ሃገር ቤት ስለ መግባት ወቅታዊ መግለጫ፣ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ት.ዴ.ት./TAND)

ሃገር ቤት ስለ መግባት ወቅታዊ መግለጫ፣ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ት.ዴ.ት./TAND)

ኢትዮጵያ ላለፉት 27 ዓመታት በህወሓት/ኢህኣዴግ መዳፍ ስር ወድቃ፣ ህዝቡ የብዝበዛና የኣፈና ሰለባ ሆኖ ሲማቅቅ እንደኖረ ዓለም የተገነዘበው ሓቅ ነው። ይህ እውነታ የወለደው ብሶት ህዝቡን ለኣመጽ ከማነሳሳት ኣልፎ ኢህኣዴግ እንዲናጋና ከውስጡም ኣዲስ የለውጥ ኣራማጅ ሓይል እንዲፈጠር አስገድዷል። ይህ በዶ/ር ኣብይ ኣህመድና በኣቶ ለማ መገርሳ የተመራው  የለውጥ ኣራማጅ ሓይል  ይዋልይደር ሳይል ኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ፈር አስይዞ፣ ከመከፋፈል ወደ አንድነት፣ ከኣፈና ወደ ነጻነት ትሸጋገር ዘንድ ታሪካዊ አስተዋጸኦ በማድረግ ላይ ይገኛል። ይህ ሓይል ሂደቱ እግቡ ለማድረስም በጠ/ሚ ኣብይ የሚመራ ኣዲስ መንግስት መስርቶ የለውጡን ጎዳና ተያይዞታል።

ይህ ህዝቡ የተዋደቀለት የለውጥ ሂደት እንዲሳካና ህዝቡ የተመኘው ፍትሃዊ ስርዓት እውን እንዲሆን ማንም ሰላም፣ እኩልነት፣ አንድነትና እድገት ፈላጊ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ያለማቋረጥ ሊደግፈውና ሊዋደቅለትም ይገባል። መገንጠልን በመቃወም፣ አንድነትን በማራመድ ከ30 ዓመታት በፊት ከህወሓት ተለይቶና 23 ዓመታት በስደት ላይ ሆኖ ሲታገል የቆየው ት.../TAND በዚህ የለውጥ ጎዳና እንደሚሰለፍ ከውጥኑ ጀምሮ በመደጋገም ግልጽ ኣድርገዋል። በሚልዮኖች የሚቆጠር የኣዲስ ኣበባ ህዝብ ቅዳሜ አደባባይ ወጥቶ ያሳየውን የድጋፍ ሰልፍም በሙሉ ልብ ኣድንቋል። ይህንን ታላቅ እርምጃ ለማደናቀፍ ሙከራ ያደረጉ ሽብርተኞችንም አምርሮ እያወገዘ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችንም ጽናቱን ይመኝላቸዋል።

እየተከሰተ ያለው የህዝብ እንቅስቃሴ የመጪው ፍትሃዊ ስርዓት አመላካች ነጸብራቅ ሆኖ እያለ፣ በሌላ በኩል ግን የድሮዎቹ የህወሓት/ኢህኣዴግ ባለስልጣናት ጥቅማቸውንና ስልጣናቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ የለውጥ ሂደቱን ለማደናቀፍ ልዩ ልዩ መሰሪ ዘዴዎች በመጠንጠንና ብሎም በመቃወም ላይ እንደሚገኙ ግልጽ እየሆነ መጥቷል። ይህ ዓይነቱ  የሃገርንና የህዝብን ብሩህ ተስፋ ወደ ጎን የሚገፈትር ጨለምተኛ እንቅስቃሴ ሁሉ ት.../TAND ኣሁንም ሮ ይቃወማል።  

የት.../TAND ማእከላይ ኮሚቴ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱትን ሁለቱ ተጻራሪ ክስተቶችና ባጠቃላይ በለውጡ ሂደት ላይ ማከል ያለበትን ኣስተዋጸኦ የሚገመግም ኣስቸኳይ ስብሰባ ከ 22 – 23 / 06 / 2018በማካሄድ የሚከተሉትን ውሳኔዎች ኣስተላልፏል።

1. .../TAND በሃገራችን እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ሂደት በመደገፍ ሙሉ ይሉን ሃገር ቤት ውስጥ ኣስገብቶ የበኩሉን ኣስተዋጸኦ ለማበርከትድምዳሜ ላይ ደርሷል።

2. .../TAND /የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) መስራች ኣባል ድርጅት ሆኖ የህብረቱን ዓላማ ከግቡ ለማድረስ ኣሁንም ተሳትፎውን የሚቀጥል መሆኑን ኣጽንኦት በመስጠትና፣ ለ/ እንደዚሁም ለውጡን ፈላጊ ከሆኑ የተለያዩ የትግራይ ንቅናቄዎች ጋር ያለውን ኣጋርነት በትጋት እንደሚገፋበት በማረጋገጥ፣ ኣሁን በሃገራችን ውስጥ የተጀመረው የለውጥ ሂደት ሳይደናቀፍ ይቀጥል ዘንድ ት.../TAND የበኩሉንኣስተዋጸኦ ማበርከት ይቻል ብሎ ስለኣመነ ባስቸኳይ ሃገር ቤት ለመግባት ወስል።

3. ይህ ውሳኔ በተግባር ላይ ይውል ዘንድ ኣስፈላጊ ሁኔታዎችን ለማመቻቸትና ከለውጥ ኣራማጆቹ ጋር ተቀራርቦ ለመመካከር በኣፋጣኝ አስፈላጊ እርምጃዎችን እንዲወስድ ውሳኔ ኣስተላልፏል።  

 ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

 26.06.2018

LEAVE A REPLY