የደህንነት አባላት ከፓርቲ አባልነት መውጣት አለያም ተቋሙን መልቀቅ እንዳለባቸው ተገለጸ

የደህንነት አባላት ከፓርቲ አባልነት መውጣት አለያም ተቋሙን መልቀቅ እንዳለባቸው ተገለጸ

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የፖለቲካ ፓርቲ አባል የሆኑ የብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች ከፓርቲ አባልነት መውጣት አልያም ተቋሙን መልቀቅ እንዳለባቸው የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል አደም መሀመድ አስጠነቀቁ።

ብሄራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት ከፖለቲካ ወገንተኝነት የፀዳ እንዲሁም ለህዝብ የቆመ እንዲሆን የሪፎርም (ለውጥ) ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም አስታውቀዋል። ተቋሙን ከፓለቲካ ወገንተኝነት ነፃ ከማድረግ ባሻገር ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚሰራበትና የሚሳተፍበት ይደረጋል ማለታቸውን ኢቲቪ ዘግቧል።

ጄኔራል አደም ይህን ያሉት ለሶስት ቀናት የሚቆይ አዲሱን አመራር የሚያስተዋውቅና የሪፎርም ስራዎች ላይ ውይይት የሚደረግበት መድረክ በአዲስ አበባ ሲጀመር ነው።

በአሁን ወቅት ከመንግስት በተሰጠው አቅጣጫና በህዝብ ጥያቄ መሰረት ተቋሙን የህዝብና የሀገር ማድረግ ስራ እየተከናወነ መሆኑንና በአገልግሎት ማሻሻያው በተሰጠው ሀላፊነትና ስልጣን መሰረት የፖለቲካ ወገንተኝነት ሳይኖረው ኢትዮጵያውያንን እኩል ማገልገል እንዲችል እየተሰራ ነው ብለዋል።

የብሄራዊ የመረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኞች ህግና ስርዓትን ተከትሎ እንዲሰሩ ጄኔራኩ አሳስበዋል።

LEAVE A REPLY