ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
“ለውጥ ጥቂት ንቁ የሆኑ የለውጥ አራማጆችን እና
ለውጥ ተመልካቾች ከዳር ተቀምጠው የሚመለከቱት እ
የመልካም ሀሳብ አላሚ እና የጽናት ሰው እንሁን፡፡ ማንዴላ የኢትዮጵያ ወጣቶች የተወደደውን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ለመፍጠር እና የመልካም ሀሳብ አላሚዎች እንድንሆን ያስተምሩናል፡፡ ምክንያቱም የኢትዮጵያ መልካም ቀኖች እየመጡ ነውና፡፡
እ.ኤ.አ ታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም አቅርቤው በነበረው ትችቴ ለኢትዮጵያ ወጣቶች የሚል ምክር አቅርቤ ነበር፡፡
እንደመር! አንቀነስ! እንባዛ! አንከፋፍል!
በነብይነት ባህል ለኢትዮጵያ ምሁራን መናገር [ 1]
የጸሀፊው ማስታዋሻ፡ በኢትዮጵያ ለአብይ አህመድ ቡድን አባዥዎች ምልመላ በድፍረት እራሴን የሾምኩ ዲያስፖራ ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ እና ቡድናቸው በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ አዎንታዊ ነገሮች እና የመጨረሻ ለውጥ እንዲመጣ ከፍተኛ ተጋድሎ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
ሆኖም ግን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እና ቡድናቸው ብቻውን ሀገሪቱ ከገጠማት የምጣኔ ሀብት ቀውስ ሊያድናት አይችልም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ከብዙ ዘመናት ጀምሮ ተጋርጠውብን የቆዩትን የውስጥ እና አህጉራዊ ችግሮች በመፍታት ድህነትን፣ ድንቁርናን እና ደካማ የጤና አገልግሎቶችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ማስወገድ አይችሉም፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እና ቡድናቸው ዕገዛን ይፈልጋሉ! አሁኑኑ፡፡
ስለሆነም በይፋም ሆነ ይፋዊ ባልሆነ፣ ወይም ደግሞ በቀጥታም ሆነ ቀጥተኛ ባልሆነ፣ ወይም መደበኛም ሆነ መደበኛ ባልሆነ መልኩ በእኔ በእራሴ ተነሳሽነት የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስት በዲያስፖራው ውስጥ ያለውን የምሁራን እና ባለሞያዎችን ኃይል እንዲደምር እና ኢትዮጵያን ከአምባገነናዊ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ሽግግር እንዲያደርግ፣ ከጎሳ ጭቆና ወደ ብሄራዊ አንድነት፣ ነጻነት እና ከጥፋት ለመዳን ከጎናቸው እንዲሰለፉ ለማድረግ በእራሴ ህሊና ወስኛለሁ፡፡
ለበርካታ ዓመታት የኢትዮጵያን ምሁራን ወገኖቼን በተለይም በዲያስፖራው የሚገኙትን በኢትዮጵያ ውስጥ ለሰብአዊ መብት መከበር እና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ በንቃት እና በቀጥታ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጥሪ ሳቀርብ ቆይቻለሁ፡፡
ሆኖም ግን ሳቀርባቸው የቆየኋቸው ተደጋጋሚ ጥሪዎች ጆሮ ዳባ ልበስ ተብለው የቆዩ መሆናቸውን ሳስብ ሀዘን ይሰማኛል፡፡
አሁን እያቀረብኩት ባለው በዚህ ማስታዋሻዬ ኢትዮጵያን ከጎሳ ዘረኛ አምባገነናዊ ስርዓት ወደ ብዙሀን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት፣ ከወሮበላ ዘራፊ መንግስት ወደ ተጠያቂነት እና ግልጽነት ወዳለው መንግስት ሽግግር ለማድረግ ሌት እና ቀን በመስራት ላይ የሚገኙትን ጠቅላይ ሚኒስትራችንን ቡድናቸውን ለማገዝ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ምሁራን እና ባለሞያዎች ከጎናቸው እንድንሰለፍ እንደገና በድጋሜ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡
በአሁኑ ጊዜ ለምናካሂደው ተግባራዊ ድርጊት እያቀረብኩ ያለሁት ጥሪ ግን የተለዬ ነው፡፡
የአሁኑ ጥሪዬ የኢትዮጵያ የነብስ አድን ጥሪ ነው፡፡
ነብሳችን ከአንድ የጭቆና አገዛዝ ቡድን ወደ ሌላ የጭቆና አገዛዝ ቡድን እንዳትሸጋገር ለማዳን የቀረበ ጥሪ ነው፡፡
የኢትዮጵያን ነብስ ለማዳን እና ነጻ ለማድረግ የቀረበ ጥሪ ነው፡፡
ኢትዮጵያ በእራሷ ቀጥ ብላ እንድትቆም የቀረበ ጥሪ ነው፡፡
ኢትዮጵያ እንድትነሳ፣ እንድትራመድ እንድትቆም እና እንድትደመር የቀረበ ጥሪ ነው፡፡
በዲያስፖራው ማህበረሰብ ውስጥ ለሚገኙት የኢትዮጵያ ምርጥ እና የብሩህ አእምሮ ባለቤቶች በአሁኑ ጊዜ የአትዮጵያ የፍቅር ባቡር ለመንቀሳቀስ ዝግጅት ሲያደርግ በባቡሩ ጣቢያ ሆነን ዝም ብለን በመመልከት ላይ መሆናችንን ፍጹም ግልጽ ላደርግ እፈልጋለሁ፡፡ በባቡሩ ውስጥ ለመሳፈር ወይም በባቡር ጣቢያው ውስጥ በመሆን ሳንሳፈር ለመቅረት ለመወሰን በጣም ትንሽ ጊዜ ብቻ ቀርታናለች፡፡ የአብይ ቡድንን ለመቀላቀል እና አንድ ነገር በማድረግ ነጻነትን እና ክብርን አውጆ መኖር ወይም ደግሞ ቀሪውን ህይወታችንን ምን እየተደረገ እንደሆነ፣ ምን ማድረግ እንደሚቻል እና ምን መደረግ እንዳለበት እያሰላሰልን በማቃሰት የመኖር ምርጫ አለን፡፡
በአሁኑ ጊዜ በአንድ ላይ የመቆም እና የመደመር ጊዜ ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ለአንድ መቶ ሚሊዮን ሕዝቦች ሁነኛ ለውጥ ለማምጣት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ አሁን መጀመር አለብን!
“ለሕዝብ የተሻለ ነገር ለማድረግ እና አንድ ነገ ር ለማድረግም ዕድሉ እያለህ ያንን ነገር ማድረግ ካልቻልክ ጊዜህንበምድር ላይ በከንቱ አባክነሀል ፡፡”
አሁን በቅርቡ ለመገናኛ ብዙሀን በሰጠሁት መግለጫ ለኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ ምሁራን እና ባለሞያዎች ስንጠብቀው የቆየነው ጊዜ የደረሰ (ወይም ለጥቂቶቻችን ደግሞ ለማስወገድ የምንሞክረው) መሆኑን አውጃለሁ፡፡
አንዳችን እና እያንዳንዳችን የኢትዮጵያ እውነተኛ ልጅ መሆናችን የሚታይበት ወይም ደግሞ ግድ የሌለን እና ከውጭ የቆምን የውጭ ተመልካች ሰዎች እና እንግዶች መሆናችን የሚጋለጥበት ቅጽበት ነው፡፡
በአብይ አህመድ የኢትዮጵያ የፍቅር ባቡር ለመሳፈር ወይም ደግሞ ባቡሩ ባቡር ጣቢያውን ለቆ ሲወጣ ለመመልከት ብቻ የተዘጋጀን መሆናችን እና በመጨረሻም ወደ ታሪክ ቆሻሻ የምንጣል ለመሆናችን የምንወስንበት ጊዜ አሁን ነው፡፡
የኢትዮጵያ የፍቅር ባቡራችን ወደ አንድ መዳረሻ ብቻ ሊመራ የሚችል አንድ ሀዲድ ብቻ ነው ያለው፡፡
የኢትዮጵያ የፍቅር ባቡር መዳረሻ “የተወደደች/ዉድቷ ኢትዮጵያ” እየተባለች የምትጠራ በተራራው ጫፍ ላይ እያንጸባረቀች የምትገኝ ከተማ ናት፡፡
ወደ ባቡሩ ምንም ዓይነት ጓዝ እና ጭነት ማምጣት አያስፈልግም፡፡ ነጻ ጉዞ ነው፡፡ ከስራ መሳሪያዎቻችሁ እና ከሙያዎቻቸሁ ጋር ብቻ መምጣት ነው፡፡
ሳይንቲስቶች፣ አጉሊ መነጽሮቻችሁን ማይክሮስኮፖቻችሁን እና የርቀት ማሳያ መሳሪያዎቻችሁን/ቴሌስኮፖቻችሁን አምጡ፡፡ ሐኪሞች እና የጤና ባለሞያዎች የልብ ማዳመጫ እና የሙቀት መለኪያ መሳሪያዎቻችሁን አምጡ፡፡ መሀንዲሶች እና የስነ ህንጻ መሀንዲሶች ፕሮትራክተሮቻችሁን አምጡ፡፡ የሕግ ባለሞያዎች የሕግ መጽሐፎቻችሁን አምጡ፡፡ መምህራን ጠመኔዎቻችሁን እና ወረቀቶቻችሁን አምጡ፡፡ የባንክ እና የቢዝነስ ባለሞያዎች የተሰመሩ ወረቀቶቻችሁን/spreadsheets አምጡ፡፡ ጸሐፊዎች እና ተመራማሪዎች ህትመቶቻችሁን አምጡ፡፡ አርቲስቶች የቀለም ቡርሾቻችሁን እና የሙዚቃ መሳሪያዎቻችሁን አምጡ፡፡ ሁላችሁም የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ምሁራን እና ባለሞያዎች የምትሰሩባቸውን መሳሪያዎች በሙሉ አምጡ፡፡ “የተወደደችዋን ኢትዮጵያን” በምንገነባበት ቦታ ሁላችሁንም እንፈልጋችኋለን፡፡
ኢትዮጵያ በልግስና ትታደላለች፡፡
በዲያስፖራ ወይም በሌላ የሚኖረው እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በፈቃደኝነት ቦታ እና ሚና አለው፡፡
እነዚህን ነገሮች የምለው እንዲሁ በአላሚነት ህልመኛ ነው ልትሉ ትችላላችሁ፡፡
አዎ፣ ህልመኛ አላሚ ነኝ፡፡ ከቀድሞ ጀምሬ ሳልም የቆየሁ፡፡
እ.ኤ.አ ሀምሌ 2012 ዓ.ም እንዲህ የሚል አንድ ህልም ብቻ እንዳለኝ ተናግሪያለሁ፡ “ኢትዮጵያ በሰላም ጎዳና“
እ.ኤ.አ ሀምሌ 2012 ዓ.ም በተጨማሪ መልካም ነገር እና ይቅርባይነት በሚባሉ መንገዶች ላይ ጉዞ እንደምናደርግ ተናግሪያለሁ፡፡
እ.ኤ.አ ሀምሌ 2018 ዓ.ም ህልሜ እውን ሆነ፡፡ በመጨረሻም በመልካም ነገር እና በይቅርባይነት መንገድ ላይ አብይ አህመድን አስከትለን በመጓዝ ላይ እንገኛለን፡፡
ስለሆነም ለሁሉም ዲያስፖራ የኢትዮጵያ ምሁራን እና ባለሞያ ወገኖቼ ከአብይ አህመድ ጋር በመቀላቀል እና በኢትዮጵያ የፍቅር ባቡር በመሳፈር እንዲህ የሚለውን የጆን ሌኖን መዝሙር እየዘመራችሁ እንድትጓዙ ሞቅ ያለ ግብዣዬን አቀርብላችኋለሁ፡
ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝቦች በሰላም እንደሚኖሩ አስ ቡ፡፡
ህልመኛ ነህ ልትሉን ትችላላችሁ፡፡ ሆኖም ግን እ ኔ ብቻ አይደለሁም፡፡
ሆኖም ግን እንደ እኔ ያሉ ሌሎች አንድ መቶ ሚሊ ዮኖች አሉ፡፡
አንድ ቀን አሁን በቅርቡ ወደ እኛ ልትቀላቀሉ ት ችላላችሁ፡፡ እናም ኢትዮጵያ አንድ ትሆናለች፡፡
እ.ኤ.አ ሀምሌ 12 ቀን 2012 ዓ.ም ለኢትዮጵ ያ ምሁራን እና ባለሞያዎች ያስተላለፍኩት ትንቢታ ዊመልዕክት፣
እ.ኤ.አ ሀምሌ 12 ቀን 2012 ዓ.ም ለኢትዮጵያ ምሁራን ካስተላለፍኩት መልዕክት ይልቅ አሁን እያስተላለፍኩት ያለው መልዕክት ለእውነታ የበለጠ እንደሚደውል አምናለሁ፡፡
እ.ኤ.አ ሀምሌ 15 ቀን 2012 ዓ.ም ለኢትዮጵያውያን ምሁራን እና ባለሞያዎች እንዲህ የሚለውን አስቸኳይ ሁኔታ በመጥቀስ የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፊያለሁ፡
በአሁኑ ጊዜ በአንድ ላይ መቆም እና መደመር አለ
በጊዜ ሂደት በለውጥ ላይ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ምሁራን በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ከዳር ቆመው መመልከት አይችሉም፡፡ ቶማስ ፔይን እንዳስቀመጡት “የበጋ ወታደሮች፣ የጸሐይ ብርሀን
የኢትዮጵያ ምሁራን ኢትዮጵያን ከአገዛዝ ወደ ዴሞክራሱ ለማሸጋገር የመረጃ እና የእውቀትን ክፍተት ለመሙላት እና ከአዲስ እና ፈጠራ ከታከለባቸው ሀሳቦች ጋር በመምጣት እራሳቸውን ማደራጀት አለባቸው፡፡
ኢትዮጵያን የሚያጠኑ ሁሉም ምሁራን በአሁኑ ጊዜ አስቸኳይ ሁኔታ ገጥሟቸዋል፡፡ እስከ አሁን ድረስ በእራሳቸው ላይ ነግሶ የቆየውን ዝምታ ወይም ደግሞ እራሳቸውን በሾሙ እና ለእራሳቸው ብቻ ትክክለኛ የሆነ ዴሞክራሲን አንግበው ሌላውን እየተቹ ባሉት ላይ ዝምታን በማስወገድ ኢትዮጵያ ከአምባገነናዊ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲ በምታደርገው ሽግግር እገዛ ማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡
በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ በመስቀለለኛ መንገድ ላይ ቆማለች፡፡ የለውጥ ምልክቶች በጉልህ ይታያሉ…
…የኢትዮጵያ አምባገነኖች የመንፈላሰሻ ጊዜዎች ተጠናቀዋል፡፡ እነዚህ እድለ ቢስ ቀኖች የተስፋ መቁረጥ እርምጃዎችን በመውሰድ የመጨረሻ ጨዋታቸውን በመጫወት ላይ ለሚገኙት እድለቢስ አምባገነኖች ቀኖች ናቸው፡፡
የኃይማኖት ጽንፈኝነት የእሳት ነበልባል ለማቀጣጠል ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ በሁሉም መንገዶች ላይ ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብቶችን ለማዳፈን የሞት ሽረት ትግል በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ በስልጣን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ለመኖር ለመናገር የሚዘገንን የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመፈጸም ላይ ይገኛሉ፡፡
በመጨረሻም በአሁኑ ጊዜ እየተገነዘቡት ያለውን ሙዚቃቸውን እና እንዲህ የሚለውን የጋንዲን እውነተኛ መልዕክት በመጋፈጥ ላይ ይገኛሉ፡
“ጨቋኝ አምባገነኖች እና ገዳዮች አሉ፡፡ ለጊዜው
ስለሆነም በመጨረሻው ጨዋታ ጨቋኞች እና ገዳዮች የዕቅድ መፍትሄ እና እንስሳዋ እንዳለችው የድሮ አባባል እንዲህ የሚለውን የመጨረሻ የጥሩምባ ካርዳቸውን ይመዛሉ፡ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል“
ሆኖም ግን እነርሱ ያሰቡት የጎርፍ ማዕበል፣ የእሳት ቋያ እና የመሬት መንቀጥቀጥ ምንም ዓይነት ልዩነት ሳይፈጥር በመንገድ ላይ ሁሉ ያገኘውን እነርሱን ጭምር ዶግ አመድ እንደሚያደርግ አልተገነዘቡትም፡፡
…ሆኖም ግን እነዚህ ቀኖች በተጨማሪ ለህዝቡ የተስፋ ቀኖች ናቸው፡፡ በመጨረሻ በጭቆና አገዛዝ ጉድጓድ ታነል ላይ የብርሀን ብልጭታ ሊመለከቱ ይችላሉ፡፡ ወደ ነጻነት፣ ዴሞክራሲ እና የሕግ የበላይነት የሚያመላክቱ ቀንዲሎችን መመልከት ይችላሉ፡፡
የጠረጴዛዎች የእይታ ድባብ በፍጹም ተቆይሯል፡፡ ህዝቡ ጨቋኞችን መፍራቱን አሽቀንጥሮ ጥሎታል፡፡ ጨቋኞች ግን ህዝቡን መፍራታቸውን በማሳየት ላይ ናቸው፡፡ ህዝቡ ምን ሊያደርግ እንደሚችል በፍርሀት ይጨነቃሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ህዝቡ እየተበሳጨ እና እየተራበ ነው፡፡ ንዴት ወደ ቁጣ፣ ጥላቻ እና የኃይል እርምጃ ይቀየራል፡፡ ረሀብ ሰውነትን ብቻ አይደለም የሚያጠፋው ሆኖም ግን ነብስን ጭምር እንጅ፡፡ የተራበ ሰው የተበሳጨ ሰውም ጭምር ነው፡፡ ለዚህም ነው በጨዋታው የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ጨቋኞች ፍርሀት እንደሚኖር የተጻፈው፡፡
የኢትዮጵያ ልሂቃን እና ምሁራን የሰውን ጨቋኝነት ብቻ ሳይሆን የርሀብን፣ የበሽታን፣ የድንቁርናን እና የድህነትን ጨቋኝነት ጭምር ለማጥፋት ሙያቸውን፣ ክህሎታቸውን እና እውቃታቸውን አንዱ ለሌላ ማካፈል አለባቸው፡፡ ጨቋኝነት በሁሉም አቅጣጫ መወጋት አለበት፡፡ የረሀብ እና የድርቅ ጨቋኝነትን ለመዋጋት ዕቅድ ለመንደፍ እና ድል ለመቀዳጀት የግብርና ባለሞያዎች ተግባር ነው፡፡ የኢትዮጵያ የትምህርት ባለሞያዎች በተስፋ እጦት የበሰበሰውን የትምህርት ጨቋኝነት ስርዓት ለመገዳደር መነሳት አለባቸው፡፡ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ሀኪሞች በሕዝቦቻችን ላይ ስቃይ ያነገሰውን የበሽታን ጨቋኝነት ለማጥፋት ኃይላቸውን ማሰባሰብ አለባቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ በጭጋጎ በመስራት ላይ ያሉት ኢትዮጵያውያን ሀኪሞች ብዛት በመላ ኢትዮጵያ ተሰራጭተው ከሚገኙት ሀኪሞች የበለጡ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚስቶች፣ መሀንዲሶች፣ ሳይንቲስቶች፣ የሕግ ባለሞያዎች፣ የታሪክ ምሁራን፣ አርቲስቶች፣ ተመራማሪዎች፣ ወዘተ. ወደ አንድ በመምጣት ህብረት መፍጠር እና ጨቋኝነት የሚገለጽባቸውን ሁሉንም ነገሮች መዋጋት አለባቸው፡፡
በእራስ የሙያ መስክ የእራስን ክህሎት መጻፍ እና መናገር የስራው የመጀመሪያ ምዕራፍ ነው፡፡ የኢትዮጵያ የአካዳሚክ እና ምሁራን ማህበረሰብ አባላት ከዚህም በተጨማሪ የአደባባይ ምሁራን እንድትሆኑ እማጸናለሁ፡፡ ኢንተርኔት በዜጎች እና በኃይለኛ መንግስታት መካከል ትልቅ እኩልነትን ለማምጣት ብቻ የተቀመጠ መሳሪያ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን በምሁራን እና በደናቁርት (አውቀው ደናቁርት በሆኑት እና በድንቁርና ለታወሩት) መካከልም ጭምር የሚሰራ እንጅ፡፡
በበርካታ መንገዶች ኢንተርኔት ሀሳብን በነጻ ለመግለጽ ሙሉ ነጻነት ይሰጣል፡፡ የተማሩ ምሁራን እና የአካዳሚክ ሰዎች በአንድ በኩል እና ለጥፋት የሚያነሳሱ ቃላትን የሚተፉ፣ ወደፊት ጥላቻ እና አለመቻቻልን የሚፈጥሩት በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሕዝቦች ልቦች እና አእምሮዎች እኩል ተደራሽነት አላቸው፡፡ ሆኖም ግን ሁሉም በኢንተርኔት ከሚገኙ መረጃዎች እና ሀብቶች በጣም ውድ እና ጠቃሚ፣ ብርሀን ሰጭ እና በተግባር ለመፈጸም የሚችሉ ጥቂት ነገሮች ብቻ አሉ፡፡