የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሞሃመድ ኡመር በቁጥጥር ስር ዋሉ

የቀድሞው የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ሞሃመድ ኡመር በቁጥጥር ስር ዋሉ

ሰበር ዜና፡-

/ኢትዮጵያ ነገ ዜና/፡- በትናንትናው ዕለት ከሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንትነት የተነሱት አብዲ ሞሃመድ ኡመር(አብዲ ኢሌ) በመከላከያ ሰራዊት አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቢቢሲ ሶማልኛ ዘግቧል።

አብዲ ኢሌ በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ከዋሉ  በኋላ ጅጅጋ ከሚገኘው ቤተ መንግስት እንደተወሰዱ የአይን እማኞች ለቢቢሲ ሶማልኛ ገልጸዋል።

አብዲ ኢሌ ተነስተው በምትካቸው አቶ አህመድ አብዲ ሞሃመድ የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆነው በስራ አስፈፃሚ አካላት ትናንት መመረጣቸው መገለጹም ይታወሳል።

የአብዲ ኢሌን መታሰር ተከትሎ የክልሉ ልዩ ፖሊሶች፣ ሄጎ የተባሉ ወጣቶችና አንዳንድ የአብዲ ኢሌ ቅርብ የሆኑ ባለስልጣናት ግጭት ለማስነሳት ጥረት እያደረጉ መሆኑንም ከስፍራው ሚወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል።እነዚህ አካላት የጅጅጋ ከተማ ነዋሪዎችን ጦርነት ሊቀሰቀስ ነው በሚል ፕሮፖጋንዳ ከተማውን ለቀው ወደ ገጠር እንዲሸሹ እየቀሰቀሱ ነውም ተብሏል።

ባለፈው ቅዳሜ የጀመረው አለመረጋጋት በርካታ ሰዎች የሞቱ ሲሆን የእምነት ተቋማት፣ባንኮች፣የንግድና መኖሪያ ቤቶች መውደማቸውን ሲዘገብ መቆየቱ ይታወሳል።

LEAVE A REPLY