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እኩል አሻራውን ያላሳረፈበትየጦር ሜዳና ድል በኢትዮጵያ ታሪክ የለም ማለት ይቻላል።

                                                     ካርታ ፭

ከነዚህ ጦርነቶች ወዲያ፣ ተመሳሳይ እጅግ በጣም ጥልቅ የሆነ የኦሮሞች የውሕደትሂደት በሌላውም መስክ በጉልህ ሲፈጸም እናያለን። ወረራቸውን ጀመሩ በተባለውበመቶ ዓመታቸው ውስጥ፣ ኦሮሞች ከፍተኛ የቤተመንግሥት ባለሟሎችና ያገር ግዛትአስተዳዳሪዎች ከመሆን አልፈው ከፍተኛ ኢትዮጵያ ቀለም ትምህርትም ደረጃየመጠቁና የበቁ ግለሰቦች እንደነበሩ ጢኖ በመባል የሚታወቁት ጸሓፈትእዛዝ አዛዥተክለሥላሴ [፲፮፻፲፪፲፮፻፴፪] ጥሩ ምስክር ናቸው። ንጉሠነገሥቱ አፄ ሱስንዮስእንደልቤ ታማኝየሚሏቸውና ዋናው አማካሪያቸው የነበሩት አዛዥ ጢኖ የኛምየራሳችን ቋንቋ ብለው ከሚመኩበት አማርኛ በተጨማሪ፣ ሮሞን፣ እንዲሁምግእዝ አሳምረው የሚያውቁ አቀላጥፈው የሚናገሩ ቅኔ የሚቀኙ፣ አንደበታቸውየተባ፣ ብዕራቸው የሰላ ጸሓፊ ብቻ አልነበሩም በጊዜያቸው በመላ ኢትዮጵያ ውስጥየለየላቸው ምርጥ የቅኔ ምሁራን በመባል የሚታወቁት ቢቈጠሩ ሥር እንኳንየማይሞሉ የቅኔ ትምህርት ዐዋቂዎች ክበብ ዋና አለቃቸው ነበሩ አድናቂዎቻቸውኢትዮጵያውያን ብቻ አልነበሩም፤ በጊዜው በአገሪቷ ውስጥ ከፍ ያለ ዕውቀት የነበራቸው አውሮጳውያንም በማሰብ ችሎታው የረቀቀ፣ በተሰጥዎው የመጠቀ፣ በትምህርቱተደነቀሰው ነበሩ ብለው ይመሰክሩላቸዋል።

ኦሮሞች ብዙም ሳይቈዩ እያንዳንዱ ነገዳቸው በየሰፈረበት ቦታ የጥንት አረመኔአዊልማዱ ትቶ በቋንቋ፣ በባህልና በእምነት ከሰፊው የአካባቢው ሕዝብ ተዋህዶናተመሳስሎ ይገኛል። በ፲፰ኛ ዘመነምሕረት መጨረሻ ደግሞ ኦሮሞኛ ራሱ ከማንኛውምየዓለም ፊደል አስቀድሞበአገርበቀሉ ግእዝ ሆሄያት መጻፍ ጀመረ። በቀጣዩ ዘመንመጨረሻ አካባቢ ደግሞ ቅኔም በኦሮሞኛ ሲቀኝበት ይታያል የቋንቋውን ፍጹምኢትዮጵያዊነት በፊታውራሪነት የመራው ግን የፖለቲካው ዘርፍ ነበር። ይኸበዘመነመሳፍንት ወቅት ስናይ ግልጽ ይሆንልናል

ዘመነመሳፍንት ማለት ባጭሩ ኢትዮጵያን ከዳር እስከዳር የሚያስተዳድር ማእከላዊመንግሥት በጠፋበት ወቅትወሬሸኮችበመባል የሚታወቁት የየጁ ባላባቶችነገሥታቱን በዘፈቀደ እንደጉልቻ እንዳሰቸው እየቀያየሯቸው ሸዋ ስተሰሜንማለትም ከወሎ እስከባሕረ ኤርት ያሉትን ግዛቶች በበላይነት ቀጥቅጠው ይገዙየነበሩበት ወቅት ነው ታሪክ ስሕተት የጊዜውን አስተሳሰብ በመከተልየጋላ ግዛትዘመን ብሎ ቢጠራም፣ ሐቁ ግን የተለየ ነው።ወሬሸኮችአመጣጣቸው ከዐረብምድር ይባላል። ስለዚህ የጁዎች ኦሮሞች አይደሉም ግን ከኦሮሞኛ ሆነአማርኛ እንዲህም ከሌላው ቋንቋ ተናጋሪ ሕዝብ ጋር በአምቻና፣ በጋብቻ፣ በባህልናበእምነት እጅግ የተሳሰሩ በመሆናቸው ሥርወ መንግሥታቸው በስብጥርነቱ እውነተኛየኢትዮጵያዊነት መግለጫ ማለት ይቻላል። ወሬሼኮች ሹመታቸው እንደራሴነትነው። ግን በዘመነመሳፍንት ለስም ብቻ ንጉሦችን እየሾሙና እየሻሩ፣ከውጭ አገር ጋርበሚያካሄዱት መንግሥታዊ ግንኙነቶች የጽሑፍ ልውውጦችአንዳንዴ ራሳቸውንሐበሻ [ኢትዮጵያ] ንጉሥ ሌላ ጊዜ ደግሞ የኢትዮጵያርእሰ መኳንንትእያሉበማስታወቅ፣ የመንግሥትን ሥልጣን ጠቅልለው የያዙት እነሱ ነበሩ

ዘመነመሳፍንት ራሱ የሁለ አዲሶች ኀይሎች ማለትም ባንድ በኩል እቴጌ ምንትዋብሞግዚትነት የሚመራው የቋሮች፣ በሌላው በኩል ደግሞ ኦሮሞ ባላባት ልጅበነበረችው እቴጌይቷ ምራትና ጋፊዎ መካከል ይካሄድ የነበረው የሥልጣንሽኩቻ ውጤት ቢባል ስሕተት አይመስለኝም ሁናቴው በግልጥ የሚያሳየን ነገርቢኖር ከሁለት መቶ ዓመት በፊት በስተደቡብ ወደመኻል አገር ውን የጀመረውዘላኑ የኦሮሞ ሕዝብ በጋብቻ፣ በባህልና በኑሮ ከቀረው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋርተዋሕዶ በከፍተኛ ደረጃ መንግሥትን የመምራት ሥልጣን ለመጨበጥ እንደቻለ ነውከዚያም በመቀጠል፣ በ፲፱ኛ ዘመን መኻል በቋራው አፄ ቴዎድሮስ ተጀምሮ በአፄምኒልክ የቀኝ ጃቸው በነበሩት በራስ ጐበና በተጠናቀቀው ኢትዮጵያ የመልሶአንድነት ምሥረታና ግንባታ እንዲሁም በተከታታዩ የዕድገቷና የልማቷ ሥራ ከመሪነትእስከተራ አላፊነት ባለው ዘርፍ በመሰማራት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ካበረከቱት ዋነኞቹየኦሮሞነት ጥንት ዝምድና ያላቸው እንደሆ ታሪክ ይመክራል።

በኦሮሞ ሕዝብ ላይ በመጠኑ ሰፋ ያለ ገለጣ ለመስጠት ፈለግሁበት ዋናው ምክንያትፍልሰቱ በኢትዮጵያም ሆነ ኅብረተሰቡ ራሱ ላይ ያመጣውን ሥርነቀል የሆነ ጥልቅናሰፊ ለውጥ በአጭሩ ለማሳየትበዚያው ልክ ደግሞ፣ የኦሮሞን ሕዝብ ኢትዮጵያዊነትበመካድ አንዳንድ የብሔረሰቡ ልሂቃንና ድርጅቶቻቸው የሚነዙት ታሪክ መሠረተቢስእንደሆነ ለማገናዘብ ነው። የኦሮሞ ሕዝብ የውሕደት ሂደ የሌላውንም የኢትዮጵያንኅብረተሰብ ሁናቴ ያንጸባርቃል ማለት ይቻላል። ለከብቱ ግጦሽ ፍለጋ ሲል በስደቡብከባሌ አካባቢ የተነሣው ዘላን ሕዝብ፣ ግማሽ ዘመን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በየደረሰበትሁሉ፣ የጥንት ኑሮውን ስልት ትቶ መስፈር በግብርና መተዳደር ጀመረ። በየሰፈረበትምአካባቢ ከተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር በባህል፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖትና በትውልድመዛመድና መዋሐድ የግድ ሆነበት። በተለያየ የሥራና የሥልጣን ዘርፍ ተሰማርቶየአገርንና የመንግሥትን ህልውና በመጠበቅና በማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅዖ ሊያደርግበቃ። እንግዴህ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ምን መሆኑን ከእንደዚህ ዐይነቱ ታሪክለመማርና ለመረዳት አያዳግትም ብዬ አምናለሁ።

ከዚህ በታሪክ ጸሓፊዎች ግምት ቢያንስ ከስድስት ሺዓመታት በላይ የቈየ ይልቁንምየመንግሥትና የሕዝብ መንሰራፋት የመስፋፋት፣ የውርስና የቅርስ፣ የአምቻና የጋብቻታሪክ እጅግ በጣም አድርገን በከፍተኛ ደረጃ መገንዘብ የሚገ ሁለት ጉዳዮች አሉእነኚህም፣ ስለኢትዮጵያም ሆነ ስለኢትዮጵያዊነት በተናገርን ቊጥር ተደጋግመውመጉላት፣ በጥብቅ መነገርና መሰመር ያለባቸው ነጥቦች ናቸው ብዬ አምናለሁ። ጉዳዩሕዝብ ሆነ መንግሥትን ይመለከታል። አንደኛው፣በኢትዮጵያ ውስጥ በተፈጸመውመንግሥት መንሰራትና መጠናከር ሂደትና ተግባር ሌላው ተነጥሎ ተለየጥቅም ያገኘ ሆነ ገኝ የቀረ፣ የተከፋም ሆነ የተጐዳ የኅብረተሰብ ክፍል የለም ብቻሳይሆን፣ ኑሮም አያውቅም። ትላንት ወራሪ አጥቂ የነበረው ኅብረተሰብ ብዙምሳይቈይ ከጥንቱ ባለጋራው ጐን አብሮ በመሰለፍ፣ አዲ የውጭም የውስጥም ወራሪሲከላከል፣ የአገሪቷን ዳርና ድንበር ሲጠብቅና ሲያስጠብቅ፣ ግዛቷንም ሲያስፋፋ፣ራሱም ሆነ ለወገኑና ለአገሩ ደኅንነ ሲል ጦር ሜዳ በየጢሻው፣ በየበረሃውናበየዱሩ ሲወድቅ ሲዋደቅ አጥንቱን ሲከሰክስ፣ ደሙን ሲያፈስ ይታያል። እንግዴህታሪክ ግልጥ አድርጎ የሚያስረዳን ነገር ቢኖር በኢትዮጵያ ታሪክ ማንኛውም ኅብረተሰብበጊዜውና በተራው ጐጂም ተጐጂም ተጠቃሚም መሆኑን ነው።

ሁለተኛው ከፍተኛ ነጥብ በኢትዮጵያ የተካሄደው የመንግሥት መንሰራፋትም ሆነየሕዝብ ፍልሰት የመጨረሻ ውጤታቸው የሚመሰገን የሚደነቅ ቢሆንምሂደታቸውየተፈጸመው ግን አብዛኛውን ጊዜ በሰላማዊ መንገድ አለመሆኑን መገንዘብ ነውአልፎ አልፎ በሰላማዊ መንገድ ቢከናወንም ብዙውን ጊዜ የሚያመዛዝነው ግንጉልበትና ጥቃት እንደነበር የማይካድ ሐቅ ነው ይኸም ማለት አንዱ ኅብረተሰብከጥንት መኖርያው ተነሥቶ ወደሌላው አካባቢ ሄዶ ሲሰፍር፣ የአገሩ ነባ ሕዝብመጤውን ከበሮ እየደለቀለት፣ እምቢልታ እየነፋለት፣ ቀይ ምንጣፍ አንጥፎለት፣ ቄጠማጐዝጒዞለት፣ ጮቤ እየረገጠ፣ በሆሆታና በእልልታ፣ በሽለላና ዝለላ የተቀበለበትወቅት ሁናቴ ኢትዮጵያ ታሪክ መዝገብ ውስጥ ከቶውኑ የለምኑሮም አያውቅም ብልስሕተት አይመስለኝም። ኢትዮጵያ ኅብረተሰብ መካከል የፍልሰቱ ታሪክ በውጭም ሆነባገር ውስጥ ጸሓፊዎች በሰፊው የተነገረለት ሕዝብ ቢኖር የኦሮሞኛ ቋንቋ ተናጋሪውክፍል ብቻ ነው ማለት ይቻላል። ይኸ ኅብረተሰብ ከደቡብ ወደመኻል አገር ፍልሰትናመንሰራፋት እንደጀመረ በወቅቱ በአካባቢው የነበረው ጶርቱጋላዊ ጳጳስ አቡነቤርሙዴዝ በመጠኑ መዝግበውታል በጽሑፋቸው እሳቸው ነበሩበት ወቅትእንኳንኦሮሞች ለከብቶቻቸው ግጦሽ ሲሉ የኢትዮጵያን ሦስት ሰፋ ግዛቶቿወርረው ቊጥጥሯቸው ሥር ለማድረግ እንደበቁ አቡኑ ይናገራሉ እነዚህምስፋታቸው ካስትልንና ጶርቱጋልን የሚያካክሉ ባሌና ደዋሮ አገሮች እንዲሁምብቻውን ልክ እንደፈረንሳይ መሬት የሚሰፋ የሐዲያ ግዛት ናቸው ይኸ እንዴት ሊሆንእንደቻለ ጳጳሱ ገልጹልን እንዲህ ይላሉ።

ጋሎች መኖርያቸው በሞቃዲሾ አካባቢ ነው።አገራቸውን ያጠ አለነዋሪባዳ ምድር አድርገው ሊያስቀሩት ብቻ ሲሉ፣ ጐረቤቶቻቸውን ሆነ ሌላውንማንውንም አገር እየወረሩ የሚኖሩ ጨካኝና ኀይለኛ ሕዝብ ናቸው አንዱንአገር [በኀይል] ሲይዙ፣ ወንዶቹን በሙሉ ያርዳሉ፤ የልጆቹን አባለዘራቸውንይቈርጣሉ፤ አሮጊቶቹን ይገድላሉ፤ ልጅ እግሮቹን ደግሞ ለጥቅማቸውስለሚፈልጓቸው እንዲያገለግሏቸው ሲሉ ይወስዷቸዋል

                                                                                           ካርታ ፮

የአቡኑ ምስክርነት የተጻፈበት ወቅት ከፍተኛ የትርምስምስ ብጥብጥ ጊዜ በመሆኑ፣ሙሉ በሙሉ ግል ጥላቻ የጠራ አስተያየት ነው ብሎ ለመቀበል አስቸጋሪ መሆኑአይጠረጠርም። ሁኖም፣ ሳቸው በኋላ ወደሠላሳ ያህል ዓመት ቈይተው የጻፉትዕውቁ የኦሮሞ ታሪክ ሊቅ አባ ባሕርይም ሆኑ ሌሎችም በተከታታይ በተለያየ ወቅትናምክንያት ታሪኩን ያጠኑት የውጭና የውስጥ አገር ተመራማሪዎች የጳጳሱን ዘገባእንዳለ አላንዳች ክርክር ይጋሩታል

የኦሮሞ ብሔረሰብ እስከመሃሉ አገር ሊስፋፋ የበቃው፣ ከፊቱ ያለውን እየተዋጋናእያጠፋ ኀይለኛውን ሕዝብ ደግሞ አልፎ እየሄደ፣ ገበረለትን ኅብረተሰብ ግንጉዲፈቻ፣ሞጋሳ [ሞገ] ገበር የተባሉ ሥርዐቶቹን በመጠቀም ጦር ኀይል ከሥልጣኑሥር እያስገባ እያንበረከከባህሉንና ቋንቋ ደፍጥጦ ሰብእናውን ጨፍልቆ፣በኦሮሞነት አጥምቆ ሁለተኛ ደረጃ ዜግነት እየሰጠ መሆኑን ሁላቸውምይስማሙበታል

እዚህ ላይ መነሣት የሚገባ አንድ አንኳር ነጥብ አለ። ይኸውም፣ አንዳንድ የተዛባ የታሪክግንዛቤ ያላቸው ይልቁንም ጠባብ ጐሣነትና የግራዘመም ርእዮተዓለም አቀንቃኞችአፄ ቴዎድሮስ ተወጥኖ በአፄ ምኒልክ የተደመደመውን የኢትዮጵያን አንድነት መልሶግንባታና ተግባሩን የፈጸሙትንም ሆነ ሱም ፍሬና ውጤት የሆኑትንየምኒልክሰፋሪዎችበማለት እስከመወንጀል ደርሰዋል። ከዚህም የተነሣ ቢያንስ ከሰባተኛዘመነምሕረት ጀምሮ የኢትዮጵያ ማእከላዊ መንግሥትና የሕዝቧ መገናኛና መግባቢያቋንቋ የሆነውን አማርኛ የሚናገረውን ሕዝብና ግለሰ ከያሉበት በግፍ ከወንዛቸውና ከሕዝባቸው እየነጠሉ እያፈናቀሉ በማስወጣት ከፍተኛ ኢሰብአዊ ግፍ እየፈጸሙእንዳሉ ማየት ዛሬ የተለመደ ሁኗል። መገንዘብ ያቃታቸው ግን፣የምኒልክ ሰፋሪዎችጋዳ ሰፋሪዎች አዳልና ከሱማሌ ሰፋሪዎች አገውና ከትግሬ ሰፋሪዎችየማይለዩ አለመሆናቸውን ነው። ሁሉም በየጊዜውና በየምክንያቱ ተነሥቶ አጋጣሚውንተጠቅሞ በኢትዮጵያ የአንድነትም ሆነ የጥቃት ወረራ ተሳትፏል። ሁሉም ከሌላ አካባቢየመጣ ሰፋሪ ነው።

አማርኛ ምኒልክ ሰፋሪዎችጋር የሚዛመደው፣ ለዘመናት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋንቋሁኖ መገኘቱና፣ ከተለያዩ አካባቢና ቋንቋ ተናጋሪ ኅብረተሰብ የተወጣጡየኢትዮጵያንየአንድነት መልሶ ግንባታ በተግባር ያዋሉት ጀግኖች አባቶችና ሠራዊታቸውእየተኰላተፉም ቢሆን ስለተናገሩት ብቻ ነው። ጥንት ባንድ ወቅት፣ አምሐራ ወይንምአማራ ከተባለ አካባቢ ጋር ግንኙነት ኑሮት ይሆናል። ቢኖረው፣ አዝማናት ያስቈጠረታሪክ ነው። ዛሬ ዋጋ የለውም፤ ምንጩን ማወቁ ግን ጥሩ ነው። ያኰራል ዛሬ ግንአማርኛ፣ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት መሠረታዊ መግለጫና መለዮ ነው። የተለያዩየኢትዮጵያ ብሔረሰቦች መግባቢያ፣ መገናኛና ጥብቅ መተሳሰርያ ሰንሰለት ነው።ኢትዮጵያውያን፣ በ፲፮ኛ ዘመነምሕረት ቱርኮችን፣ በ፲፱ኛ ዘመነምሕረት ኢጣሊያኖችንድል ያደረጓቸው፣ አማርኛ በመኖሩ መሆን መረሳት የለበትም። አለበለዚያ፣ ጥረታቸውናትግላቸው እንደባቢሎን ግንብ ገንቢዎች ባክኖ በቀረ። ቢሆንማ፣ ኢትዮጵያም ኩሩየነፃነት ታሪኳን፣ ኢትዮጵያውያንም የሥነልቦና ጥንካሬንና አልበገርነትን ከትውልድወደትውልድ ለማስተላለፍ ባልታደሉም ነበር። ኢጣሊያንኛ የኢጣሊያኖች፣ እንግሊዝኛየእንግሊዞች ቋንቋዎች እንደሆኑ ሁሉ፣ አማርኛም የኢትዮጵያውያን ነው።አውሮጳውያን ሴማዊ ቢሉትም፣ ሰባ ከመቶ ያላነሰ ኩሻዊነት አለው። ስለዚህየኢትዮጵያን ብሔረሰቦች በሙሉ ለማንኛዉም ሳያዳላ የሚወክል፣ ከማንኛውም ጋርየማይተሳሰር፣ ሲናገሩት ጉሮሮ የማይከረክር፣ ምላስ የማይዶለዱም፣ ገለልተኛ፣ ግልጽናጥርት ያለ ቋንቋ ነው። ለዕድገቱ አብዛኛው የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ከፍተኛአስተዋፅዖ እንዳበረከተ ራጥርም። በውስጥም በውጭም ግንኙነት፣ መሪዎቹ የተጠቀሙት፣ የአካባቢያቸውን ቋንቋ ሳይሆን፣ አማርኛን ነው አፄ ዮሐንስ የትግራይተወላጅ ናቸው። ግን ሥራቸውን ያካሄዱት በሚቀላቸው ትግርኛ ሳይሆን በአማርኛ ነው። በምዕራብ ኢትዮጵያ በ፲፱ኛ ዘመነ ምሕረት ማቈጥቈጥ የጀመሩት የኦሮሞባላባቶች ግዛቶች መሪዎች ሆኑ፣ በእንግሊዝ ቈስቋሽነት የምዕራብ ኢትዮጵያ የጋላ ባለቃልኪዳን መንግሥታትን ለማቋቋም የቃጡት እንደነደጃዝማች ሀብተማርያም የመሳሰሉት፣ ከእንግሊዝም ከኢጣልያንም የመንግሥት ባለሟሎች የተጻጻፉት በአማራ ሳይሆን በአማርኛ ነው። ወደበስተኋላ ገፋ ካልን ደግሞ፣ የዘመነመሳፍንት የኦሮሞገዢዎች እንዲሁ። ግራኝ ራሱ አማርኛ ተናጋሪ እንደሆነ፣ የወረራው ታሪክ ጸሓፊውይገልጥልናል።

አማርኛን ምኒልክ ሰፋሪዎችጋር ብቻ ማዛመድ ከታሪክ ጥራዘነጠቅነትና ከጥላቻውጭ፣ ሌላ ምክንያት አይኖርም። ምኒልክ ሰፋሪዎችተብዬዎቹ፣ አማርኛ ይናገሩእንጂ፣ ከመጡበት ብሔረሰብና አካባቢ አኳያ ካየናቸው፣ ደምበኛ ምርምር ተደርጎባያረጋግጥም፣ ተጨባጭ ሁናቴው የሚያስረዳን ወደሰማንያ ከመቶው በላይ የኦሮየጉራጌ፣ የትግሬ እንዲሁም የቤኒሻንጉል ኅብረተሰብ አካል ናቸው። በአንድ ቃል፣ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በጉልህ የሚያንጸባርቁ፣ የተለያዩ ብሔረሰቦች ስብጥርናቸው ልበልና ወዳቋረጥኹት ወደዋናው ነጥቤ ማለትም ወደመንግሥት መንሰራፋትልመለስ።

ማእከላዊ መንግሥት መንሰራፋት ጠባይ ከሕዝቡ የፍልሰት ባሕርይ የተለየ አይደለምማለት ይቻላል። ሁኖም የመንግሥት መንሰራ ነፃና ራስገዝ ብሔረሰቦች ካባቢዎች መካ የሚከሠቱትን አለመግባባቶችንና ግጭቶችን አስወግዶአንድነትናስምምነት ማምጣቱ እጅግ የተቀደሰና የሚደነቅ ድርጊት መሆኑ አይካድም። እነዚህጉልበታቸውን በርስበርስ ጥቃት በከንቱ ከማባከን፣ ሰላምና ዕርቅ በሰፈነበት ምድርራሳቸው ልፅግናና ዕድገት ሲሉ እናት ለሆነችው አገራቸው ልማት ተባብረውናተስማምተው እንዲሠሩ መንግሥት ሁላቸውን እንዳንድ አገር ባንድ የግዛት ሥልጣንጥላ ሥር ቢያመጣም የመንሰራ ሥራ ግን ራሱን የቻለ አስከፊ ገጽታ እንዳለመረሳት የለበትም። ንድ አገር ሲመሠረት መንገዱ አልጋ በአልጋ ሳይሆንብዙ ደምየተፋሰሰበት፣ ሕዝብ የወደመበት፣ አካባቢ የተደመሰሰበት ነው። ታሪክ በምስክርነትከወሰድን፣ በፈቃደኝነትና በውውይት በምክክርና በመግባባት የተመሠረተ መንግሥትከቶውኑ በዓለማችን ላይ ኑሮ አያውቅም ሌሎቹን ትተን እስኪ ዛሬ በምግብናዋና ዘመናዊነቷ ኀያላኖቹ የምዕራብ መንግሥታት አካል አንዷ የሆነችውን ጀርመንንእንመልከት።

ጀርመን፣ ከዐምስት መቶ በላይ ልዑንና ራስገዝ የነበሩትን ልዩልዩ መንግሥታት አንድ በማምጣት እንደአንድ አገር ሁና ከተፈጠረች ወደሁለት መቶ ዐምሳ ዓመታትልታስቈጥር ቀርባለች እነዚህ መንግሥታ መሬታቸው ኩታገጠም ከመሆን አል፣ በዘር፣ ባህልና በቋንቋ ያላቸው ልዩነ እምብዛም ልነበረ ይሁንና በሰላማዊመንገድ ሁላቸውንም ወደአንድነት ማምጣቱ ለዘመናት ሞከርም ጥረቱ ፋይዳሁኖ ነው የቀረው ከአንነቱ ይበልጥ ይቀናቸው የነበረው ርስበርስ በጦርነትእየተፋተጉ እየተጨፈላለቁ መኖ ነበር። ሰላ ውድ ወደአንድነት ማምጣትርባናቢስ መሆኑን ተረድቶ፣በብረትና በደምኀይል አንድ ያደረጋቸው አምባገነኑየፕሩሲያው መሪ ቮን ቢስማርክ ሲሆን፣ እሱምአንድ አገር እንዴት እንደተመሠረሶሰጅ እንዴት እንደተሠራ መጠየቅ አይገባም፤የሚል አንድ ድንቅ አባባል ቶልናል

ኢትዮጵያ ከሦስት ዓመት በላይ የሚገመት አኩሪ የአንድነትና የመንግሥትነት ታሪክእንዳላት ምንም የማያከራክር ሐቅ መሆኑን ዐይተናል በዚህ የረ ታሪክ ውስጥ አንድነቷ ከጊዜ ወደጊዜ ፈርሶ የቈዳዋ ይዘት የጠበበ የሰፋበት ወቅትእንደተፈራረቀባት አንሥተናል በዘመነመሳፍንት የተገረሰሰው አንድነት በዘመናዊመልኩ ከአን መቶ ዓመት በኋላ ተመልሶ ገነባ የበቃው ጦርነት በድርድርም ላይተንተርሶ ነበር። ይሁንና ከሌሎች አገሮች ሁናቴ ጋር ታይ የኢትዮጵያ ዘመናዊአንድነት ንባታ ከፍተኛ ብልህነትና አርቆአሳቢነት የተካሄደ ተግባር ብቻሳይሆንአብታዊና አድናቆትንም የሚያተርፍ ነው ብል ስሕተት አይመስለኝም ለምሳሌያህል እንደአሜ በዘርና በቀለም በመበካከል በመደብና በጾታ በመለያየት፣ በዕውቀትና በሀብት በመመሠረት፣ ልዩነትንና አድልዎን ያማከለ፣ ኅብረተሰቡን አንዱንለማዕርግ ሌላውን ባርነት ከዚያ ሎሌነት በይፋ በሕግ የደነገገ አይደለም። ወይንም እንደ አብዛኞቹ አገሮች በብሔረሰብነትና በቋንቋ በማመኻኘት፣ ኅብረተሰብ ሆነ ግለሰብ ዕድሉ የተቀጨበት፣ አንዱ ሌላውን የጨነበት፣ ደምየተቀባበት ሁናቴ አልታየም። እንዲሁም በእምነቱ፣ በዘሩ፣ ወይንም በቀለሙ ልዩነትምክንያት፣ አንዱ ወገን ጌታ፣ ሌላው ባርያ ሁኖ የኖረበት ወቅት አልነበረም። እንደጀርመኖች የዘር ማጥፋት ዘመቻ አልተካሄደም። እንዲሁም ባህልንና ቋንቋስለማይጋራ፣ በቀለም ስለማይመሳሰ በሀብትና በጉልበት ስለማይመጣጠን፣ ጾታናትውልድ ስለሚለ ብቻ ተነጥሎ፣ ለሌላ የተሰጠው ዕድል የተነፈገ የኅብረተሰብክፍል የለም በአስተዳደር ደረጃ አንዳንድ ጉድለቶች መኖራቸው አይካድም። ግንየኢሕአዴግ አገዛዝ የመንግሥትን ሥልጣን እስከተቈጣጠረበት ወቅት ድረስ፣ ልዩዘውግ ወይንም የዘውግ አባል በመሆኑ ወይንም ዘውጉ ከሰፈረበት አካባቢበመምጣቱ፣ አለበለዚያም ቋንቋውን በመናገሩ፣ ወይንም በጋብቻ ሆነ በሌላ መልክበመተሳሰሩ ብቻ በይፋ ሆነ በኅቡዕ የተሸለመ፣ ወይንም የተንቋሸሸ፣ የተጨቈነ፣ ዜግነቱን ያጣ የሌላው አገልጋይ እንዲሆን ማዕቀብ የተጣለበት፣ በሕግልማድም ከሥልጣንም ከዕድገትም የታገደ ግለሰብም ሆነ ብሔረሰብ በኢትዮጵያታሪክ ውስጥ አልታየም። ይልቅስ በኢትዮጵያ ታሪክ ማአከላዊ መንግሥት ሲስፋፋ፣ በተደጋጋሚ ጉልህ ሁኖ የሚታይ ነገር ቢኖር፣ የተሸነፈውን ክፍል ወይንም ኅበረተሰብለመግዛት ወይንም ለመጨቈን ሳይሆን፣ ሕዝብን ርስበርሱ ለማቀራረብና ለማዋሀድ፣ ከባ ወራሪም በትብብር ለመከላከል ነው ቢባል ይመረጣል ታሪክ ሲመረመር፣ የኢትዮጵያ ማእከላዊ መንግሥት የአስተዳደር መፈክር አራት መሠረታዊና አንኳርበሆኑ ነጥቦች ሊጠቃለል ይችላል። አንደኛ፣ ወደፈለግህበት ሂደህ፣ በሰላም ኑር። ሁለተኛ፣ ግብር ገብር። ሦስተኛ፣ ነጋዴዬንና ገበሬዬን (የአገር ሀብት ምንጭእንደመሆናቸው)፣ መንገደኛዬንም አትንካብኝ። በመጨረሻ፣ በአካባቢህ ሰላም አትንሣ። መንግሥት ጦርነት የሚያውጀው፣ አካባቢውንም ሆነ ግለሰቡን የሚቀጣው፣ ከእነዚህመሠረታዊ የዜግነት ግዴታዎች፣ አንዱም ቢሆን ቢፈርስና ሳይሟላ ሲቀር ነው።  

የኢትዮጵያን የአንድነት ግንባታ ከሌሎች አገሮችና መንግሥታት የሚለያት ሌላምአስገራሚ ገጽታ አለው። የኢሕአዴግ መሪዎች ክሺዘጠኝመቶስድሳዎቹ ሰባዎቹተማሪዎች እንቅስቃሴ ለጥቅማቸው ሲሉ ተበድረው ሚያነበንቡት አርቲቡርቲ ካልተሸነገልን በስተቀር ደጋግሜ እንዳነሣሁት፣ የኢትዮጵያ ሥልጣኔና መንግሥት ሆነየአገሪቷ የአንድነት ግንባታ፣ ካንድ ከተለየ ብሔረሰብ ወይንም አካባቢ ጋር የተያያዘበትናተቈራኝቶ የታየበት ጊዜ አልነበረም። ሁኖም አያውቅም። በመጀመርያ ደረጃ፣ ዘመነመሳፍንት ፈርሶ የነበረው የሕዝቡና ያገሩ አንድነት መልሶ በዘመናዊ መልኩ የተቋቋመው ባንዴ ሳይሆን በሂደት ው። እንደአንድ አገ የተቋቋመው ካንድከተወሰነ አካባቢ ወይንም ጐሣ በመነጨ ጦርና መሪ ሳይሆን፣ ተለያየ ወቅትናምክንያት ከየአካባቢው ተወጣጣና ተቀናጀ፣ በመሪነትም ሆነ በሠራዊት ደረጃ፣ ልዩልዩ ብሔርንና ብሔረሰቦችን ባቀፈ ኀይል ነው ቀለል እንዲልልን እስኪ ዐጠር ባለመልኩ ወደዝርዝሩ እንግባና እንየው።

ዘመነ መሳፍንትን አክትመው ሲያበቁ፣ ያንድነቷን መሠረት የጣሉላት አፄ ቴዎድሮስየቋራ ተወላጅ ናቸው የንጉሠነገሥትነት በትር እንደጨበጡ፣ በሰሜን ኩል በተከታታይ ብቅ ሉት ውጭ አገር ወራሪዎች ጥርስ እንዳትገባእየተዋጉ፣ በመጨረሻም በጦር ሜዳ ላይ ሕይወታቸውን የሠው አፄ ዮሐንስ የትግራይተወላጅ ነበሩ። ከአውሮጳውያን መንጋጋ አድነውት፣ደቡቡን ቀኑት አፄ ምኒልክ ከሸዋሲሆኑ፣ የምዕራቡን ክፍልና ግንባር ያደላደሉት ጉሥ ተከለሃይማኖት ግን ከጐጃምናቸው። እያንዳን ንጉሥ በጐ፣ በጀግንነታቸው እጅግ የታወቁና የተፈሩ፣በጦርዕቅዳቸው የሚደነቁ፣ ቈራጥና ስመጥሩ በሰሜን እንደራስአሉላ አባ ነጋ፣ በምዕራብእንደራስ ደረሶ አባ ቦ፣ በመኻል አገር የሸዋው ራስ ጐበና አባ ጥጉ የመሳሰሉ የጦርአበጋዞች ነበሯቸው። ሌላውን የዘር ሐረጋቸውን እግምት ሳናስገባ፣ በአባታቸውናበአካባቢያቸው ብቻ ተመሥርተን በትውልዳቸውና አፋቸውን በከፈቱ ቋንቋ ከሄድንደግሞ ራስ የኦሮሞ፣ ራስ ደረሶ የአገው፣ ራስ አሊ የትግሬ ብሔረሰብ ናቸውይባላል እንግዴህ በዚህ መልክ የተቋቋመችው አገር ሕዝ መሪዎቹ ያስተዳድሩየነበሩት ለማንም ሳያዳ ገንዘባቸው ዐቅማቸው በፈቀዱት መጠን ሁሉንምበእኩልነት ስለነበር፣ አንዱ ዘውግ በተለየ መልክ ሞንሙኖ እንዲፈስ ሌላውተቀፍፎ እንዲኳሰስ ደረገበት ቅት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አልነበረምአልታየም።

እነዚህ የጦር መሪዎችም ሆኑ ነገሥታቱ ለታላቅ ክብርና ማዕርግ የበቁት ደግሞ፣ በኢትዮጵያ በመወለዳቸውና የኢትዮጵያዊነት ካባ በመልበሳቸው ነው ማለት ይቻላል። ከላይ እንዳየነው፣ የኢትዮጵያዊነት ታላቁ ዕሴት ምሥጢር፣ ከማንም ተወለድ፣ ከየትአካባቢ ና፣ ዕጣፋንታህ ከሆነ ችሎታና ብቃት ካለህ፣ ታማኝነት ካሳየህ ለማንኛውምወግና ማዕርግ ዕጩ ብቁ ነህ የሚል መሠረታዊ የማይካድ እምነት በያንዳንዱ ልብለዘመናት ተቀርጾ መኖሩ ነው። ተለያየ ጊዜ ኢትዮጵያን የጐበኙትን ምዕራባውያንበጣም ካስደነቋቸው ነገሮች ዋነኛው የተለያየ አካለጉድለት ያላቸው (ለምሳሌ ያህልዐይነስውሮች) እንኳን ሳይቀሩ ከፍተኛ ትምህርት ተምረው ታላቅ ክብርና ማዕርግበቅተው አላንዳች ማዳላት ከሌላው እኩል ሁነ ማየታቸው ር። ይኸ በዚያ ወቅትበምዕራባውያን ዘንድ የማይታሰብ እንደነበር ብዙዎቻችን እናውቃለን በ፲፱ኛዘመነምሕረት ላይ የአ ቴዎድሮስ አማካሪ የነበረው እንግሊዛዊውፕላውዴን እጅግ ያስገረመው ነገር ቢኖር፣ በኢትዮጵያ ምድር ሌላ ይቅርናየሚለብሰው ቡትቶ እንኳን በሌለው ባንድ ጭንጩ ድኻ ሥነልቦና ስለገዛራሱ ያለውጠንካራ አስተያየት በር ፕላውዴን በጽሑፉ ዕድልና ለመታደል ጉዳይ ሁኖአንዱ ከሌላው ለጊዜው እኩል ይሆንም እንኳን፣ በኢትዮጵያ ማንኛውም ሰውበመሠረቱ ያው [እኩል] ነው። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ራሱን ለታላቅ ዓላማየተወለደ እንደሆነ አድርጎ ያምናል ፍጹም የማትረባ ፍንጣሪ እንኳን ቢትሆንይኸንን ምኞቱ ቀጣጥለዋለች ይላል።

በፕላውዴን ትውልድ ርም ሆነ በቀረው ምዕራብ ዓለም እንደዚህ ዐይነትአመለካከት በሕዝቡ ሥነልቦና ለመቅረጽና ተግባራዊ ለማድረግ ከፍተኛ ደም ያፋሰሰሥርነቀል የሥርዐት ለውጥ ማካሄድ ግድ ሆኖባቸዋል። ኋላ የፈረንሳይ መንግሥትከፍተኛ መሪ ሁኖ ለታላቅነት የበቃውና፣ መላ አውሮጳን ያንቀጠቀጠው ናፖሊዎንቦናፓርቴ ዐይነት የፈረንሳይ አብዮት ባይኖር ኖሮ፣ የአንድ አገር መሪ መሆን ቀርቶ፣ ለተራመኰንንነትም እንኳን ለመታጨት ዕድሉ የመነመነ ነበር። ለምን እንዳል ባጭሩላብራራ። ብዙዎቻችን እንደምናውቀው፣ ከፈረንሳይ አብዮት በፊት አብዛኛውየምዕራባውያን ኅብረተሰ ቤተክህነት ቤተመሳፍንትና ቤተአልባሌ በተባ፣ የየቅላቸው ሰብእናና አገልግሎት ባላቸው በሦስት ማኅበራዊ ዕርከን የተደረደሩ ነበር። በየመንግሥታቱ የበላዮቹ ሁለቱ የየአገራቸው ባላቶች ሲሆኑ፣ ቤተአልባሌስምየሚጠራው ሦስተኛ ርከን መደብ ግን በተለያየ የሥራ ዘርፍ ተሰማርቶ ዐሥራት፣ግብርና ቀረጥ በመክፈል፣ ሁለቶቹን ማገልገል ካልሆነ በስተቀር ሌላ ፋይዳአልነበረውም። የበላዮቹ ሁለቱ የአገሩ ጠቅላላ ሕዝብ ዐሥር ከመቶ እንኳን የማይሞሉቢሆኑም፣ ሥልጣኑንና ማዕርጉን፣ ሹመትንና ዕድገትን አጠቃልለው በእጃቸውስላደረጉት ቤተአልባሌ ክፍል አባል ምንም ቢተጋና ቢጥር፣ ቢቋምጥና ቢለማመጥ፤ ቢማለድና ቢገዳገድ፣ ከመደቡ ወጥቶ ለወግና ለማዕርግ የመብቃት ዕድሉ የተቀጨበር የፈረንሳይ አብዮት ርዐቱን አፍርሶ ባመጣው አዲሱ ሥርነቀልለውጥ፣ ሹመትንና ዕድገትን ችሎታና ብቃት ላለው ሁሉ ክፍት በማድረጉ ናፖልዎን ከመጀመርያዎ ተጠቃሚዎች አንዱ በመሆን ከተራ ወታደርነት ተነሥቶ በሠላሳ ዓመትያህል ዕድሜው፣ ንጉነገሥት በመሆን የአገሩ ከፍተኛ ሥልጣን መያዝ፣ አብዛኛውን አውሮጳ ለመግዛት ቅቷል ድልአድራጊው ሠራዊቱም እግሩ ረገጠበት የአውሮጳ ምድር አሮጌውን ሥርዐት ገርሰ በአዲሱ እየተካ ሄዷል

ምዕራባውያን ማኅበረሰብ አኳያ፣ ኢትዮጵያው ሁሉም ነገር ተሟልቶና ተስተካክሎ ባይሰጣቸውም፣ በአውሮጳ ሆነ በሌላ ዓለም ሰፍኖ የነበረውን ግፈኛ ሥርዐትቀምሰው አያውቁም እያንዳድንዱ ኢትዮጵያዊ ውቃቤው ካልራቀው፣ ችሎታውካለው የማይመጣጠንለት ማዕርግ የማይታጭበት የሙያ ዘርፍ የለም ብሎ ያምንነው ብል ከእውነት የራቀ አባባል አይደለም። ወጉ አካባቢውና አስተዳደጉሁሉምይቻላል፤ ግን ያለፋልየሚል አመለካከት አብዛኛው ዘንድ እንደማያፋልም የማንነትመግለጫው አድርጎ በአእምሮው ቀርፀውለታል። የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ አወቃቀርእንደአውሮጳ ዐይነት ቢሆን ኖሮ ሁለቱ የቋራውና የተምቤኑ ካሣዎች አፄ ቴዎድሮስናአፄ ዮሐንስ ለመባል እንዲሁም በአድዋ ጦርነትና በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ግንባታ ከፍተኛታሪክ የሠሩት እንደፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስና ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ የመሳሰሉት ዝናለማትረፍም ሆነለፊታውራርነትና ደጃዝማችነት ማዕርግ ዕድል ባላጋጠማቸው ነበር።

የኢትዮጵያዊነት እሴቶች ብዙዎች ናቸው። ለመዘርዘር ሰፊ ጊዜና ከፍተኛ ትዕግሥትይጠይቃሉ። እኔ ግን አንዱን ባጭሩ ላነሣ ፍላጎቴ ነው። እሱም ሕግ ርነትንና በሕግፊት ሁሉም ሁኖ መታየት እንዳለበት ነው ግሪካዊው ሄሮዶቱስም ሆነ፣ ነቢዩመሐመድ ከነሱም በኋላ የመጡት ያገር ጐብኚዎች፣ ኢትዮጵያ ሕዝብ ግፍ ላለው ጥላቻው፣ ስለፍትሕ አፍቃሪነቱ እንደሚወድሱ፣ በተለይም ነቢዩ ኢትዮጵያ ገዢ መደብምንም ዐይነት በደል የማይታገሥ ሕዝቡን በፍትሕና በቅንነት የሚገዛብሎእንደገለጠ ቀደም ብለን አይተናል። ንጹሕ በግፍ እንዳይቀጣ፣ ግፈኛው ዋጋውን ሳያገኝከፍትሕ እንዳያመልጥ፣ በደለኛውን አበጥሮ ለመወሰን በየኅብረተሰቡ ፍቱን ተብለውየሚታመኑ እንደሙግት በተጠየቅ፣ አፈርሳታ፣ ሌባሻይ የመሳሰሉ ባህላዊ ዘዴዎችና ተቋሞች አሉ። በመንግሥትም ደረጃ ከክርስቲያኑ ፍትሐነገሥት ውጭ፣ ከከፍተኛው የዙፋን ችሎት እስከ ዝቅተኛው የአፈር ወይንም የሥር ዳኝነት ተዘርግቷል።

እነዚህ ባህላዊ ተቋሞች ኢትዮጵያውያን ስለሕግ እጅግ የዳበረ ግንዛቤ እንዳላቸውያሳያሉ ብዬ አምናለሁ ግፍንም በብዙ ዘዴና ጐራ የትም ቦታ ቢሆን ወደኋላ ሳይሉናሳያመነቱ በቊርጠኝነት የሚዋጉ መሆናቸውን አንዳንድ ታሪካዊ ድርጊቶችን ማገናዘብይጠቅማል በአክሱማውያን ዘመን አፄ ካሌብ በየመን አገር ክርስቲያኖች በሃይማኖታቸው ምክንያት በአይሁዳዊ ገዢ ቢሰደዱ፣ ጦራቸውን አደራጅተው በመሄድከእምነ ልዩነት የተነሣ ማንም በየትም መሰደድ እንደማይገባው በተግባርአስተምረዋል። አሳዳጁንም ያገሩን ገዢ ወግተው ከሥልጣኑ አባርረውታል። ቅርቡፈረንጆች አቈጣጠር በ፲፰፻፰ .. ላይ የኢትዮጵያ መርከበኞች ወደኒውዮርክ ከተማመጥተው ሊጸልዩ ሲሉ ወደቤተክርስቲያን ጐራ ባሉ ጊዜ፣ በጥቍሮቹ ለተመደበው መደዳ እንጂ ከነጮቹ ጋር ተቀላቅላችሁ መቀመጥ አትችሉም ቢባሉበእግዚአብሔር ቤተጸሎት ምንም ዐይነት ልዩነት አይገባም ብለው ጥለውበመውጣት፣ ሌሎችጥቁሮች በማስተባበር አንድጋ ሁነው የመጀመርያዋን የኢትዮጵያ ምጥማቅ ቤተክርስቲያንየሚትባለውን በከተማዋ ረቈሩ። ይህች፣ በኢትዮጵያ መርከበኞ የተቈረቈረችው ቤተክርስቲያ በአሜሪቃ ለጥቍር ሕዝብነፃነትና እኩልነት በተካሄደው ትግል ታሪክ ከፍተኛ ሚና እንደተጫወተች በግልጽ ይነገራል

አፄ ካሌብም ሆነ መርከበኞቹ ሥራ የሚያስረዳን ኢትዮጵያውያን ግፍ በማየትየሚከፉ ብቻ ሳይሆን፣ በሰው ዘር እኩልነትና መብት ላይ እንደማይደራደሩ ነው። አስተሳሰባቸው ከአውሮጳውያኑ ምን ያህል እንደላቀና ወደፊት የገፋ መሆኑንምያመለክታል ብል ስሕተት አይመስለኝም በጽሑፍም ደረጃ ብንመለከተው ይበልጥይኸንን አጥብቀን እንረዳለን። በአውሮጳ ታሪክ ዛሬው ዘመናዊ አስተሳሰብና ሥልጣኔፈርቀዳጆች በ፲፯ኛና በ፲፰ኛ ዘመነምሕረት ላይ ብቅ ያለው አብርሆ በመባልየሚታወቀው እንቅስቃሴ መሪዎች ናቸው ይባላል ከመካከላቸው በተለይ ሁለትፈላስፎች እንግሊዛዊው ጆን ሎክና ፈረንሳዊው ቮልቴር በታላቅነታቸው ይደነቃሉ። ሁለቱም ግን በሰው ልጅ እኩልነት የማያምኑ፣ ሴቶች ልባምነት የሚክዱ ሲሆኑ፣ ለማትረፍም ሲሉ ገንዘባቸውን በሰፊው ያዋሉ ጥቊሩን ሕዝብ በባርነት በመነገድነበር። ከነሱ ወደመቶ ዓመት አስቀድመው በኢትዮጵያ ድር የታዩት ዘርዐያዕቆብናወልደሕይወት የተባሉ ሁለት ፈላስፎች ግን ስለሴቶችም ሆነ ስለቀረው የሰው ልጅእኩልነት፣ ስለጋብቻ ክቡርነት ስለሃይማኖት ትርጒም ከዚያም አልፎ ጥቅምና ጉዳትብቻ ሳይሆን ባርነት ራሱ ያለመታደልና ያጋጣሚ ጉዳይ ሁኖ እንጂ ባሮቹ ከሌላው የሰውልጅ እኩል መሆናቸውን አትተዋል ጽሑፋቸው፣ አውሮጳውያን የሚመኩባቸውን፣ የዘመናዊ ሥልጣኔ ፈርቀዳጆ የሚሏቸውን ከላይ የጠቀስናቸውን ፈላስፎች እጅግበጣም ያስንቃሉ። የአውሮጳውያን አስተሳሰብ በተራማጅነቱ ከነዚህ ሁለቱኢትዮጵያውያን ርእዮተዓለም ጋር ሊመጣጠን በቃው በጣም ቅርብ ጊዜ ነው ለማለትያስደፍራል በኔ እይታ የነዘርዐያዕቆብን አስተሳሰብ ልዩ የሚያደርገው በጽሑፍመስፈሩ እንጂ እንደ አዲስ ግኝት ሁኖ መታየት ያለበት ነው ብዬ አላምንም አቋማቸው የሚያንጸባርቀው ከመላጐደል አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዘመናት ይጋራየነበረበኅብረተሰ መካከል ሰፊው ይንሸራሸር የነበረውን የቈየና ሥርየሰደደአሳብ ነው።

ኢትዮጵያነት ሕግ የበላይነት ማመ ይጠይቃል። ይኸንንም የሚያመለክቱ የተለያዩ ማስረጃዎች አሉ በየጊዜው ከተራው እስከመኰንኑ፣ ከባለዳባው እስከባለካባው በሕግ አምላክ፣” “በእግዜር፣” “በጃንሆይ [አምላክ] የሚለው አገላለጽ፣ ከዚህመሠታዊ እምነት የመነጨ ነው ንጉሥም ቢሆን የእግዚአብሔር ምድራዊ ምስለኔማለትም እንደራሴ እንደመሆኑ መጠን የሕግ የበላይነትና ያገርን ወግ መጠበቅናማክበር እንዳለበት በሕዝቡ ዘንድ ይጠበታል። እንዲሁም ከሥሩ ያሉትባለሥልጣኖች ጭምር። እውነቱ እንደዚህ ሁኖ እያለ፣ ከዘውዳዊ መንግሥት መገርሰስጀምሮ ስለገዢው ክፍል ይልቁንም ስለነገሥታቱ አምባገነንት ራሳቸውን ከሕግ በላይአድርገው ያዩ ነበር በማለት ብዙ ወቀሳ ይሰነዘራል። ክሱ የመነጨው ከስድሳዎቹ ፀረዘውድ ሥርዐት አዝማቾች ቢሆንም ሌሎቹ ዐውቀው ይሆን ሳያውቁ አሳቡንሲያስተጋቡት ያየን ነን አልፈው አልፈው ወቀሳውን የሚደግፉ ክሥተቶችቢታዩም፣እውነቱ ግን ጠቅላላ አሠራሩንና ለትውልድ ሲተላለፍ የመጣውን ትውፊትልማድ አያንፀባርቅም። የኢትዮጵያ ነገሥታት መፈጸም ከሚገባቸው ታላላቅ አላፊነቶችመካከል እንደዋነኛ ሁኖ የሚቈጠረው ከመሳፍንት እስከተራ ሕዝብ ያለውንማንኛውንም ሰው አቅድ ባለው ሕግ ማስተዳደር፣ እንዲሁም ከቁጣ የራቀአለሕግ ከመቅጣት የተቈጠበ መሪነትን ማስመስከር ነው። የንጉነገሥቱም ሆነየምስለኔዎቻቸው ታላቅነት የሚገለጠው ሥራቸውም የሚደነቀው፣ የማያዳላ ፍርድበመስጠታቸው፣ አንዲሁም በቅንነትና በፍትሕ መግዛታቸው በሕግአክባሪነታቸውም ጭምር ነው። እነራስ አሉላ እነፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስንእንዲሁም አፄ ምኒልክ የመሳሰሉት መሪዎች በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትያተረፉት ኅብረተሰባቸውን በፍትሕና በርትዕ በማስተዳደራቸውና ማንም ከሕግ በላይእንዳልሆነ በማሳየታቸው ነው።አፄ ቴዎድሮስ ወደሸዋ በዘመቱ ጊዜበፍትሐ ነገሥትሳያስፈርዱ በአንዳንድ ከፍተኛ በደል ፈጽመዋል በሚሏቸው ሰዎች ላይ የወሰዱትጨካኝ ርምጃ ከዚህ በፊት ታይቶ ስለማይታወቅበሕዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ፍራቻና ሽብር ከማሳደር አልፎ በጣም እንዳስወቀሳቸውም የታሪካቸው ደራሲዎች ይናገራሉ።ይኸ ዐይነቱ ወቀሳ ለአፄ ዮሐንስም ተርፏል። ሁኖም አፄ ቴዎድሮስና አፄ ዮሐንስየሕዝቡ ተቃውሞ በወቀሳ ብቻ በመገደቡ እጅግ የታደሉ ናቸው። እንደነሱ ሥልጣናቸውን አላገባብ በመጠቀማቸው ለብዙዎቹ የደረሰባቸውን ጽዋአልቀመሱም። በዚህ ረገድ በርካታዎቹ ዕጣ ሥልጣናቸው ውድቀት ውጭ ሌላእንዳልነበረ ታሪክ ደጋግሞ ይመሰክራል። በዚህ አፄ ተክለጊዮርጊስ ጥሩ ምሳሌ ሊሆኑላሉ ብዬ አምናለሁ ንጉሡ ከርሳቸው በፊት ያልተተከለ ግብር በበጌምድር ሕዝብላይ ቢጥሉበት፣ በበጌምድር የለ ግብር፣ በሰማይ የለ ዱር፣ በጌምድር ደረቱን ለጦርእግሩን ለጠጠር የሚል መፈክር አንግቦ፣ ተቃውሞ ሲነሣባቸው ዙፋናቸውንእንዳጡ ድሮም በውድቀት ላይ የነበረውን ንጉሥነትን ከፋ ውርደት ስለረጉስማቸው በተቀጽላተፍጻሜተ መንግሥት ተክለጊዮርጊስበመባል ይታወቃል። ሌሎችምእንደነአፄ ዘድንግል፣ አፄ ሱስንዮስ የመሰሉት ያገሪቷን ወግና ሥርዐት ጥሳችኋልተብለው በጦር ኀይል ከዙፋናቸው እንደተወገዱ ታሪክ ይመሰክራል

ለማጠቃለል ያህል፣ የኢትዮጵያዊነት ፍቹ በቃሉ መሠረትፊቱ የጠቈረነው ቢባልም፣የሚያሳየው በተለያየ ስም የሚጠራና የሚያኰራ ታሪክ ባለቤት የሆነ ሕዝብየሚኖርበትን አገር ማንነት ነው። አንድ ኢጣሊያናዊ ታሪክ ጸሓፊ ኢትዮጵያንየሕዝብ ቤተመዘክርናት ብሎ ይገልጻል። እውነቱ ግን ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን እያንዳንዱኢትዮጵያዊም ጭምርየሕዝቡ ቤተመዘክርነው ማለት ይቻላል። እያንዳንዱ በአካላቱ የአብዛኛውን የኢትዮጵያን ኅብረተሰብ ደምና ሰብእና አዝሎ ይዞራል። ይኸምከስድስት ዓመት በላይ ባስቈጠረው በተለያየ ሁናቴና አጋጣሚ የተፈጸመው የሕዝብከቦታ ወደቦታ መዘዋወርና የማእከላዊ መንግሥት መንሰራራት ከነሱም ጋር ተያይዘውየመጡት ሁናቴዎች ፍሬ ነው። የዘውግና የግራዘመም ርእዮተ ዓለም አራማጆችና አቀንቃኞች የረሱት ነገር ቢኖር፣ ይኸን የኢትዮጵያን ሕዝብ ረጅም የታሪክ ጉዞና እሱምበሂደት ያመጣውን የትውልድና የባህል፣ የቋንቋና የሃይማኖት ትስስርና ውርርስ፣ ውሕደትና አንድነት ነው። ይኸ ሕዝብ በረጅም ጉዞው ሌላው ዓለም ከፍተኛ መሥዋዕትየከፈለባቸውን የሰው ልጅ እኩልነት፣ የሕግ የበላይነት፣ የነፃነት፣ የፍትሕና የርትዕ እሤቶችን በሥነልቦናው በከፍተኛ ደረጃ አዳብሯቸዋል ማለት ይቻላል።

በመጨረሻ መረሳት የማይገባው ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊነት ከሌላው የአፍሪቃና አብዛኛው የዓለም ሕዝብ የሚለዩት የአገሪቷ ጥንታዊነትና ለባዕድ ወራሪ ጥቃት አልበገርነት ብቻ አይደለም። ሲወርድ ሲዋረድ የመጣው ሕዝቧ አንድነትና የአስተዳደሯ አገር በቀልነት ነው። ቅኝ ገዢዎቹ አውሮጳውያን ዓለምን ሊቀረማመቱና ሊበዘብዙሲሉ በየሰፈሩበት ነባሩን ሕዝብ ለጥቅማቸው እንደሚመቻቸው አድርገው በጐሣናበቋንቋ ሲከፋፍሉ፣ ኢትዮጵያ ግን ይኸንን ግፍ አልቀመሰችም። ኢጣልያንም ለዐምስትዓመት አገሪቷን በያዘችው ወቅት እግብር ልታውለው ብትሞክር አልተሳካላትም።እንግዴህ እውነታው እንደዚህ ከሆነ አሁን በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት የሚያራምዳቸው የጐሣና የመለያየት ታሪክ እንዴት መጣ ብለን መጠየቁ ተገቢይመስለኛል።

ከኢጣሊያን ይልቅ ኢትዮጵያ አሁን ላሉት ከፍተኛ ጠንቅና ቀውስ መሠረታቸውእንግሊዞች ወዳጅ በመምሰል ድሉን በያ ቊጥር በየጊዜው የፈጸሟቸው መሠሪተግባሮች ናቸው ቢባል ግንዛቤው ከእውነት የራቀ አይመስልም። እንግሊዞች፣ መጀመርያ አፄ ቴዎድሮስ ዳግማዊን ሊወጉ ሲሉ ያገዟቸውን አፄ ዮሐንስን አታልለውደርቡሾች የተከበቡትን ግብጾች እንዲያድኑ ከተደራደሩ በኋላ፣ የተስማሙበትን ውልአፍርሰው ጣልያኖችን ምጥተውባቸዋል ኢጣሊያኖችም በእንግሊዝ ርዳታ ከኢትዮጵያ ነጥቀው የወሰዱትን መሬት ኤርትራ የሚል አዲስ ስም ሰጥተውከኢትዮጵያ ለዩት። በውስጧ ይኖሩ የነበሩት የተለያዩ ዘጠኙ ብሔረሰቦችበየጐሣዏቻቸው ሲጠሩ የጋራ መታወቂያቸው ኢትዮጵያዊነት እንጂ በሌላ ስምአልነበረም። ኢጣሊያ ኢትዮጵያዊነትን እሷው በፈጠረችው ኤርትራዊነት ተካችው።ቀጥላም፣ ኤርትራን እንደአገር ሊታለማት አልሞከረችም፤ ይልቅስ ሕዝቧን ለሎሌነትናለጠመንጃ ጉርሻ ሲትዳርግ፣ አገሩን ደግሞ የቀረችውን ኢትዮጵያን ለመውረርእንደመፈናጠርያዋ አድርጋ ንደተጠቀችው ሁላችንም የምናውቀው ታሪክ ነው

የቅኝ ግዛ ፍቅር ያንገበገባቸው እንግሊዞች ለዚህ ዓላማቸው መሰናከል ሊትሆንወይንም አደጋ ሊታመጣ ትችላለች በማለት ያሠጋቻቸውን ኢትዮጵያን ለማዳከም ያላደረጉት ጥረት፣ ያልሞከሩት ስልት፣ ያልጠነሰሱት ተንኰል የለም ማለት ይቻላል። በ፲፱፻፳ዎቹ መጨረሻ ላይ ኢጣልያ ኢትዮጵያን ሲትይዝ፣ እንግሊዞች ባንድ በኩልበጠላት ባልተያዘው የምዕራብ ክፍል ጦርነቱን ለመቀጠል የታቀደውን የኢትዮጵያንጊዜያዊ መንግሥት ለማቋቋም ርዳታቸውን ዚያው ልክ ደግሞ በተፈጥሮሀብቱ እጅግ በጣም ባለጸጋ ብለው ለብዙ ዘመን ቋምጡ የነበሩትን ይኸንኑ አካባቢ ከሱዳኑ ግዛታቸው ጋር አዋህደው ለመግዛት እንዳቀዱ ይታወቃል። ለዚህም ሲሉያኔው ወለጋው ባላባት ደጃዝማች ሀብተማርያም ጋር ሁነው የምዕራብ ኢትዮጵያየጋላ ባለቃልኪዳን መንግሥታት የሚል ግዛት ለመፍጠር ዶለቱ። ያሰቡት ባለቃልኪዳኑ መንግሥታት ግዛት ገና ከጅምሩ ቢጨናገፍም፣ ተግባራቸው ግን ጠላትንሊቋቋም የታሰበውን የኢትዮጵያን ጊዜያዊ መንግሥት አኰላሸ። ቈይቶም የኦሮሞነፃነት ግንባር ተባለው የጐሠኞች እንቅስቃሴ መነሻው ሕይወቱ በእንጭጩ የተቀጨው የእንግሊዞቹ ጥንስስ የነበረው የጋላ ባለቃልኪዳን መንግሥታት መሆኑመዘንጋት የለበትም።

የእንግሊዞች ደባ በዚህ አላቆመም። የኢትዮጵያ አጐራብች የሆኑት የራሳቸውና የፈረንሳይ ቅኝግዛቶች ማለትም ሱዳን የሱማሌ ምድር፣ ጂቡትና ኬንያ፣ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ደባ ጓደኛዋ ኢጣሊያ ሲያዙባአጥቂውን ለማባረር የበቁትኢትዮጵያ አርበኞች ጋር በመተባበር በር ኤርትራውያንንም ለዘመናትትመኙ ከነበራችሁ ከእናት አገራችሁ አንድ እንድትሆኑ ንጉሣችሁ ደርልና በኢጣልያንቅኝገዢአችሁ ላይ ተነሡበትብለው ሰበኩላቸው። አጋጣሚ ሆነና ኢትዮጵያ ነፃነት ኤርትራም ተረፈ እንግሊዞች ግን እንደተለመደው በቃላቸው አልጸኑም። ይልቅስሥር የሰደደ ዘረኝነታቸውና ስለጥቊር ሕዝብ ያላቸው ከፍተኛ ንቀት በይፋ ተገለጸ። እንደኢትዮጵያ ዐመጽ በናዚዎች ተይዛ የነበረችውንና በአፍሪቃ ጦር ኀይል ርዳታነፃነቷን ሊታገኝ የበቃችውን ፈረንሳይ አለምንም ቅድመሁኔታ ነፃ ወጧት ጊዜ፣ መሬቷ በፍጹም አልተነካም። ከዚህም አልፎ ናዚዎች ተይዘው በነበሩት በድሮቅኝግዛቶቿ ጭምር ፈረንሳይ አምባገነንነቷን መልሳ እንድታረጋግጥ፣ በሌለው ኀይሏምዕራብ ጀርመንን ተቀራሙ አራቱ ኀያላን አገሮች ተቋዳሽ አደረጓት ወደጦርደኛዋ ጥቁሯ ኢትዮጵያ ስንመጣ ግን ሁናቴው በጣም የተለየ ነበር። ታላቋን ሱማሌፈጥረው ሊገዙ ሲሉለዘመናት የኢትዮጵያ መሬት የነበረውን ውጋዴንን አንለቅምብለው ቁጭ አሉ። ኢጣሊያንን ሊተኩ ያሰቡ በሚመስል መልኩ ጦር ጓደኛቸውኢትዮጵያ ሞግዚትነት ለመያዝ ቃጡ። ኤርትራ እናት አገሯ ቢትቀላቀል፣ጥቅሙ ኢትዮጵያን ሚያጠናከር ሁኖ ስለታያቸው የጦርነት ጊዜ ስብከታቸውን ረስተው በ፲፰፻፹፱ . . ኢትዮጵያና የኢጣሊያን መንግሥታት የተዋዋሉትን የአዲስአበባ ስምምነት በመጣስ፣ አገሩን አንለቅም አሉ። ከዚያም ይባስ ብለው በነሱሞግዚትነት ሥር ከሱዳን ቅኝግዛታቸው በማዋሀድ አገሩን ሊቈጣጠሩት አለበለዚያም የትግራይን ጠቅላይ ግዛት ከኢትዮጵያ ጐምደው ወስደው ከኤርትራ ጋር በማዋሀድ፣ ትግራይትግርኛ የተባለ አዲስ ነፃ አገር ለመፍጠር ተፍጨረጨሩ። ኢትዮጵያንንና ኢትዮጵያዊነትን በሕዝቡ ዘንድ ለማስጠላት ሲሉ በሰሜኑ ከፍል በየጊዜው የተንኰል ሥራቸውን በተለያየ መልኩ አቀናጅተው ሥውር ስብከታቸውን አካሄዱ።

እንግሊዞች ዕቅዳቸው በምንም መልኩ ግቡን ለመምታት ባይችልም፣ በየአካባቢውየዘሩት የከፋፍለህ ግዛ ሤራቸው ዘር ግን ሥር ሰድዶበዐመፀኞች ጀሌዎቻቸውአማካይነት አቈቊጦ ለፍሬ በቅቷል። የዐመፀኞቹ ዋና መነሻ የሥልጣን ቋመጣሲሆን፣ በሕዝብ ፍላጎትም ሆነ በችሎታ ወይንም በብቃ ዕጦት ያገኙ ያልቻሉትንወይንም የተነፈጉትን ሥልጣንና ማዕርግ በነፍጥ ኀይል ለመንጠቅ መከጀላቸውአያከራክርም። በማይወክሉት ሕዝብና አካባቢ ስም ያካሄዱት የነፃነት ትግል፣አላስፈላጊ ከፍተኛ የሰው ሕይወት ጥፋት፣ የአካባቢ ውድመት፣ የንብረት ቀውስናየአስተዳደር ነውጥ ሲያስከትል፣ ነሱ ይኸ ሁሉ ያዩት እንደልጆች ጨዋታ ነው። ምንምአልመሰላቸውም። ነሱ ዘንድ ነፃነት፣ በዘር ማጽዳት በርእዮተ ዓለም ስም ያንድ እናትልጆች በግፍና በጭካኔ መግደል፣ ሰይፍና ጦር መማዘዝ እንደጀብዱ ተቈጠረ። ኢትዮጵያም በገጠሟት የችግሮች ተደራራቢነት፣ የዐቅም ውስንነት፣ አንዳንዴም በአስተዳደር ድክመት ምክንያት በተቀናጀ መልኩ ልትጋፈጣቸው ስላልቻለች፣ እሷንየማዳከም፣ አንድነቷን የማናጋት፣ ታሪኳን የማንቋሸሽ ዓላ ከመላ ጐደል ለጊዜውምቢሆን ተሳክቶላዋል ሥልጣንም እንደያዙ የራሳቸውን አረመኔኣዊ ድርጊቶች ሲያስተሠርዩ፣ የባላንጣቸውን ግፍ ለፍርድ ሲያቀርቡ፣ በግልጥ ያሳዩት ነገር ቢኖር ፍርድቤቱ የፖለቲካቸው ደንገጡሮች እንጂ ሌላ ትርጒም እንደሌላቸው ነው

የሚገርመው እነዚህ ግለሰቦች የጥቂቶቹ ወላጆች በአገር ክህደት የሚወነጀሉቢሆኑም፣ አብዛኞቹ ግን ኢትዮጵያ በታላቅ እንክብካቤ ያስተማረቻቸው፣ አገራቸውንከነጭ የባርነት ቀንበር አወጥተው በጀግንነት ተዋግተው መልሰው በማቋቋም የገነቧት የአርበኞች ልጆች ናቸው። ጀግኖቹ ራሳቸው የመማር ዕድል ሳያገኙትምህርት ቤት አሠርተው፣ አስተማሪ አስቀጥረው ከፍተኛ መሥዋዕት ከፍለውያስተማሯቸው፣ እነዚህ ልጆቻቸው ከነሱ የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩና፣ ኢትዮጵያንም በትምህርት ገበታ ባገኙት ዘመናዊ ዕውቀታቸው ገንብተዋት በሥልጣኔ ከገፉት አገሮችጋር አስተካክለዋት፣ ከተቻለም አስቀድሟት፣ ከኋላቀርነትና ከድኅነት ማቅ አላቅቀዋት፣ ለቀጣዩ ትውልድ እንዲያስረክቧት በማሰብ ነበር። ግን ሁሉ ሕልም ሁኖ ቀረ። ይባስብሎ ደግሞ ልጆቹ እንደጀግኖች አባቶቻቸው መሆ ሲያቅታቸው፣ እንደማድነቅ ጠሏቸው። ብዙዎቹ ታሪካቸውን አኰሰሱ፤ ከነሱ በመወለዳቸው ተጸጸቱ፤ ጀብዷቸውንናቁ። አንዳንዶቹ በግልጥ ባይሉትም፣ ለነጭ ባለመገዛታቸው ተቈጩ።

በዚህ መልክ አገርና ወገን በማንቋሸሽና በመበታተን ተግባር በግንባር ቀደምትነትየመሩት የኤርትራ ነፃ አውጭ ድርጅቶችን ያቋቋሙት ናቸው። የኤርትራ ነፃነት ግንባርሆነ፣ እሱን የተካው ሻቢያ በመባል የሚታወቅ ባላንጣው የኤርትራ ሕዝብ ነፃነትግንባር፣ ዓላማቸው ኤርትራን ከኢትዮጵያ መገንጠል ሲሆን፣ ይኸንንም ለማስፈጸምናለማፋጠን የቻሉት በልኡካኖቻቸውና ኰትኲተው ባሳደጓቸው የጡት ልጆቻቸው መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል። ልኡካኑ መካከል አዞ የተባለው የኢትዮጵያ ተማሪዎችንቅናቄ ቡድን ፲፱፻፷ዎቹ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ጀምሮ በኢትዮጵያ በየዘርፉ ለተከሠተው የታሪክ ግንዛቤና የርእዮተዓለም ቀውስ ሆነ ላስከተለው ኢሰብኣዊተግባር በከፍተኛ ደረጃ ተጠያቂ ነው ቢባልም፣ የጡት አባታቸውን ሕልም በግብር እውንእንዲሆን ያበቁት ግን ከአብራኩ የወጡት የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) የትግራይ አርነት ሕዝባዊ ወያኔ (ሕወኣት) ናቸ ማለት ይቻላል። ኢሕአፓና ሕወኣት፣ መጀመርያው በኅብረብሔርነት ሁለተኛው በጐሣነት ላይ የተመሠረቱ የማይጣጣሙ ድርጅቶች መስለው ቢታዩም፣ በዓላማቸውና በርእዮታቸው ግን አንድመሆናቸው መረሳት የለበትም። የሁለቱም ዓላማቸው ሥልጣን ሲሆን፣ ተጠቀሙትም ከበስተጀርባቸው ያሉትን የአሳዳጊያቸውንና የአጋዦቻቸውን የመገንጠል ጥያቄ በኢትዮጵያ የጭቁን ብሔሮች ሽፋን ማስፈጸም እንደሆነ ድርጊታቸው ይመሰክራል። የሁለቱም አንጃዎች ርእዮተ ዓለም ከ፲፱፻፷ዎቹ የተማሪዎች እንቅስቃሴ በተዋሱት፣ ብሔር፣ ብሔረሰቦች የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው የመወሰን መብት እስከመገንጠልበሚል መርህ ዙርያ የተገነባ ሲሆን፣ ዋናው ልዩነታቸው የትኛው አስቀድሞ ይተግበርበሚለው ላይ ነው። ኢሕአፓትግሉ ሊሠምር የሚችለው በኅብረብሔራዊ ድርጅት ሲመራ ነውሲል፣ ሕወኣቶች በበኩላቸው፣ የለም፤ በቀዳሚነት የተለያዩ ጭቁንብሔር፣ ብሔረሰቦች በየራሳቸው ድርጅት አማካኝነት ትግላቸውን ጀምረው፣ ከዚያ በኋላየኅብረት ግንባር ሲፈጥሩ ነውበሚል አቋም ላይ ነው። ስለዚህ ሁለቱም ስልት እንጂርእዮተ ዓለም አይለዩም ማለት ተገቢ ነው  

ሁለቱም ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የሚያንቋሽሹ፣ አባቶችንና ታሪክን የሚያዋርዱ፣በአጉል ትምክህትና ትዕቢታቸው ያበጡ፣ የማይስማማቸውን በጭካኔ ከማረድ ወደኋላየማይሉ ለሥልጣንና ለገንዘብ ሲሉ አገር ከመሸጥ ወይንም ከጠላት ጐን ተሰልፈውመውጋት ዐይናቸውን የማያሹ ስለመሆናቸው በየጊዜው በተለያየ አጋጣሚ የፈጸሙትድርጊታቸው ይመሰክራል። በምንም አኳያ ቢታዩ፣ ሁለቱም አገርና ሥልጣኔ ጠንቅናቸው ማለት እጅግ የለዘበ አነጋገር ይመስለኛል። ሁለቱም በኢትዮጵያ ንታዊነትናታላቅነት አያምኑም። በነሱ አስተያየት፣ ከዚህ በላይ ደጋግመን እንዳየነው ዓለምየሚደነቅበት፣ የመላው ዓለም ጥቊር ሕዝብ የሚኰራበት የኢትዮጵያ ታሪክ የሚጀምረው ከአፄ ምኒልክ ሲሆን ሌላው የደብተሮች ፈጠራ ነው። ስድስት ዓመታት በላይ ያስጠረውን የኢትዮጵያ ሕዝብ የርስበርስ መወላለድ፣ በአምቻናበጋብቻ፣ በባህልና በሀብት፣ በቋንቋና በሃይማኖት መተሳሰር ይክዳሉ። ኢትዮጵያ ለነሱ፣አንድ አማራ በተባለ ጨቋኝ ብሔረሰብ ወረራ የተቋቋመች መቶ ዓመትየማይሞላ ታሪክ ያላት አገር በተጨማሪ፤ ኢትዮጵያ አማራው በሁሉም ዘርፍየበላይነቱን ይዞ የሚገዛባት፣ አማራ ሆነው ብሔረሰብ ግን በግፍ በገፍየሚማቅባት እስር ቤት በመሆኗ፣ ፈርሳ፣ ጨቋኝና ተጨቋኝ በሌለበት መልኩ በነሱአምሳል በአዲስ መልክ መገንባት ይኖርበታል ይላሉ

መጠነኛ የማሰብ ችሎታ ላለው ሰው የኢሕአፓ የሕወአት ርእዮተ ዓለምናስለኢትዮጵያ ታሪክ ያላቸው ግንዛቤ የሕፃናት ቧልት ከመሆን አያልፍም። ከዚህ በላይካየነው እውነኛው ሁናቴ ጋር እጅግ አድርጎ ይማታል፣ ይጋጫል። ይሁንና ኢሕአፓኢትዮጵያ ፍጻሜ በሚከተለው በምድረገነት ስብከቱ በአገር ፍቅር ስሜት የነደደውዘመናዊ ትምህርቱን ከነባ ሥርዐ ወግ ማጣጣም ያቃተውን፣ ቦዘኔውንናሕልመኛውን፣ እንዲሁም ግልቱንና ገልቱ ወጣት ቀልብ በሰፊው ሊስብ እንደበቃየማይካድ ሐቅ ይመስለኛል ሁኖም አብዛኞቹ ድርጅቱ ለሥውር ዓላማው ሲልየፈጠረው ነጭ ሽብር የተባለ የግድያ መፈክሩ ሰለባ በመሆን ለእንግልትና ለእልቂትዳረጉ፣ከመሪዎቹ ራሳቸው በከፈቱት ጦርነት ጥቂቶቹ ቢሞቱም፣ ብዙዎቹግን፣ቅዳቸው ሲባክንና ሲመክን እንደምንደኛ እረኛ ተከታዮቻቸውን ቀይ ሽብርበተባለ ጠላታቸው እጅ ጥለው ጓዛቸውን ጠቅልለው ወደውጭ አገር እንደፈረጠጡየቅርብ ጊዜ ታሪክ ስለሆነ እዚህ መድገም አይመስለኝም

ኢሕአፓ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ለማዳከም ቢቻልም ለማጥፋት ከተነሡትድርጅቶች አንዱ ቢሆንም ለሥልጣን ግን አልበቃም። በለስ የቀናለት ሕወአት ብቻነው። ሕወአት እንደኢሕአ በኤርትራ ነፃ አውጭ ድርጅቶች በተለይም በሻቢያተኰትኲቶ ቢያድግም፣ ለአፄ ምኒልክ ቤተመንግሥት ያጨው ግን በቀዝቃዛ ጦርነትፍጻሜ ማግሥት የተከሠተው አዲሱ የዓለም ኀይሎች አሰላለፍ ነው ማለት ይቻላልብቸኛ የዓለም ዘበኛ ሁና የቀረችው አሜሪቃ ስለኢትዮጵያ ያላት እይታ፣ ሥጋትናፍራቻ እንግሊዝ የዓለም ጠባቂ ከነበረበት ጊዜ የተለየ ልነበረም። አሜሪቃ በቀይ ባሕርአካባቢ ባላት ዘላቂ ብሔራዊ ጥቅሟ አኳያ ኢትዮጵያን ሲታያት አደገኛ አገር ሁና ነውያገኘቻት። የገዢዎ አገርወዳድነት፣የሕዝቧ ሥራአፍቃሪነትና ታታሪነት፣ የታሪኳታላቅነት፣ በመላው ዓለም በይበልጥ ደግሞ በአፍሪቃና በሦስተኛው ዓለም ካላትዕውቅናና ከፍተኛ ተሰሚነት እንደሌሎቹ የሦስተኛ ዓለም አገሮች በዓለም ባንክ ብድርሳትጨፈለቅ ምጣኔሀብቷን አስተካክ መጓዛ ጋር ተደራርቦ፣ በቀላሉ የማትገጠርአገር መሆኗ ሜሪቃን እጅግ ማሳሰቧ እንዳልቀረ መገመት ይቻላል በአ. . ከሺ፱፻፸፫እስከ ሺ፱፻፸፯ .. በውጭ አገር ጉዳይ ጸሓፊ የነበሩት ዶር. ሄንሪ ክሲንጀር ላገራቸውመንግሥት አቀረቡ የተባለ ዘገባ እንደሚያመለክተው፤ ኢትዮጵያ ዕድሏ ሁኖ በዘመናዊሥልጣኔ ገፍታ ራሷን የቻለች አገር ብትሆን በማንም የማትደፈር መሆኗ አይቀሬ ነውይላል ዶር. ክሲንጀር ይኸንን ሁናቴ አስቀድሞ ለመጋፈጥ ከተቻለም ማጨናገፍየሰጡት መፍትሔ ሰላም አገሪቷ እንዳይሰፍንሕዝቧ በጐሣ ሥርዐት ከፋፍሎርስበርሱ እየተጋጨ በማያባራ ሁኬት ተዘቅጦ እንዲኖር የሚረዳ መሆን አለበትይላበሳቸው ዘገባ መሠረት፣ ኢትዮጵያ ሰላም ካገኘች የማትቻል አገር ስለምትሆን፣

 አሜሪቃ በቀይ ባሕር ላይ ያላት ሚና ወደፊት ዋጋ እንዳያጣእንዳያድጉማሰናከል ከሚገባቸው በቀይ ባሕር አዋሳኝ ታዳጊ አገሮች መካከል አንዷ ኢትዮጵያመሆን አለባት። ስለዚህ ከንጉሥ ኀይሌ ሥላሴ በኋላ ኢትዮጵያን የሚመራመንግሥት ሰላም እንዳያገኝና፣ አገሪቷም እንደዐረብ አገሮች ተከፋፍላና ተነጣጥላእንድበታተ [ማድረግ ይገባል] መንግሥታችን [ቀይባሕር የበላይነቱን መጠበቅየሚችለው] ኢትዮጵያን ከጎረቤቷ ከሱማሌ ጋር ብቻ ሳይሆን፣ ከፍለ ገሮቿንራሳቸውን በሰሜንና በደቡብ ከፋፍሎ፣ ካማውን ወገን መርዳት፣ ያላመፀውንጐሣ እንዲያምፅ በማበረታት ከዳር ድንበሯ ዘላለም ሁከትና ጦርነት እንዳይለያትበማድረግና፣ ፀረመንግሥት ተዋጊዎችን በሲአይኤ አደራጅቶ ሰላም በአገሪቷበመንሣት ብቻ ነው።እኛ ያሳደግነው ውሻም ቢሆን ሊነክሰን ቢሞክርከሥልጣኑ ማስገልበጥ፣ ላንዲት ዘመን እንኳ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ሰላምሳይሰፍን ሰሜ ደቡ ማለትም ኤርትራ፣ ትግሬ፣ አማራ፣ ጋላ እየተባባሉ እርስበርሳቸው እየተነካከሱ ለረጅም ጊዜ ቈዩ ቀይ ባሕር ለአሜሪቃ መንግሥትጠቃሚ በር ሁኖ ይኖራል።

አሜሪቃ በርእዮተ ለማቸው የሚመሳሰትን ግን አገርወዳዶችና ፀረብሔርተኞችየሆኑትን ድርጅቶች በማግለልሕወአትን ለመደገፍ አላስፈላጊየተፍጨረጨረበትይኸንን ሥውር ዓላማዋን ለማሳካት ድርጅቱ ታማኝነቱንስላረጋገጠ መሆኑ የሚያጠራጥር አይመስለኝም። ግን ያንድ ጐሣ መንግሥት በመባልእንዳይወቀስ በተሰጠው ምክር መሠረት፣ ሕወአት ኅብረብሔራዊ የፖለቲካ ቡድኖችሕዝብ ከጠላውና ዐንቁሮ ከተፋው ከደርግ መንግሥት ጋር ተፋልሞ ድል ከተጐናፀፈበኋላ በአሜሪቃ ግፊትና ሳያስብበት በተፈጠረው መላ ኢትዮጵያን የመግዛት ዕድልታላቋን የትግራይ ነፃ ሬፓብሊክ የማቋቋም አሳቡን ለጊዜውም ቢሆን ለመጣል ተገደደከዚያም ለመርሀግብሩ አስፈጻሚ ናሉ ብሎ ያሰባቸውን አጋር ድርጅቶች ፈጥሮየኅብረብሔርነት ሽፋን ለመስጠት ሲል ከየብሔረሰቦቹ ወደመመልመል ዘመቻ ገባ።ኢህአፓ ከመሰሉ ግራዘመም አቀንቃኞች አቋሙን ለማሳመን የበቃውን በመቀላቀል፣ልግምተኞቹን በመደምሰስ አለበለዚያም ከአካባቢው በማባረር፣ ድርጅታዊ መዋቅርከሌላቸው ብሔሮች ደግሞ እንደራሱ መለስተኛ የማሰብና የመመራመር ችሎታያላቸውን እንደኅብረተሰቦቹ ልሂቃን በመምረጥ ከሰበሰበ በኋላ በአምሳሉየተፈጠረውን ይኸንን የጐጠኞችና የአገር ካጆች ክበብ ነው ለማለት የሚስከጅለውንየድርጅቶች ቅንጅት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) በሚል ስም አጠመቀው። ድርጅቶቹ ከበላይ ሁኖ ሚቈጣጠረው ዳግማዊ ወያኔበመባል ከሚታወቀው ሕወሓት በተጨማሪ፣ኢሕአዴግ በመነሻው ሌሎች ሦስትየጠባብ ብሔርተኞች ድርጅቶችን ያጠቃልል ነበር ሥልጣኑንም የተቋደሰው በሻቢያችሮታ እየተንቀሳቀሰ ክል ነው በሚልበት አካባቢ በጊዜው የነበረውን የፖለቲካ ቀውስበመጠቀም ይዞታውን ማስፋፋት እየተቀላጠፈ ይሯሯጥ ከነበረው ከኦሮሞ ነፃነትግንባር (ኦነግ) ጋር በር የኦነግ መሪዎች በሥልጣን ድርድር ባለመስማማታቸው ተዋጊወታደራቸውን በጦር ሜዳ ለጠላት ትተው በአይሮፕላን ሲፈረጥጡ፣ ኢሕአዴግብቻውን ያገሩ ፈላጭ ቈራጭ ሁኖ ርቷል  

ኢሕአዴግን ራሱን የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ብሎ ይጥራ እንጂ በተደጋጋሚ በሥራው ያስመሰከረው ግን የኢትዮጵያን ሕዝብእንደማይወክል፣ አብዮታዊነት እንደሌለው፣ የዴሞክራሲ ሆነ የኢትዮጵያናየኢትዮጵያዊነት ጠላት መሆኑን ብቻ ነው። ኢሕአዴግ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮአጉልቶ ያሳየው ነገር ቢኖር፣ የተዛባውን ሕወአት ርእዮተ ዓለም ማስፈጸሚያ መሣርያመሆኑን ነው። ገና ከበረኻ ትግሉ ወቅት ጀምሮ ሕወአት ሁለት ነገር እንደማያፋልሙዓላማዎቹ አድርጎ ይዟል። አንደኛ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ማጥፋት። ሁለተኛየኢትዮጵያ ሕዝቦች ጠላትና ጨቋኝ የሚለውን አማራን መደምሰስ።

ኢሕአዴግ አማራ ብሎ በሠየመው ኅብረተሰብ ላይ ብዙ ግፍ እንደፈጸመና እንዳስፈጸመበገፍ ተገልጿል ተፈጸሙ ከተባሉት ድርጊቶች አብዛኞቹ በሥዕል የተቀረጹ፣ ለሰውመብት በቆሙ ባስተማማኝ ብሔራዊና ዓለምዐቀፍ ድርጅቶች የተጠናቀሩ፣ እሙንበሆኑ ያይን ምስክሮች የተደገፉ ስለሆኑ ማስተባበሉ ከመደናቈርና የአትኳራ ግብግብከመግጠም ውጭ ሌላ ፋይዳ ያለው አይመስለኝም። የግፎቹ ኢሰብኣዊነትናየፈጻሚዎቻቸውም አውሬነት ለሚሰማ ሁሉ ከመዘግነን አልፎ፣ ሰው ሁኖ መፈጠሩንራሱን የሚያስጠላ ከመሆኑ የተነሣ፣ ልቦና ያለው ተመልካቺም ሆነ ሰሚ፣ በይስሙላመንግሥትነት በወያኔ የሚመራውን የኢሕአዴግ ገዢዎች በጀርመንና በኢጣሊያንምድር ከታዩት ከናዚና ከፋሽስት መንግሥታት መሪዎች በምን እንደማይለዩአስመስክረዋል ብል የተሳሳትሁ አይመስለኝም

እንግዴህ እዚህ ላይ ጽሑፌን ባጭሩ ልቃጭ። ኢትዮጵያ ታላቅና ረጅም ታሪክ ያላትምድር ናት። እሷን የመሰለ ክቡርና ስመጥሩ አገር ማስተዳደር ሰፊ ዕውቀትና ብልህነትይጠይቃል። የዘውዱን ሥርዐት የገረሰሰው የደርግ አገዛዝ የጥራዘ ነጠቆች ስብስብ እንደመሆኑ በሁለቱም ረገድ አልታደለም ከባዕዳን የተበደረውን ርእዮተዓለም በብረትኀይል ቢጭንባት አገሪቷ አልቀበለውም ብትለው ጭካኔና ግዽያ ተጠቅሟል። ኋላምበሰይፍ የገደለ በሰይፍ ይሞታልና ደርግ ኢሕአዴግ በተባለ ጉልበተኛ የጐሦችጥርቅም ድርጅት ከሥልጣኑ ለመባረር በቅቷል። ኢሕአዴግ የተካነው እንደደርግበገዳይነቱና የኢትዮጵያን ታሪክ በማዛነፍ ብቻ አይደለም። ከዘራፊነት አልፎ የአገሪቷንብቷን በመግፈፍ መሬቷን ሸራርፎ ለባዕዳን በመስጠት፣ ግዛቷን በመገነጣጠልምነው አባቶቻችንአገር ሲያረጅ ጃርት ያፈራልያሉት ምሳሌዊ አባባል እውነተኝነትአለው ብለን ካልተቀበልነው በስተቀር፣ በታሪኳ ያልተደፈረች፣ በሥልጣኔዋ የብዙዎችመመኪያና ኩራት የሆነች አገር እንዴት እንደዚህ በመሰለ በባዕድ አምላኪ፣ ለአገሩናለወገኑ፣ ለታሪኩና ለክብሩ ደንታ በሌለው፣ ከዚያም አልፎ ተርፎ በወንጀልና በዘረፋበተሰማራ አገዛዝ ሥር ልትወድቅ በቃች ለሚለው ጥያቄ የሆነ ያልሆነ መልስ በመስጠትከመቀባጠር ለጊዜው ሊፈታ የማይችል እንቆቅልሽ ነው ብዬ ማለፍ እመርጣለሁ።ካልሆነም መልሱን ለውድ አንባቢዬ እተወዋለሁ።

አሁን ባለንበት ወቅት አንድ ነገር ግልጥ እየሆነ ነው። ሕወአት በአጋር ድርጅቶቹመሣርያነት፣ ኢትዮጵያዊነትን ለመግደልና ከሕዝቡ ጭንቅላት መንቅሮ ለማዉጣትያልጠመደው ወጥመድ፣ ያልተጠቀመው መሣርያ፣ ያልፈጸመው ድርጊት፣ ያልደነገገውሕግ፣ ያልፈጠረው ምክንያት፣ ያልፈለገው ዘዴ ባይኖርም፣ እስካሁን ድረስኢትዮጵያዊነትንና የኢትዮጵያን አንድነት ሊያጠፋና ሊደመስስ ግን እንዳልቻለብዙዎቻችን እያየነው ነው። ለዚሁ ዓላማ ድርጅቱ ተግቶ በሠራ ቊጥርየኢትዮጵያዊነት መንፈስና ስሜት በአብዛኛው ዘንድ እየተጠናከረ እንጂ እየቀዘቀዘሲሄድ አልታየም። ይልቅስ ዛሬ ያለንበት የፖለቲካ ሁናቴ ሚያመለክተው፣ የኢሕአዴግመንግሥት ባለፉት ለሠላሳ ዓመት ያህል ሳይታክት ሸረበው ኢትዮጵያን የማፍረስ ደባከሽፎበት፣ አሁን በየቦታው በሕዝብ ዐመፅ እየተናወጠ ባለበት ወቅት መሪዎቹ መካከል አብዛኞቹ ሥልጣ ዕድሜያቸውን ለማራ ሲሯሯጡ ሌሎች ደግሞቅንነት የተላበሰ በሚመስል መንገድ የሙጥኝ ብለው ታላቂቷን ኩሩ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በመቈናጠጥ ላይ ናቸው

LEAVE A REPLY