የኢንጂነር ስመኘው በቀለን ግድያ ተከትሎ በተለያዩ ቦታዎች ተቃውሞ እየተደረገ ነው

የኢንጂነር ስመኘው በቀለን ግድያ ተከትሎ በተለያዩ ቦታዎች ተቃውሞ እየተደረገ ነው

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- የኢንጂነር ስመኘው በቀለን ግድያ በመቃወም የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ ከሰዓት ወደ አደባባይ ወጥተዋል።

በከተማ ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል። እስካሁን ንብረትነቱ የወያኔ የሆነው አንድ ሰላም ባስ በእሳት ጋይቷል። የኢንጂነር ስመኘው በቀለን የተቀነባበረ ግድያ ባስቸኳይ ተጣርቶ ለህዝብ ይፋ እንዲሆንም ጠይቀዋል። የተቃውሞ ሰልፉ እስካሁን እንደቀጠለ ነው።

በሌላ በኩል በሺህ የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጣቢያ በማምራት የኢንጂነሩን ግድያ በፅኑ ተቃውመዋል። ሰለፈኞች ካሰሟቸው መፈክሮች መካከልም “ሀገር  አትፈራርስም፣ ኢንሳ በአስቸኳይ ግድያውን  አጣርቶ ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ፤ የኢንጂነር ስመኘው ደም ፈሶ አይቀርም፤ ኢትዮጵያ ነጻ ትውጣ” የሚል ድምፅ አሰምተዋል።

ሂደቱ የፌዴራል ፖሊስ ዛሬ  ከሰዓት በኋላ በሰጡት መግለጫ ኢንጂነሩ ቀኝ ጆሮ በኩል  በጥይት ተመትተው ህይወታቸው ማለፉን ገልጿል። በቀኝ እጃቸው በኩል ኮልት ሽጉጥ መገኘቱንም ጠቁመዋል፡፡ ፖሊስ አስከሬኑ የተገኘበት መኪና የፎረንሲክ ምርመራ አድርጓል፡፡ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የአስከሬን ምርመራ እየተደረገ መሆኑም  የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል ተናግረዋል፡፡ በመስቀል አደባባይ የነበረው ካሜራ ከመንገድ  ስራ ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል ከቦታው መነሳቱን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል፡፡

LEAVE A REPLY