/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የአባይ (ህዳሴው) ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ስመኘው በቀለ መስቀል አደባባይ በመኪናቸው ውስጥ ሞተው መገኘታቸው ተገልጿል። ዛሬ ሐምሌ 19/2010 ዓ.ም ጠዋት ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን አስከሬናቸው ለምርመራ ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል መወሰዱን ፖሊስ ገልጿል።
በመኪናቸው ውስጥ ሞተው የተገኙት ኢንጂነር ስመኘው በተገደሉበት ወቅት የመሳሪያ ተኩስ የሰሙ በአቅራቢያው የነበሩ እማኞች ለፖሊስ በመደወል ሁኔታውን ያሳወቁ መሆኑ ታውቋል።
ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ላለፉት ሰባት ዓመታት የህዳሴው ሀይል ማመንጫ ግድብ ግንባታን በዋና ስራ አስኪያጅነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል።
በሌላ ዜና
የብአዴን ማዕከላዊ ጽ/ቤት ሀላፊ የነበሩት አቶ ተስፋየ ጌታቸው በአሜሪካን ሀገር በህክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት ምሽት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የአማራ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
አቶ ተስፋየ ጌታቸው በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ሂደት በመምራት ከፍተኛ ድርሻ እንደነበራቸው ይታወቃል።