ወዲ ብርሃነ “ኮሽ ባለ ቁጥር (በህወሃት) ማሳበብአስቂኝ ነው” ብሎናል። ልክ እንደ ቦስተን ማራቶን፤ ንጹሃን ዜጎች ላይ ቦንብ ሲወረወር፤ ሌላው ይጨነቃል፤ ኮካ ደግሞ ይስቃል። የቦንብ ፍንዳታ በተሰማ ቁጥር ሕዝብ የነሱን የፈስ ቡክ ገጽ ለመዳሰስ የሚሯሯጠው የተለመደ ፍንጭ ስለሚሰጠው ብቻ መሆኑን እንኳ ገና አልባነነም። የመረጃ ፍንጭ መስጠታቸው ባልከፋ፤ ግና ጉዳዩን ማን መመርመር እንዳለበት ኮካዎች የሚወስኑበት ዘመን፤ እንደ ፈርኦን አሽከሮች የባህር ውሃ ከበላው ወራት አለፉ።
ዘንግተነው ካልሆነ በስተቀር፤ በሟቹ ግዜም፤ “ነገ መርካቶ አካባቢ በአስር ሰዓት ቦንብ ይፈነዳል” እያሉ በብሄራዊ ቴሌቪዥን ይነግሩን ነበር። የአበሻ ዘር በወቅቱ ያስጨንቀው የነበረው ታዲያ የቦንቡ መፈንዳት ሳይሆን፤ ሊታሰሩ እቅድ የተያዘላቸው “አሸባሪዎች” ጉዳይ ነበር። ፍቅር እንደ ወንጌል እየተሰበከ ባለበት በዛሬ ዘመን ደግሞ የጅቦቹን የልብ ትርታ የሚለካልን ቴርሞ ሜትር የኮካዎቹ ገጽ ሆኗል።
“የቀን ጅቦች” የተሰኘው ነጠላ ስም እንደ ሰደድ እሳት ተለቆ፤ ጅቦቹም ያሻቸውን ሲያደርጉ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሁንም ፍቅርን ነው የሚሰብከው። እሳት ጫሪን ከመቅጣት ይልቅ፤ እነሱ የሚጭሩትን እሳት እየዞረ ማጥፋት የለት ስራው ስላደረገ። ይህንን በማድረግ ትእግስቱን ጫፍ ቢያመላክታቸውም እነሱ ግን በንቀት ያዩት ይመስላል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከኪነጥበብባለሙያዎች ጋር ውይይት አደረጉ የሚለውን መልካም ዜና ገና ሰምተን ሳንጨርስ የማግለል ፖለቲካ ጉዳይ ተከተለ። ተስፋ አስቆራጭ ዜና!
የአስቴር በዳኔን ከቤተ-መንግስት መባረር ስንሰማ፤ የዚያ ቫይረስ ተሸካሚዎች በኪነጥበብ ስም መስረጋቸውንያመላክተናል። ክስተቱ ያሳዝናል። ድርጊቱ በየትኛውምመስፈርት ቢለካ፤… የተፈለገው ምክንያት ቢደረደር፤ ስህተትያለመሆኑን አያስረግጥም።
ማቹ ጠቅላይ ሚንስትር ኪነ ጥበብ ባለሞያዎችን ባናገሩበትግዜ “ማን ይጠራ፧ ማን ይቅር፧ ማን ምን ይጠይቅ?” ሸፍጥ ሰዓሊ ስዩም አያሌው “ሰራዊትና ሰራዊቶቹ” በሚል ርዕስበአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ አስነብቦን ነበር። አቶ መለስ ከሰራዊት ፍቅሬ የወርቅ ብዕር ተሸልመው ነበር። ጋዜጠኞችን በማሰራቸው እና በፕሬስ አፈናቸው። አሁንም እነዚሁ ሰዎችቆባቸውን ቀይረው አዛዥ ሆነውልናል።
“ግዜው የመደመር ነው፣ ግዜው የምህረት ነው፣ ግዘውየይቅርታ ነው፣ ፍቅር ያሸንፋል።”.. ካልን አንዱን የበኩር ሌላውን ደግሞ የእንጀራ ልጅ የምናደርግበት ምክንያት አይኖርም። “አስቴር በዳኔ ለብቻዋ እውነትን የደፈረች ልጅተመርጣ ለምን ከአዳራሹ እንድትወጣ ተደረገ?” የሚለውጥያቄ ለብዙዎቻችን እንቆቅልሽ ሆኖብናል። ከጅቦቹ ጋርእየተሞዳሞዱ የማስታወቂያ ስራውን ጭምር ጠቅልለውየያዙት ግልገል ጅቦች እያሉ፤ ይህች ልጅ ለምን? “ኢትዮጵያዊ አይደለሁም” ይል የነበረው፤ ኦነግን ሳይቀር በሁለት እጃቸውተቀብለው ያስተናገዱ መሪ፤ ሃስዝብን በነጸ የገለጸ ዜጋ ላይ የማግለል ፖለቲካ ይሰራሉ ብለን ለመገመት ይከብደናል። የቀንጅቦቹ ያሉት ሁሉም ስፍራ ነው።
ዛሬ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያዊነት የሚቆረቆር መብዛቱ በጎ ነው። ከነፈሰው የሚነፍሱ ግብዞች፤ተቆርቋሪዎች እኛ ብቻ ነን ሲሉ ማየት ግን ያምማል።
አንዳንድ ቀላጆች እንደሚሉት አስቴር በዳኔ የጠቅላዩ ስልጠና አያስፈልጋትም፤ እስዋ አስቀድማ ተደምራለች እያሉ የሚነግሩን ቁም ነገር እንደተተበቀ ሆኖ፤ ጉዳዩን ከማድበስበስ ይልቅ ጸሃይ ላይ አውጥቶ ማስጣቱ ትምህርት ይሆን ይሆናል።
የድብቅ ፖለቲካ አይኖርም ተብለናል። ሃገርየምትተዳደረው ገንዘብ እና ጥላቻ ባሰከራቸው ካድሬዎችሳይሆን በፍቅር እና በህግ እንደሆነም ተነግሮናል። በጠቅላይሚንስትሩ የመደመር ራዕይ ላይ ጥርጣሬ እንዲፈጠር፤ ሌሎችንተስፋ የሚያስቆርጥ፤ ጥላሸት የሚቀቡ ወያላዎች የሚሰሩትተንኮል እንዳለ ይሸታል።
አርቲስትዋ በቤተ-መንግስት ደብተር እንጂ ድማሚትይዛ እንዳልገባች እርግጥ ነው። አስቴር ከሌሎች አርቲስቶችየተለየ ሃሳብ እንዳለትም ይታወቃል። የተለየ ሃሳብ ያለው ዜጋደግሞ አይደመርም የሚል ደንብ አልወጣም። የአርቲስትዋ ሃሳብ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ራዕይ ጋር የሚጻረርም አይደለም።
ከዚህ ቀደም፤ ህወሃት አርባኛ አመቱን ሲያከብር፤በደደቢት በረሃ ውስጥ ተገኝታ እንደሌሎቹ አላጎበደደችም።ይልቁንም በህወሃት አናት ላይ የሃሳብ ቦንብ አፈንድታእንደነበር እናስታውሳለን። በዚያ በአስፈሪ ድባብ ውስጥ ማይክጨብጣ፤ “እውነትን መናገር እወዳለሁ። … በእርግጥ የፖለቲካሰው አይደለሁም። …. እናንተስ በምርጫ ትወርዱ ይሆን?” ብላ ጠየቀች።
“ህዝብ ‘አጎብዳጆች’ ይለናል።” አለች አስቴር በዳኔ።የፖለቲካ አየሩ እንደዛሬው ጸዳ ያለ አልነበረም። የኪነ-ትበብሰዎቻችንን መፈተኛ ግዜ ነበር። ከአስቴር ውጭ ጥርስየሚያስነክስ አይደለም ተራ ጥያቄ እንኳን የጠየቀ አርቲስት አልነበረም። ሁሉም አሞጋሽ ነበር።
አስቴር በአለቆቻቸው ላይ እንደዚያ አይነት የድፍረት ቃልበመናገርዋ አርቲስቶቹ እንዳኮረፏት ሰምተን ተደንቀን ነበር።እነዚያ አሽቃባጮች ዛሬ የፊት ተሰላፊ ሆነው እስዋን ሲገፏትሰምተን ዝም ልንል እና ልናዝን አይገባም። የደደቢቱ ድፍረትዋ እስካሁን ብዙ አስከፍሏታል። የአሁኑ ድርጊታቸው ደግሞ፤ የቀንጅቦቹ ሆን ብለው ሞራልዋን ለመጉዳት ስራ እንደጀመሩ ቢያመላክትም፤ ኢትዮጵያ ሕዝብ በሚያከብራት እናበሚመሰክርላት ስለሆነች ልትኮራ ይገባታል። ምክንያቱም የሃቅን መንገድ መረተች እንጂ፤ ያላግባብ ባለሃብት እንደሆኑአርቲስቶች አጎብድዳ መኖርን አያቅታትም። ለቀን ጅቦች ዘንድሮ የሙስና በር የተዘጋ ይመስላል።
አስቴር ከአዳራሹ እንድትወጣ ተደረገ። ስልጠናው ቀጠለ። ኪነ ጥበብ በኢትዮጵያ ውስጥ በምን ሁኔታ ላይእንደሚገኝና የንፅፅር ትምህርት ሰጥተዋል ተብሏል። ስልጠናውን የወሰዱት አርቲስቶች በቴሌቭዥን የሰጡዋቸውን ቃላትም ሰምተናል። ራያና ቆቦ!
የዶክተር አብይ ሰዎችን ለስልጠና ሲጠሩ የሰልጣኞችን እውቀት፤ የግንዛቤ እና የትምህርት ደረጃ መጥነው ቢያቀርቡ ይመረጣል። ትምህርቱ እንዲዋሃዳቸው ምንም የእንግሊዝኛ ቃልባይጠቀሙ ደግሞ መልካም ነው። ለምሳሌ እነ ሳሞራን ሲያሰለጥኑ ትምህርቱን ያዘጋጁት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ስለነበር ሰዎቹ ገለጸውን ለመረዳት እንደተቸገሩት በግልጽ ይታያል።
የአርቲስት ሰርጸ ፍሬ ሰንበት እና የተዋንያን ሰለሞን ቦጋለን ከስልጠናው በኋላ ተጠይቀው የሰጡትን መልስ ብቻ ሰምቶ አርቲስቶቹ ስልጠናውን እንዳልተከታተሉት መገመት ይቻላል። ሰለሞን ቦጋለ እንዴት መስራት እንደሚገባን አቅጣጫ ጠቋሚ ትምህርት ነበር ሲል። ሰርጸ ግን ከኮሚኒስት ተኮር ጥበብ ነጻ ሆነን መስራት እንደሚገባን … ለምሳሌ ግድብ ሲሰራ ስለ ግድብ ዝፈኑ ከሚል ዕዛ ይልቅ አርቲስቱ በራስ ፈጠራ እንዲመራ የሚል አስተምሮት እንደሆነ ነግሮናል።
ከመጣው ጋር ማሸርገድን አቁሙ ሲሉ ምክር እንደሰጡም ምንጮች ገልሰዋል። በተለይ ድምጻዊ ጌትሽ ማሞእና ቴዎድሮስ ተሾመን በስም ጠርተው “አብረን አድገናል።ጓደኛ ነን። አሁን ቤተሰብ ነን.. ምናምንም ማለታችሁን አቁሙ ማለታቸውን ቃሊቲ ፕረስ ዘግቧል። እንደ ዶ/ር አብይ ገለጸ ሁሉም የኪነጥበብ ሰው እኩል ነው መታየት ያለበት። እርግጥ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ስሙን የተሸከመ ሁሉአርቲስት አይደለም። ከጥበብ ይልቅ ንዋይ ያስቀደመ ሁሉ አርቲስት አይባልም። “ገንዘብን ሳይሆን ጥበብ አስቀድሙ” ይላሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ። እንደዚህ አይነቱ አስተምሮት እንደ አስቴር በዳኔ ላሉ አርቲስቶች አያስፈልጋቸውም።