/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/ ፡ – በአሁኑ ሰዓት የጥቁር ገበያና የባንክ ምንዛሬ መቀራረብ ወደፊት ሊያስከትል የሚችለው ቀውስ አሳሳቢ ሆኗል። የአብይ አህመድ መንግስት የገበያ ሁኔታውን ለመቆጣጠር በተለይ የውጭ ምንዛሬ ላይ ከፍተኛ ስራ በመስራት ላይ መሆኑን ያሳወቀ ሲሆን በውጭ ሀገር የሚኖሩ “ዲያስፖራ” ኢትዮጵያዊያን አስተዋጾ እንዲያደርጉ መጠየቁ ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎ ሰሞኑን ኤርፖርትን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች ዘመናዊ መሳሪያዎች ተገጥመው ገንዘብ ከሃገር ውስጥ በህገወጥ መንገድ እንዳይወጣ ፍተሻ መጀመሩን ምንጮቻችን ገልፀዋል። በተያያዘ ሀገር ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ገንዘባቸውን ባንክ ውስጥ እንዲያስገቡ ግፊት እየተደረገ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
አንድ አንድ የመንግስት ወሰጥ አዋቂዎች በተለይ በአሁኑ ሰዓት የዶ/ር አብይ መንግስት “ሌቦች” በማለት የሚጠሯቸውን በምዝበራ የህዝብንና የመንግስትን ገንዘብ በአደባባይ በመዝረፍ የሚታወቁ ግለሰቦችን ለማዳከም ከፍተኛ እንቅስቃሴ የተጀመረ ሲሆን መንግስት ይህንን በግለሰቦች እጅ የገባ ጥሬ ገንዘብ ለመቆጣጠር አዲስ ገንዘብ አሰከማሳተም የዘለቀ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል ለመረዳት ተችሏል።
[ኢትዮጵያ ነገ ዜና]