የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትሕዴን/ የትጥቅ ትግል ማቆሙን አስታወቀ

የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትሕዴን/ የትጥቅ ትግል ማቆሙን አስታወቀ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- መቀመጫውን በኤርትራ ያደረገው የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ትህዴን) ወይም ዴምህት የትጥቅ ትግል ማቆሙን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ:: የድርጅቱ መግለጫ እንደሚያመለክተው ከ17 ዓመታት በፊት ወደ ጫካ ገብቶ ሲታገል እንደቆየና  ከዛሬ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም ጀምሮ የትጥቅ ትግሉን ማቆሙን አስታውቋል።

 በዶክተር አብይ አህመድ የሚመራው የለውጥ ሀይል ወደ ስልጣን የመጣው ድርጅታችንና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ የትግል ውጤት መሆኑን በማመን እንደሚደግፍም ገልጿል።

ትህዴን ባወጣው መግለጫ በሀገር ውስጥና በየግንባሩ የሚገኙ አባላቱ ከማንኛውም የሀይል እንቅስቃሴ እንደቆጠቡ ሲል መመሪያ አስተላልፏል።

 በመጨረሻም ዴምህት ወደዚህ ውሳኔ ሲደርስ አሁን ባለው ስርዓት ህዝባችን ሙሉ በሙሉ ለውጥ ሊያገኝ ይችላል ከሚል እምነት የተነሳ ሳይሆን፤የተገኘውን እድል በመጠቀም በሀገራችን በሚካሄደው ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል በተለይም በትግራይ ክልል ውስጥ ከሚቀሳቀሱ እንደ አረና እና በህወሓት ውስጥ ከሚገኙ ለውጥ ፈላጊ ሀይሎች ጋር አብሮ ለማስራት መዘጋጀቱን ጨምሮ አስታውቋል።

LEAVE A REPLY