ሰልፉ ባየሁ ቁጥር የትግራይ ህዝብ ለዚህ አለመታደሉ ውስጤ ያለቅሳል

ሰልፉ ባየሁ ቁጥር የትግራይ ህዝብ ለዚህ አለመታደሉ ውስጤ ያለቅሳል

የባህርዳሩን ሰልፍ አየሁት፣ በጣምም ተገረመኹኝ፣ ብአዴንሙሉ በሙሉ ከድሮ የህውሓት ተላላኪዎቹ ባይጸዳም፣ በሰልፉተገኝቶ ለለውጡ አጋር መሆኑን እና ዋና ተዋናይ መሆኑን በም/ል ጠ/ሚ እና በክልሉ ፕሬዝዳንት ደጋግሞ ጠቅሰዋል።

ብአዴን አመራር በተለይ ገዱ አንዳርጋቸው ህውሓቶችን እንዲህ ሲልይገልጻቸዋል “ሽንፈታቸው መቀበል ያቃታቸው የኣሮጌ ዘመንቁማርተኞች” ገዱ ከልቡ ከሆነ ጨዋታው ገብቶታል ማለት ነው!የትግራይን ህዝብ እና ህውሓትን ለይተዋል፣ በጣም እናመሰግናለን።

እኔ እንደ ትግራዋይ ግን፣ ሰልፉ ባየሁ ቁጥር የትግራይ ህዝብ ለዚህ አለመታደሉ ውስጤ ያለቅሳል ”የኣሮጌ ዘመን ቁማርተኞች” (ህውሓቶች) የትግራይ ህዝብ ከሌላው ህዝብ ነጥለው፣ለማጣላት፣ ለማዋጋት የሚያደርጉትን ጉዞ ሳይ ከዚህ ቦሃላምየትግራይ ህዝብ ለኣሮጌ ዘመን ቁማርተኞች ብሎ ገና ብዙ ዕዳእንደሚከፍል ይታየኛል። ለኣሮጌ ዘመን ቁማርተኞች ስልጣን ላይለመቆየት ተብሎ የትግራይ ተወላጆች በወሎ በባቲ የማይገባመስዋእትነት እየከፈሉ ይገኛሉ።

የኣሮጌ ዘመን ቁማርተኞች የትግራይ ህዝብ ጸረ ኢትዮጲያ ህዝብ ለማሰለፍ በአማራ ክልል፣ በደቡብ ክልል ገንዘባቸውን አፍስሰው ትናንት ደደቢት በነበሩበት ጊዜ የቀለባቸውን ህዝብ እንዲገደል፣ ንብረቱ እንዲወድም እናሌላውን ቢሄር እንዲጠላ እያደረጉ ነው! ህውሓቶች ቂመኞች! እባቦች! ከመሆናቸውም ጭምር፣ ልባቸውለፍቅር ሳይሆን ለቂም ብቻ የተፈጠረ ስለሆነ፣ ገዱ ለወ/ሮእማዋይሽ፣ ጀነራል አሳምነው ሲያቅፍ፣ የኣሮጌ ዘመን ቁማርተኞች ለአቶ ገብሩ አስራት፣ ለወ/ሮ አረጋሽ አዳነ፣ ለዶ/ር አረጋዊ በርሀ የፍቅር፣ የይቅርታ ልባቸውን እስካሁንዋ ሳአት ድረስ ክፍትአይደለም።

                                                                                                                                                                                                                                                                                                                    ወ/ሮ እማዋይሽ ከገዱ አንዳርጋቸው ጎን ተቀምጠውሳይ፣ የዓረናዋ የሽብርተኛ እስረኛ አደይ አልጋነሽ እና የአስራሰባትአመት ፍርደኛ (እስረኛ) ወጣት ፍስሃጽዮን ተኽለሃይማኖትከደብረጽዮን፣ ከስብሓት ጎን አለማየቴ አዝናለሁኝ ውስጤምያለቅሳል። ጀነራል አሳምነው ከም/ል ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን ጎንሳይ እድሜ ልክ የተፈረደበትን የዓረና ትግራይ እስረኛ (ፍርደኛ) አቶ ገብረእግዝአብሄር ታደሰ ከስዩም መስፍን ጎን አለማየቴአዝናለሁኝ አለቅሳለሁኝም።

LEAVE A REPLY