የኤትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ በረራ ጀመረ፤ ሃሳብ በቅርቡ አገልግሎት ይጀመራል

የኤትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ በረራ ጀመረ፤ ሃሳብ በቅርቡ አገልግሎት ይጀመራል

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- ከ20 ዓመታት በላይ ተቋርጦ የነበረው የሁለቱ ሀገራት የአየር ትራንስፖርት ዛሬ በይፋ ስራ ጀምሯል። በዛሬው የመጀመሪያ በረራ የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ የኪነ_ጥበብ ሰዎች፣ ነጋዴዎች፣ ጋዜጠኞችና ሌሎች ግለሰቦችም የተካተቱበት 450 ሰዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡

ተጓዦቹ አስመራ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የኤርትራው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳለህና በሌሎች ባለስልጣናት ደማቅ አቀባበል መደረጉን የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትሩ የማነ ገ/መስቀል ገልጸዋል።

አዲስ አበባ_አስመራ በሳምንት ሁለት ጊዜ መደበኛ በረራ እንደሚኖር የተገለፀ ሲሆን ኢትዮጵያ አየር መንገድ የትኬት ቢሮውን በአስመራ ከፍቷል።

የኢትዮጵያና ኤርትራን በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፍ ለማስተሳሰር ከፍተኛ ጥረት እየተካሄደ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን እስካሁንም የአየርና የምድር ትራንስፖርት፣የስልክና ፓስታ፣ዲፕሎማሲ ግንኙነት ተጀምሯል። በቅርቡም ኢትዮጵያ የአሰብን ወደብ ለመጠቀም ፈጣን እንቅስቃሴ መጀመሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም መግለጻቸው ይታወሳል። ወደ አሰብ የሚወስደው መንገድ ጥገና እየተደረገለት መሆኑም ተሰምቷል።

LEAVE A REPLY